በወንዶች የሚወሰድ የወሊድ መከላከያ እንክብል አገልግሎት ላይ ለማዋል የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁንና በጤና ላይ የሚያስከትለዉ እክል አለመኖሩን የዘርፉ ተመራማሪዎችን ጠቅሶ ቢቢሲ በድህረ ገፁ አስነብቧል፡፡
በቀን አንድ ጊዜ የሚወሰደዉ ይህ እንክብል የወንድ የዘር ፍሬ እንዳይመረት ከሚያደርጉ ሆርሞኖች የተቀየጠ መሆኑን ዘገባዉ አካተቷል፡፡
ይህ የወሊድ መከላከያ በስራ ላይ በሚዉልበት ጊዜ ወንዶች ይጠቀሟቸዉ ከነበሩት ሁለት አማራጮች ማለትም ከኮንዶምንና በቀዶ ጥገና ከሚከናወን የእርግዝና የመከላከያ ዘዴ ተጨማሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ተጠቅሷል፡፡
ይሁን እጅ ይህንን የወንዶች ክኒን አገልግሎት ላይ ለማዋል ከአስር አመታት ያላነሱ ግዜያትሊወስድ ይችላል ሲሉ ኢንዶክራይን ሶሳይቲ በተሰኘ አለማቀፍ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የዘርፉ ሀኪሞች እንደተናገሩ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡
የሴቶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ከአምሳ አመታት በፊት ጥቅም ላይ ከዋለበት ጊዜ አንስቶ በወንዶች የሚወሰድ የወሊድ መከላከያ እንክብል አለመኖሩ ብዙ ሲያነጋግር መቆየቱን የጠቀሰዉ ዘገባ ጉዳዩን ከፆታ እኩልነትና መብት አንፃር የሚመለከቱት አንዳሉ ይጠቅሳል፡፡

0 Comments