የመምህር ግርማ ወንድሙ በጎ ሥራዎች


እንደሚታወቀው ከ 2008 - 2011 ዓ.ም መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ለወገን 10,918,632 ብር ( አስር ሚልዮን ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ) ብር በመለገስ ሀገራዊ አስተዋጾ አድርገዋል ።
እንደ ቀድሞ እሁድ መጋቢት 29 2011 ዓ.ም በየረር ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ትልልቅ አባቶችና ጳጳሳቶች በሚገኙበት ልዩ የሆነው የወንጌል የፈውስ እና የበረከት ስራ በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ አማካኝነት እና በአለም ላይ ከሚገኙ ከወንጌል ተማሪዎቻቸው ጋር በመሆን ለየት ያለ መንፈሳዊ ጉባኤ እና ለ ወገን የበረከት ስራ ይካሄዳል ።
ከሚከናወኑት የበረከት ስራዎች ውስጥ

1 ለደብረ ከዋክብት ዝቋላ ገዳም ፦ የኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ የሚውል

2 ወላጅ አልባ እንዲሁም ለተጎዱ አረጋውያን እርዳታ < የበረከት ስራ > የሚከናወን ስለሆነ እግዚአብሔር በፈቀደላችሁ መጠን የበረከቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ እናሳስባለን ።
<< ልጆችን በማሳደግ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረለት ልትሆን ይገባል። >> 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፤ 10
ምንጭ፦ Memhir Girma Wondmu Facebook page

Post a Comment

0 Comments