በዮሴፍ ከፈለኝ/ በሸገር ታይምስ የታታመ
የሃገራችን ህዝብ አትሌቲክስና እግርኳስን ይወዳል…በተለይ ለኳሱ ያለው ፍቅር ለጉድ ነው…. ነገር ግን ውጤታማ
አልሆነበትም….ያም ሆኖ ለእግርኳስ ያለው ፍቅር ለመረዳት በ2005 ለደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ ዋንጫ ዋሊያዎቹ ባለፉ
ጊዜ የነበረው እውነት በቂ ምስክር ነው… ይሄ ኳስ ወዳድ ህዝብ በዚህ ስፖርት መደሰት ቢፈልግም ኳሱ ላይ
የተደቀነው አደጋ ብዙ ማሰብ የሚያስፈልገው፣ መተባበር፣ መስማማት፣ ድርጊቱን ለመጸየፍ ዝግጁ መሆንን…. በማይናወጥ
ዕምነት አምላክ ላይ መታመን….የመሳሰሉት ድርጊታዊ ምላሾችን ይሻል..በሁለት ቢላ መብላት መንፈሳዊው አለም ላይ
እንደማያወጣ ማመን የግድም ይላል….እንዳለመታደል ሆኖ እግር ኳስ ከአትሌቲክስ ምንም የወሰደው ውጤታማ የሚያደርግ
ዘዴ የለም ምናልባት አትሌቲክሱ ከአመታት በፊት ለአመራሮቹ አበል ሲጨምር በቅርቡ ደግሞ እግርኳሱ ይህን መኮረጁ
ካልሆነ በቀር የሚኮራረጁት መልካም ድርጊት አልነበረም ….ለእግርኳሱ አደጋ የሆነው ድርጊት ሲታይና ሲሰማ የነበረው
በአትሌቲክሱ መንደር ነበር….አሁን ደግሞ ኳሳችን ላይ ውስጥ ለውስጥ እየተስፋፋ ይገኛል ….ምንድነው ካላችሁ የሸገር
ታይምሱ ዮሴፍ ከፈለኝ እንዲህ ተመልክቶታል…
እያንጓለለ በአትሌቲክሱ
ይሄ መመኪያ የሆነ ስፖርታችን የተደበላለቀ ስሜት አለው… ባልዋ እኔ
አለሁልሽ ሩጫውን ተይው ብሏት ሙያዋን ቀይራ ኑሮዋን የምትገፋ አንዲት አትሌትን የማናገር ዕድል
አጋጥሞኛል…..ስትናገር እንባዋ አይኗ ላይ ግጥም ይላል… “የምወደውን ስፖርት ለምን እንደተውኩት በመረጃ ማሳየት
አልችልም ነገር ግን አብዛኞቹ አሰልጣኞች የኔን ታሪክ ያውቃሉ ግን ምን ብለው ይመስክሩ…..?” አትሌቷ ውድድሩን
መርታ 50 ሜትር ሲቀራት ትወድቃለች ….ደርባቸው የነበሩ አትሌቶች ደርሰው ያልፏታል…ይህ ሲሆን አቅም ባጣ መንፈስ
ደጋግማ አይታለች…..“ልምምድ ላይ ስንገናኝ አርፈሽ ካልተቀመጥሽ ትሞቻለሽ ይሉኛል ምንም ባለማድረጌ ግን
አዝናለሁ…በዚህ መሰል ተንኮል የሚወዱትን ሩጫ የተዉ በርካቶች ናቸው” ትላለች፡፡
“ልምምድ ልሰራ ያወለኩትን ጡት
መያዣ እና ፓንቴን ከቆለፍኩበት ሳጥን ውስጥ ደጋግሜ አጥቼዋለው በቀጣዩ ቀን ግን ሁለት ፓንትና ጡት መያዣ አገኘሁ ይህን ያህል
ይከታተሉኝ ነበር” ብላለች፡፡ “በእነ ሃይሌ ገብረ ስላሴ፣ደራርቱ ቱሉ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ አሰፋ መዝገቡና ጥቂት አትሌቶች
ጋር የነበረው መዋደድና መቀባበል አሁን አትጠብቅ” ሲል የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው አትሌት ተናግሯል፡፡ “አሁን ያለውን ለውጥ ስታይ ታዝናለህ በደምብ የሚጨባበጥ
የሚስማማ ጓደኛዬ የሚባባል አትሌት ካገኘህ እገረማለው” ሲል የችግሩን
ስጋት ያስቀምጣል…..የዚህ አስደንጋጭ በሽታና ወረርሽኝ ተረኛ ተጠቂ
የሚመስለው እግርኳሱ መሆኑ ደግሞ የህዝቡ ደስታ ላይ ውሃ መቸለስ ይሆናል የሚሉ እግርኳሰኞች መፍትሄ ይፈለግ እያሉ ነው…..
እያንጓለለ በእግርኳሱ
ይህን
እውነት ይፋ ሳደርግ የሃገሬን እግርኳስ ለማዳን የተጫዋቾችን ዝምታና ፍርሃት በመስበር እንዲጋፈጡ እንደማደርግ ተስፋ አደርጋለሁ…..ዋናው
ተጎጂ እነሱ ናቸውና….እስቲ ቆም ብለው ያስቡ…..? በቢሊየን ብር አመታዊ በጀት የሚንቀሳቀሰው እግርኳሳችን ካለበት ፈቅ ሳይል
የደላሎችና የኮሚቴዎች እንዲሁም የአሰልጣኞችና ቡድን መሪዎች አካውንትና ኪስ በሚያብጥበት ዘመን ይህ ጉድ ይኖራል ተብሎ ማን ያምናል…..?
ግን እውነት የሆነ ድርጊት ነው …እግርኳሳችን ውስጥ እያንጓለለ ገብቷል ቢባሉ ያምናሉ? አዎ በሳይንሳዊ አጨዋወት አንዱ ከአንዱ
የተሻለ መሆኑ እየቀረ በክፉ መንፈስ ድጋፍ የተሻለ ለመሆን የሚታገሉ ተጨዋቾች እየበዙ ነው ይላል ከሰሞኑ የደረሰኝ መረጃ….. በየመንፈሳዊ
ቦታዎች መሄድ ካበዙ ይህን ግፍ እንደቀልድ ይሰሙታል….. ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ተጨዋች እንዲህ አለኝ “ጸበል ቦታ ሂድ እስቲ…
የማይጮህ ተጨዋችኮ ትንሽ ነው….የተጨዋቾቹ ዕድል፣አዕምሮ ፣አቅም፣ጉልበት…..…በቀላሉ ይወሰዳል…..ገፋ ካለም ህይወቱን ሊያጣ ሁሉ
ይችላል….አሁን አሁን ምርጥ አቋም ማሳየት አስፈሪ ሆኗል….በጓደኛው ዕድል ነግሶ እያስፈራራ የሚጫወት በዝቷል….አንዴ የገጠመኝን ላውራ….የባዕድ
አምልኮው ተጠቂ ማን እንዳደረገበት የማወቅ ዕድል ገጠመውና እባክህ ተወን ሚስቴና ልጄን ላሳድግበት ብሎ ተማጽኖታል…ይህን የማያውቅ
ትንሽ ተጨዋች ነው” ሲል ድርጊቱን አብራርቷል፡፡
ድሮ ድሮ ስለ ህንዶች የምንሰማው አሁን በኛ ሃገር እየታየ ነው ኳሱን ወደ እባብ ይቀይራሉ የተባሉትን እኩይ ድርጊት ሃገራችን ውስጥ ላለማየታችን
ምንም ማረጋገጫ የለም ይላል….ኮከብ እንደሚሆን ተገምቶ በጉዳት ስም አቅሙ በክፉ መንፈስ ተወስዶ ለሌላው ሲሰጥ ማየትን የመሰለ
ህመም ከየት ይገኛል? ጉዳዩ በድብቅ እንደመካሄዱ ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የሚደፍሩ የሉም…መረጃውን ሊነግረኝ ወስኖ ሃሳቡን የቀየረ
ተጎጂ ተጨዋችን ስመለከት ልቤ በጣም አዝኗል ከነዚህ ተጨዋቾችስ ውጤት እንዴትስ መጠበቅ ይቻላል….?…..እስቲ አስቡት በችሎታ ሳይሆን
በባዕድ አምልኮ አቅም ሲጨመር….? “ይህን ያህል ትጎዳለህ ብዬ አይደለም” ተባብለው ይቅርታ የተጠያየቁ ተጨዋቾች እንዳሉም ሰምቻለው…..
በቃ ምን አለፋችሁ ተጨዋቾቹ እያበዱ ነው ማለት ይቻላል…../በራሳቸው የሚተማመኑ ምንም አይነት ድብቅ ድርጊት ውስጥ የሌሉ ተጨዋቾች
እንዳሉ ሳይረሳ ነው/ “አብሮ መብላትና አብሮ መጠጣት እየቀረኮ ነው ጫማህን አውሰኝ ማሊያውን ስጠኝ ተባብሎ መተጋገዝ እየቀረ ነው….በሰላም
መተኛት እየተፈራ ነው… የሚገርመው ሲነቃባቸው በቀላሉ “የሚጎዳህ አልመሰለኝም” በምትል ቧልት ለማለፍ መሞከራቸው ነው… የት ይደርሳሉ
ተብለው መንገድ ላይ የቀሩ፣ በምርጥ ብቃት በከፍተኛ ፊርማ ለቀጣዩ አመት ፈርመው ጉዳት ገጠማቸው በሚል ከመንገዳቸው የተሰናከሉ፣ህልማቸውን
ያጡ፣ በተቃራኒው ደግሞ ከአመት በፊት የትና ለማን ሲጫወቱ እንደነበር
የማይታወቁ ወይም ጎልተው ያልወጡ በአንድ አመት ውስጥ በተሻለ ክፍያ ልዩ ብቃት በማሳየትና ለብሄራዊ ቡድን ሲጠሩና ለረጅም ጊዜ
ሲጫወቱ ድንገት ማየታችን የተለመደ ነው፡፡
በርግጥ ያስገረሙን ሁሉ በባዕድ አምልኮ የተያዙ ናቸው እያልኩ አይደለም ውስጥህ
የሚነግርህ በየአመቱ ጥሩም ሆኑ አልሆኑ ከክለብ ክለብ እንደልባቸው
ሲሽከረከሩ የሚታዩ ነገር ግን የተሻለ ብቃት ያሳያሉ የተባሉ ድንገት ሲቀጩ ማየት ያማል…ያውም ምንም አለማድረግን
የመሰለ መጥፎ
ልብ ሰባሪ ምን አለ? ግን የትኛው ተጨዋች ይህን ያጋልጥ? ሁሉም ፍርሃት ውስጥ ናቸው” ሲል ጉዳዩ የዕምነትና
አምላኩ ላይ የመደገፍ
ብቃት እንደሚጠይቅ ይናገራል፡፡ ማን ደፍሮ ይቃወም? ማን ይናገር? ማን ይፋ ያውጣ? ሲል ይጠይቃል…በየዕምነታቸው
ሄደው የዳኑና
ዕውነቱን ያወቁም ቢሆኑ በይቅርታ መንፈስ ስለሚወጡ እነዚህ ክፉ አድራጊዎችን
ማን ያስቁምልን? ሲል ይጠይቃል፡፡ “በተለይ በአሁኑ ወቅት የተጨዋቾች ወርሃዊ ክፍያ ከፍተኛ
መሆኑ ድርጊቱ ቀጣይነት እንደሚኖረው እሰጋለሁ ስጋቴን የሚጨምረው ደካማ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾች ወደዚህ አይነቱ
ዕርኩስ ድርጊት
የመግባት ውሳኔ እንዳይኖራቸው ነው…. በደካማ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ…እንደሚባለው ኳሳችን ወደ መቃብር እንዳይገባ
እንዲሁም በምድርም
ሆነ በሰማይ እንዳንኮነን ሁሉም ሊተባበር ይገባል” ሲልም ጥሪ ያደርጋል…. “በሁለት ቢላ መብላት አቁመን
በየዕምነታችን ለምናምነው ጌታ እንጸልይ” ሲልም ተጨዋቹ ብቸኛ መፍትሄ ይሄ ነው ሲል ይናገራል፡፡
ደግሞ እንደ ተጨዋቾቹ አይሁን
እንጂ በአሰልጣኞቹም መሃል ክፉ ልምምዱ እንዳለ ተነግሮኛል..…ታሞ ለፈውስ ጸበል ሊጠመቅ የሄደ አሰልጣኝ ድርጊቱ በአሰልጣኞቹ መሃል
እንዳለ አረጋግጦልኛል…..ተጨዋቾቹ ልምምድ እየሰሩ አሞት በወደቀ
ተጨዋች አንተ ጠንቋይ ተብሎ የተሰደበ አሰልጣኝ እንዳለ አውግተውኛል….. ምንም ጥያቄ የሌለው በንጹህ የተፈጥሮ አቋም
ያለምንም የውጪ ሃይል ድጋፍ የሚሰሩ አሰልጣኞችና ተጨዋቾች መኖራቸውን መዘንጋት እንደሌለበት ነው………
እኔ የመጀመሪያውን ዕርምጃ በድፍረት ተራምጃለሁ……ተጠቂዎቹና ስጋት ላይ ያሉት ተጨዋቾች ደግሞ ይከተሉኛል ብዬ
ተስፋ አደርጋለው….. ይህ የማይሆን ከሆነና ተጨዋቾቻችን ፍርሃት ሸብቦ ከያዛቸው ግን ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ
አለበለዚያ…….እንደሚባለው ይሆናል……ደፍረው ለሚመጡ በኛ ይቁም ላሉ ለትውልድ አሳቢዎች ግን ሸገር ታይምስ በሯ
ክፍት ነው……ፍትህ ለተጨዋቾቻችን ብያለሁ፡፡

0 Comments