የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ መጨረሻ


በጣም ዝነኛ ነው፡፡ ዝናው ከሚኖርባት ሀገረ አሜሪካ አልፎ መላው አለም ድረስ ነው፡፡ በተለይ በ 2000ዎቹ አካባቢ ዝናው ጣራ ነክቶ ነበር፡፡ ይህ ሰው Michael D wayne Charter ወይም በመድረክ ስሙ Lil wayne ይባላል፡፡ በይበልጥ የሚታወቀው Lil wayne በሚባለው የመድረክ ስሙ ነው፡፡ በሚሰራቸው የ Hip Hop ሙዚቃዎች በኛ ሀገር ታዳጊዎችና ወጣቶች ዘንድ በስፋት የሚታወቀው Lil wayne ... አሁን ያለበት ደረጃ እጅግ በጣም አሳሳቢ እና አስከፊ ነው፡፡ Lil wayne ከጅምሩ ከፍተኛ የሆነ የማሪዋና እና ኮኬይን እፅ ሱሰኛ ነበር፡፡ ይህ የ 37 አመት ራፐር በአሁኑ ሰአት የአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ መጥቶ ለመመልከት ራሱ የሚያስፈራ የፊት ገፅታ እና የሰውነት አቋምን ይዞ ይገኛል፡፡ ህይወቱም እጅግ የተወሳሰበና የተበላሸ ሆኗል፡፡ መኖር እስኪያስጠላው ድረስም ራሱን ጠልቷል፡፡


ዝነኛና ሀብታም በነበረበት ወቅት ያካበተውን ሀብት እና ንብረት በሙሉ ለአደንዛዥ እፅ አውሎ ባዶውን ቀርቷል፡፡ የኔ የሚለው ምንም ገንዘብ እና ንብረት የለውም፡፡ ዘንድሮ የ 37ኛ አመት ልደቱን ሊያከብሩለት በመኖርያ ቤቱ የተገኙት የድሮ ጓደኞቹና የሙያ አጋሮቹ ልደቱን ሊያከብሩ ሔደው ... ልደቱን ከማክበር ይልቅ በሱ ሁኔታ እጅግ አዝነውና ተክዘው ነበር የተመለሱት፡፡ ብዙ ምእራባዊያን ዝነኛ አርቲስቶች የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ ሆነው ይገኛሉ፡፡ የዚህ ራፐር ግን ከሌሎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ የሚወስዳቸው እፆች ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ ከካናቢስ ፣ ከኮኬይን እና ከሔሮይን ጀምሮ ... አደንዛዥ እፅ የተባለ ሁሉ የሱ ወዳጁ ነው፡፡ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ከሞት ጋር እየተፋጠጠ ያለው ይህ ሰው ትልቅ ፀሎት እና የወዳጆቹ ርብርብ ያስፈልገዋል፡፡ የሰይጣን መጨረሻ እንግዲህ ይሄ ነው፡፡ ንሰሀ ገብቶ ፊቱን ወደ ፈጣሪው እስካልመለሰ ድረስ አሁንም የሰይጣን መጫወቻ ከመሆን የሚድን አይመስልም፡፡

ይህንን ፅሁፍ የፃፍኩት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ ... አደንዛዥ እፅን እንደ ቀልድ መጠቀም የጀመሩ በሂደት ደግሞ የእፁ ሱሰኛ ሆነው የቀሩ ብዙ ታዳጊ እና ወጣቶች አሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ... ይሔ ካናቢስ ወይም ማሪዋና የሚባለው እፅ ከመስፋፋት አልፎ በአንዳንድ የክልል ከተሞቻችን ላይ በትላልቅ ማሳዎች ጭምር ተተክሎ ይገኛል፡፡ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት መጨረሻው ይሄ ነው፡፡ መጨረሻው ስቃይ ነው፡፡ መጨረሻው ከሰውነት ውጪ መሆን ነው፡፡ እንደ ቀልድ በማሪዋና የሚጀመር የአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት ወደ ኮኬይን እና ሔሮይን አድጎ መውጣት የማይቻልበት ምስቅልቅል ህይወት ውስጥ ይዘፍቃል፡፡

Post a Comment

0 Comments