ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ዚካ ቫይረስ በእንግዴ ልጅ በኩል አደርጎ ሽሉን የሚያጠቃ የሚበክል ሲሆን የሽምጥ ሸለቆ ትኩሳት ወይም ሪፍት ቫሊ ፊቨር የሚባለው አዲሱ ቫይረስ ግን ሽልን በተለያየ መንገዶች እንደሚጎዳ አንድ ተመራማሪ ገለፁ፡፡
አዲስ የተገኘው ጥናት እንደሚያሳየው በወባ ትንኝ አማካኝነት በሚፈጠረው በዚህ ቫይረስ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ከተጠቃች በሽሉ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን እንደሚደርስ ተገልጿል፡፡
ሳይንቲስቶቹ ለምርምራቸው ቫይረሱ እንግዴ ልጅን እንዴት ሊያጠቃ እንደሚችል ለማወቅ በቫይረሱ የተጠቁ አይጦችንና የሽል ቲሹዎችን የተጠቀሙ ሲሆን በውጤቱም ቫይረሱ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 በመካከለኛው አሜሪካና በደቡብ አሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን አካል ጉዳተኛ ካደረገው ከዚካ ቫይረስ ይበልጥ ሽልን እንደሚጎዳ ደርሰውበታል፡፡
ሪፍት ቫሊ ፊቨር በዋናነት ከሰሃራ በታች በሚገኙ ከብት አርቢ አካባቢዎች የሚከሰትና ከ90 እስከ መቶ በመቶ የሚሆኑ ላሞች ውርጃና የሞቱ ጥጃዎችን ስለሚወልዱ በኢኮኖሚያቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደሩ ታውቋል፡፡
ሆኖም በሽታው በየዓመቱ በሰዎች ላይም የሚከሰት ሲሆን ጉንፋን መሰል ምልክቶች ሲኖሩት በጉበት ላይም ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡
ወረርሽኙ እንደፈረንጆቹ 2000 መጨረሻ ከአፍሪካ እንደተነሳና በሳውዲ አረቢያም ተከስቶ ከመቶ ሺህ በላይ የሆኑ ሰዎችን እንዳጠቃና ወደ 7 መቶ የሚሆኑትም ሕይወታቸው እንዳለፈ ተነግሯል፡፡
የጥናቱ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ሃርመን እንደሚሉት የዓየር መዛባት በኢንፌክሽን ምክንያት ለሚተላለፉ በሽታዎች መንስኤዎች ናቸው፡፡
እስካሁን ድረስም ክትባትም ሆነ መድኃኒት ያልተገኘለት ሪፍት ቫሊ ፊቨር አሳሳቢ በመሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስነግሯል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡

0 Comments