የአይን ማኩላር እርጅና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እድሜአቸው በገፋ ሰዎች ላይ ብቻ ነበር የሚታየው።አሁን ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ30 እስከ 40 አመት የሆኑ ወጣቶች ሁሉ ‘ማኩላር ዲጀኔሬሽን’ የተባለና ወደ አይነ ስውርነት የሚያደርስ ሕመም እየተጠናወታቸው መጥተዋል ይላሉ የሲንጋፖር የአይን ሕክምና ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሊሊ።
ይሄም የሆነበት ማክንያት ብዙ ሰዎች ማታ መብራት ካጠፉ በኋላ ተንቀሳቃሽ ስልክ እየከፈቱ ያያሉ።በጨለማ ውስጥ ወይም ጨለም ባለ አካባቢ የሞባይል ስልክን ለ30 ደቂቃ እንኳን መጠቀም መታረም የማይችል አደጋ ውስጥ የሚከት ነው።
ሕመሙም ካታራክት አይነት ሕመም ማስከተል ብቻ ሳይሆን የአይን ካንሰርም ያስከትላል። ይህ ደግሞ መድሃኒት የሌለው በመሆኑ አይን ሲጠፋ ብቻ ቁጭ ብሎ መመልከት ነው።
ይላሉ ሃኪሙ።ይህን መልዕክት ያስተላለፉት 254 የሚሆኑ የአይን ስፔሻሊት ሃኪሞች አንድ ላይ በመሆን ነው።
ብዙ ሰዎች ማታ አልጋቸው ላይ ሆነው መብራት አጥፍተው ወይም ፈዘዝ ባለ መብራት ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን እንደሚጠቀሙ ስለምናውቅ አደራ፣ አደራ፣ ራሳችሁን ከማይድን ሕመም ጠብቁ ብለዋል።
መልካም ጤንነት!!

0 Comments