
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በቅስና የሚያገለግሉ ሰዎች እጥረት እንደገጠማት ሲነገር ቆይቷል፡፡ በተለይ በላቲን አሜሪካ አህጉር ሰፊ ቁጥር ያለው ተከታይ ያላት ቤተክርስቲያኒቱ በዛ ቀጠና በቅስና የሚያገለግሉ ሰዎች ከፍተኛ እጥረት ገጥሟታል፡፡ በአማዞን ደን በተሸፈኑ ሀገሮች በዚህ ስራ የሚያገለግሉ ሰዎች ፍላጎት ቀንሷል፡፡
አሁን ግን ከቫቲካን እንደተሰማው ይህን ችግር ለመፍታት ያገቡ ሰዎችን በቄስነት ለመቅጠር በቤተክርስቲያኑ ባለስልጣናት እየተመከረበት መሆኑ ተነግሯል፡፡ ያገቡ ሰዎች በቅስነት እንዲያገለግሉ የሚያስችል እቅድ ለውሳኔ መቅረቡ ተዘግቧል፡፡
የላቲን አሜሪካ ሊቀጳጳሳት ቫቲካን የቀረበውን እቅድ እንድታጸድቅና በቀጠናው ያጋጠመው የቄሶች እቅድ እንዲቀረፍ ጫና እያሳደሩ ይገኛል፡፡ በቤተክርስቲያኑ ህግ መሰረት ለቅስና አገልግሎት የሚሾሙ ሰዎች ያላገቡ እንዲሆኑ ይገደዳሉ፡፡ አሁን ላይ ግን ይህን ህግ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ቫቲካን እየመከረችበት ትገኛለች ነው የተባለው፡፡
0 Comments