በአገልጋይ ስም የቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ተደነቀረው እንርሱም እንዳይድኑ ህዝብም እንዳይድን እንቅፋት የሆኑ!

ዲ.ን ሃይለሚካኤል ዘአርሴማ
የአምልኮ መልክ አላቸው ሀይሉን ግን ክደዋል ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈባቸው!
ተቆጭና ገሳጭ አባት ያጡ ቢነግሩአቸውም የተዋህዶን ረቂቅ ስፋት በራሳቸው ጠባብ አዕምሮ ልክ ሰፍተው እነርሱ ያልደረሱበትን የተጋድሎና የቅድስና ህይወት በሌሎችም የክርስቶስና የድንግል ማርያም ፍቅር በበዛላቸው አገልጋዮች ጨርሶ ይሆናል ብለው የማይቀበሉ ትዕቢተኞች!
#ማህበረ #ቅዱሳን በሚባለው ማህበር ውስጥ ተሰግስገው እውነትን አብዝተው የሚቃወሙና የሚገፉ ቅናተኞችና ጠማሞች ናቸው!
እንደ አለመታደል ሆኖ ጻድቃንን ለማሳደድና ለማስጨነቅ ለግብር አባታቸው ለዲያብሎስ ከአህዛብና ከመናፍቃን በላይ የሚሰሩለት የዲያብሎስ የግብር ልጆች ሆነዋል!😭
በጸጋቸው ቀርቶ በእድሜ እንኳን የሚበልጧቸውን የተዋህዶ አባቶች ርዕሰ ባህታውያን አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያምና በመምህር ግርማን ምንም አይነት የሐይማኖት ሕጸጽ ሳያገኙባቸው እንዳሁ በቅናትና በጠማማነት በመቆም ብቻ ወንድምና እኅቶቻቸውን ስለፈወሱ ሰላምን ፍቅርን አንድነትን ስለሰበኩ በከንቱ ይጠሏቸዋል!😭😭😭
ባላወቁት መጠን አባ ዮሐንስንና መምህር ግርማን ይጠሏቸዋል!የጠፋው ልጅ ከጠፋበት ድኖ ወደ ልቡ ተመልሶ ወደ አባቱ ቤት በመመለሱ በወንድሙ ላይ በቅናት እንደተብሰከሰው ልጅ፤ እንዲሁም 38 አመት አልጋው ላይ ተጣብቆ የነበረው ሰው አልጋውን ተሸክሞ በመሄዱ መዳኑ ሳይሆን በሰንበት መዳኑ እንዳንገበገባቸው ጸሀፍትና ፈሪሳውያን እነዚህም ከኢትዮጵያና ከብዙ አለም የመጡ ሰዎች በአባ ዮሐንስና በመምህር ግርማ በመዳናቸው ከመደሰት ይልቅ የመዳናቸው ምክንያት የሆኑትን አባቶችና የተባረከውን ውሀ(ጸበል) በሟንቋሸሽና በመንቀፍ ቅናትና ጥላቻ ያንገበግባቸዋል። ሉቃ 15፤ ዮሐ 5

ራሳቸውን በራሳቸው ከሲኖዶስና ከአረጋውያን አባቶች በላይ ሾመው ገዳም የመሰረቱ፤ ህሙማንን የፈወሱ፤ አጋንንትን ያስወጡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ በአመጻዋና በክህደቷ እንዳትጠፋ የቀደሙ አባቶቻችንና ቅዱሳንን ቃልኪዳን አስቦ ጥቂት ለዘር ያስቀርልን የእምነት ጀግኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ሰርቶ ማሳያ የሕይወት ምስክሮች የሆኑትን አባቶችን አብዝተው በማሳደድ የተጠመዱ የጥፋት ልጆች ሆነዋል!

ከአንድ ሰአት በላይ ተዘፍዝፈው እንደ መንደር አሮጊት የአባቶችን ስጋ በሀሜት የሚቦጭቁ ናቸው!! ወዮ መከራችሁ😭 በቶሎ ንስሀ ግቡ!!!
ጥላቻቸውና ሀሜታቸውና ማሳደዳቸው በነዚህ ሀሳቦች ዙሪያ ነው:-
* ምዕመናን ለምን በካህናት አባቶቻችን ስልጣነ ክህነትና ሀብተ ፈውስ ይፈወሳሉ? ወይም ሰው በካህናት እጅ መዳን የለበትም የሚሉ!
* አባ ዮሐንስ ተስፋ ማርያም ለምን አምስት ገዳማትን መሰረቱ? እንዴት ከዚህ ቀደም የነበሩ ቅዱሳን አባቶችን በሕይወት ሊመስሏቸው ቻሉ? እናም እርሳቸውም መወገድ ገዳሙም መፍረስ አለበት የሚሉ
አባ ዮሐንስ ተስፋማርያም ለምን በስዕለ አድኅኖአቸው ፈወሱም ይላሉ?
ለመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ ብጣቂ ጨርቅ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ሙት አስነስቶ የለምን ወይስ እነርሱስ የያዙት የሐዋርያት ስልጣነ ክህነት አይደለም ወይ! ብዙ ኃጥያት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች ተብሎ ተጽፎ የለም ወይ? ስለዚህ በዚህ አለሙ ሁሉ በክህደትና በአመጽ በጠፋበት ዘመን የእግዚአብሔር ጸጋ እድሜ ዘመናቸውን ራሳቸውን ክደው ከ40 አመታት በላይ በርሀ ኖረው እርሱን ለማገልገል ለታመኑት ለአባ ዮሐንስ ተስፋማርያም ለመላከ መንክራት መምህር ግርማ ለሌሎችም እውነተኛ አባቶች ጸጋ ቢበዛላቸው ለምን ትቀናላችሁ? እግዚአብሔር እኮ ጸጋና በረከት አያልቅበትም ለለመነው ሁሉ ይሰጣል ለምን በጸሎት ተንበርክካችሁ አትጠይቁም???
በመጨረሻም እነዚህ ልባቸው የታወረና የደነደነ የአውሬው አገልጋዮች ወደ ልባቸው እንዲመለሱ ደጋግ አባቶቻችንም ስለ ስሙ መነግላታታቸው መገፋታቸው ቃልኪዳን ክብራቸውን ቢያበዛውም መከራውን እንዲያስታግስላቸው፤ መልካም ለሰሩበት ስድብና ጥላቻ ሳይሆን ምስጋና የሚቀርብላቸው ዘመን እንዲመጣ፤ አጽራረ ቤተክርስቲያንን አጽራረ ሀይማኖትን እንዲያስታግስልን፤ እነዚህንና መሰል በጥፋት መንገድ የሚሄዱ ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ ልቦና እንዲሰጥልን ሁላችንም በያለንበት አንድ አቡነዘበሰማያት አባታችን ሆይ እንጸልይ!

Post a Comment

0 Comments