የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቴላቪቭ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም መዛወሩን አስመልክቶ በሚደረገው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ለመታደም ወደ እስራኤል ገብተዋል፡፡
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ለመታደም ከተገኙት መካከል የፕሬዚዳንት ትራምፕ ልጅ ኢቫንካ ትራምፕና ባለቤቷ ጃሬድ ኩሽነር ይገኙበታል፡፡
የኤምባሲው ዝውውር ከተሰማበት ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ምስራቅ እየሩሳሌምን የወደፊት ዋና ከተማቸው አድርገው በሚያስቡ ፍልስጤማውያን ዘንድ ቁጣ እንደቀሰቀሰ ይታወሳል፡፡
የዛሬው የኤምባሲው የመክፈቻ ስነስርዓት እስራኤል ከተመሰረተችበት 70ኛ ዓመት ጋር መግጠሙ ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በስነስርዓቱ ላይ በቪዲዮ መልዕክት ንግግር ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሆ ሁሉም ሀገራት የዩናይትድ ስቴትስን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሆኖም የአውሮፓ ህብረት በመግለጫው የኤምባሲ ዝውውሩን አጥብቆ ተቋውሟል፡፡
በርካታ ፍልስጤማውያንም የኤምባሲ ዝውውሩን በማስመልከት የተቋውሞ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ሲሆን፥ በጋዛ ያለውንም ቀውስ የከፋ ያደርገዋል እየተባለ ነው፡፡
ምንጭ፦ቢቢሲ

0 Comments