የአለባበሳችን ውጥንቅጥ !











 ጥንተ ዓለም ፡ ሰይጣን ፡ በሔዋን በኩል ገብቶ ዓለምን አቆሸሸ ፡፡ አሁን ፡ በዘመናዊ ሴቶች ገብቶ ዓለምን እያገማ ነው ፡፡ አለባበሳቸው ከእግዚአብሔር ፍጡርነት አውጥቶ አውጥቶ ወደ - ሰብአዊነት ለውጧቸዋል ፡፡ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ !!! ልብስ ሳይጠፋ ራቁት ወፍራም ልብስ ሳይጠፋ  ወንፊት ልብስ ጨርቅ ሳይጠፋ ታይት ፡፡ ዳሌና ጭን የሚያሳየው ከብት ነበር ስጋው ስለሚበላ ፡፡

  ሴቶቻችን አንድ የተበላሸ ነገር አለ ዳሌን በሱሪ ወጥሮ መሄድ ! ጭንን በሱሪ ወጥሮ መሄድ አወ ለሰይጣን ገበያ እየቀረቡ ነው ፡፡ ገዣቸው ሰይጣን ነው፡፡ ቢዮንሴ እኮ ናት እኔ እግዚአብሔር ነኝ ያለችው !!!! አቤት ድፍረት ግዜው አልቋል ፡፡ ፍየል ነበረች ብልቷን ከፍታ የምትሄደው፡ አሁን ዘረ ሔዋን በታይት ሰውነታቸውን ሸፍነው ግን እንደ ጓንት ወጥረው ጉባኤ ገብተዋል ፡፡ እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ !!! አይናቸው በጥቁር ቀለም የቀለመ ፡፡ ከንፈራቸው በቀይ ደም የቀላ ፡፡

አንገታቸው የጌጥ ዘንዶ /ሀብል/የዞረው ፡  እጃቸው በቆርቆሮ የተሽቆጠቆጠ፡፡ ታድያ ይህ ክስ ወንዶችንም ይጨምራል። ነገ የት እንምንገባ እንጃ ? እንደ ዘመነ ኖህና ሎጥ የዘመኑ ፍጻሜ ደርሷል ፡፡  
አመታቶች ቀርተውታል ዘመኑ ስለደረሰበት ሰይጣን ህዝቡን ወደ ሲዖል ይዞ
  ለመግባት እየሮጠ ነው ፡፡ በተለይ ሴቶችን እንደ ፈረስ እየጋለበ ነው ፡፡ ቸቸቸቸቸ ፈረሴ !!! ፋሺን ልብሱ ጫማው ዊጉ ቀለሙ ፡ሽቶው ኩሉ የነሱ ነው ፡፡ ቢያንስ በምድር ይዘንጡ ብሏል ዳቢሎስ ፡፡ የሚጣሉኝ ሴቶች ጓደኞቼ ተጣሉኝ ፡፡ 100  ቢያንስ 3 ከመቶ ንጹህ ናቸው ፡፡ ያውም በገጠር ያሉት ፡፡ ከተመኞቹ እማ ........ ቆንጆ ነሺ እያልኩኝ ገደል አልከትሺም ! ቆንጆ ነሽ ለሰይጣን ውዳቂ ነሽ ለአምላክ! አንዳንዴ ሳስብ ሞቴን እመኛለሁ፡፡ የሞቱት አባቶቻችን እናቶቻችን የታደሉ ናቸው ፡፡

[ምሳሌ ፳፫ ፡ ፳፩]
"ሰካራምና አመንዝራ ይደኸያል ፥ እንቅልፋምም ሁሉ የተቦጫጨቀ ጨርቅ ይለብሳል።"


Post a Comment

0 Comments