በመሪጌታ ገብረ መድኅን | ልሳነ ተዋህዶ ሚድያ
የወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ እና ተከታዮች የሚከተሉት የክህደት እምነት ።
🔹 በካህን አይቆርቡም - ቀይ ዝክር ብላ ቂጣ ጋግራ የምታቆርባቸው እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ናት።
🔹 በካህን መስቀል አይሳለሙም
🔹 ልጅ ወልደው ጸበል አያስረጩም ክርስትናም አያስነሱም- ማርያም ክርስትና አንስታላችኋለች በማለት የምታጠምቅላቸው እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ናት።
🔹 ወንድም ይሁን ሴት ከቤቷ የሄደውን በ40 እና በ80 ቀኑ ክርስትና ተነስቶ ክርስትና ስም የተሰጠውን ማተብ ያሰረውን - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ የክርስትና ስሙን ቀይራ ሌላ ስም ትሰጣለች
🔹 በ40 እና በ80 ቀኑ የተሰጠውን የክርስትና ማተብ - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ከአንገታቸው ላይ በጥሳ ሌላ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ክር ታስራለች።
🔹 የንስሐ አባት የላቸውም በካህን ንስሐ አይገቡም - የንስሐ አባታችሁ ፃድቁ አቡነ ተክለ ሐይማኖት ናቸውና ለፃዱቁ ንገሩ ትላለች።
🔹 ሲታመሙ - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ጸበል ታጠምቃቸዋለች
🔹 ቅባ ሜሮን - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ትቀባቸዋቸች
🔹 ራሳቸውን ላጭታ ቄድር - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ታጠምቃለች።
🔹 አሥራት በኩራት፣ መብዓ፣ ስዕለት እና ሙዳዬ ምፅዋት ለቤተ ክርስቲያ እንዳይሰጡ ይልቁንም ለእርሷ እንዲሰጡ - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ መመሪያ ትሰጣለች።
🔹 ቤተ ክርስቲያን ሂደው እንዳይሳለሙ - እራሷ ወ/ሮ ትግስት ፍትሐወቅ ከልክላለች።
ስለ በዓላት እና አጽዋማት
🔹 በእነሱ ቅዳሜ ሰኞ ነው እሑድ ማክሰኞ ነው። ስለሆነም ለእነሱ ረቡዕ ሰኞ ስለሆነ ረቡዕ ስጋ ይበላሉ።
🔹 7ቱ አጽዋማትን ሽራ በራሷ አጽዋማት ቀይራለች
🔹 የዘመን መቁጠሪያውን ቀይራ በራሷ ዘመን ትቆጥራለች ለምሳኔ አሁን በሷ 2022 ነው።
🔹 የጳጉሜ ቀኗ 7 ነው በማለት ቀይራለች
🔹 በ30 ቀን ያሉ ሁሉንም የወራት እና የዓበይት በዓላትን ቀናቸውን ቀይራለች።
በእምነት ዙሪያ
🔹 ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለውን ስም ከዳ ቀይራለች ወይም አትጠራም።
🔹 ጌታ የተጠመቀው በ 7 ዓመቱ ነው ብላ ክዳለች።
🔹 ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቀው 14 ዓመቱ ነው ብላ ክዳለች።
🔹 ጌታ በምድር ላይ የኖረው 42 ዓመት ነው ብላ ክዳለች።
🔹 እመቤታችን በምድር ላይ የኖረችው 72 ዓመት ነው ብላ ክዳለች።
🔹 ታቦተ ፅዮን በአክሱም የለችም የግሸን ደብረ ከርቤ የጌታን መስቀልም በግሸን የለም። ቅዱስ ሚካኤል አምጥቶ ሰጥቶኝ እኔ በጄ ተረክቤያለሁ። አሁን በእኔ ቤት ውስጥ ነው ያሉት ብላለች።
🔹 በመኖሪያ ቤቴ ውስጥ 80 ታብታት አሉ ብላለች።
🔹 በመኖሪያ ቤቴ ውስጥ 42 ጸበል አለ ብላለች።
➤ በአጠቃላይ 7ቱን አጽዋማት እኛ ስንጾም እሱ አርደው ይበላሉ።
➤ የሚገርመው ደግሞ የወ/ ሮ ትግስት ፍሐወቅ ተከታዮች በመላው ዓለም እንደ አይጥ እየተሹለከለኩ አሉ።
➤ ከላይ ለዘረዘርኳቸው የክህደት መልእክቶች የቪዲዮ ማስረጃ ከፈለጋችሁ በውስጥ መሥመር ጠይቁኝ ከራሷ አንደበት ትሰማላችሁ ለመላክ ዝጉጁ ነኝ።
የዚችን ሴትዮ አባሎቿን የምትለዩበት መንገድ በጥቂቱ፦
1ኛ. አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የአንገት ክር ያደርጋሉ።
2ኛ. የሚያደርጉት መስቀል ወጥ የሆነ ሆኖ ከመስቀሉ
ላይ 5 ነጠብጣብ ያለቀት።
3ኛ. ነጭ የራስ ሻሽ ከነጭ ነጠላ ጋር በላ ዩላይ ቀሚስ
ይለብሱበታል።
🔹 ሁላችንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን እንጠብቅ!!
0 Comments