የሲጋራ ማጣሪያና በዘዙሪያው የሚገኝ ላስቲክ በዓለም ላይ ቁጥር 1 በካይ ነው ተባለ፡፡



የሲጋራ ማጣሪያና በዘዙሪያው የሚገኝ ላስቲክ በዓለም ላይ ቁጥር 1 በካይ ነው ተባለ፡፡ ሳር መሰል የፕላስቲክ ቦርሳና መያዣ መስፋፋት በካይ በመሆኑ ትኩረት ያሻዋል ተብሏል፡፡ ሌላው አሳሳቢና ትልቅ ነገር ደግሞ ከእይታ ውጭ የሚገኙ የሲጋራ ማጣሪያዎች ናቸው ተብሏል፡፡ እነዚህ የሲጋራ ቁርጥራጭና ማጣያ ላስቲኮችም በዓማችን በብክለት ቀዳውን ደረጃ የያዙ ናቸው ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
በርካ አጫሾች የሲጋራው መያዣና ማጣሪያ የሚበሰብስ ይመስላቸዋል ግን በተቃራኒው ነው ሲሉ በካፎርኒያ ሳንፍራንሲስኮ ዩኒቨርሲቲ በትንባሆ ቁጥጥር ፖሊሲ ላይ የሚሰሩት ኤልሳቤጥ ስሚዝ ገልጸዋል፡፡
በዓለማችን በየዓመቱ 6 ትሪሊዮን ሲጋራ የሚመረት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት የላስቲክ መጠቅለያና ማጣሪያ ያላቸው ናቸው ብሏል፤ እነዚህ ተደምረው 1 ሚሊዮን ቶን ላስቲክ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡
እነዚህ የሲጋራ ላስቲኮች ምድራችን ከመበከላቸው በተጨማሪም ወደውቅያኖስ ሲለቀቁም በአሳና በሌሎች የባህር እንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሱ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡
የአውሮፓ ህብረት አሁን ችግሩን ለመፍታት እየሰራሁ ነው ያለ ሲሆን የሲጋራ ቁርጥራጮችን ለማጽዳት የሚያስችል አዲስ ህግ ያስፈልጋል፤ ሲጋራ አምራቾችም ለዚህ ስራ አስፈላጊ ገንዘብ ሊበጅቱ ይገባል ብሏል፡፡
ፈንድስ ኦፍ ዘ አርዝ በተባለ ተቋም ንቅናቄ የሚያካሂደው ማደህብ ቦልገርበ እናዳለው መንግስታት በጉዳዩ ላይ አጥብቀው መስራት እንዳለባቸው አሳስቧል፤ ከትምባሆ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ፍላጎት በበለጠ የምንኖርባት መሬት አስፈላጊ እንደሆነች ሊገነዘቡ ይገባልም ብሏል፡፡
ዘገባው የሲኤንኤን ነው

Post a Comment

0 Comments