ስለ ፉርኖ ዱቄት ያልተነገረን ምስጢር

ኢትያ ኤልያስ


ፉርኖ ዱቄት ጤናማ እንዳልሆነ ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ተጠራጥሮ አያውቅም።
በአጠቃላይ ሲታይ ምግብ ማቀነባበር የንጥረ ነገሮች ይዘቱን እንደሚያበላሸው ግንዛቤ ይኖረናል ብየ አስባለሁ።



1 ደማቅ ሰማያውዊ ጅንስ ሱሪ ማንጫ (bleach) ለምሳሌ በረኪና ውስጥ የባትሪ ሲድ ውስጥ ብትከቱት ምን ይሆናል?

ልብሱ ቀለሙን ከማጣቱ በላይ ጥንካሬውን ያጣና ብስክስክ ይላል። ይህም የሚሆነው ኬሚካላዊ ውህዶች ስለሚፈጠሩ ነው።

የስንዴ ዱቄትም በማንጣት ሂደት ውስጥ አልፎ ነጭ ፉርኖ ዱቄት ለመሆን ሁለት አማራጭ አለው።



1. ተፈጭቶ ለረጅም ጊዜ ማለት ለወራት ሲቀመጥ ቀስ በቀስ ከኦክስጅን ጋር እየተዋሃደ ነጭ ይሆናል፡፡
2. ማንጫ ኬሚካሎችን (bleaching agents) በመጠቀም በ48 ሰዓት ውስጥ ማንጣት ይቻላል።



መቼም ፋብሪካዎች የመጀመሪያውን መንገድ ይጠቀማሉ እንደማትሉኝ አምናሁ፡፡
በማንጫ የተመረተ ስንዴ ዱቄት በተለምዶ ፉርኖ ዱቄት የምንለው ማንጫዎቹ በጣም ጠንካራ ኬሚካሎች ስለሆኑ የላይኛውን የስንዴ ሽፋን bran እና ፋይበር ያለውን እና ሁለተኛውንና የንጥረ ነገሮች መከማቻ የሆነውን germ የሚባለውን ክፍል ከጥቅም ውጭ ያደርጉታል። ይህም አብዛኛውን ፉርኖ ዱቄት endosperm የተባለውን የስንዴ ክፍል በብዛት የያዘ እንዲሆን ያደርገዋል። ቀደም ብለን እንዳየነው ደግሞ endosperm በብዛት (83%) ስታርች (starch) የተባለ የእፅዋት ካርቦሃይድሬት የያዘ ክፍል ነው። ይህም ዱቄቱ የተመጣጠነ የንጥረ ነገር ይዘቱና የምግብ ይዘቱን እንዲያጣና በብዛት ስኳር ዓይነት ምግብ እንዲሆን ይሆናል።


በማንጣት ወይም bleaching ሂደት ውስጥ ምን እንደሚጠፋ ተመልከቱ።

👉 ጠቃሚ የሆኑ ቅባቶች ወይም unsaturated fatty acids ሙሉ በሙሉ ይወገዳሉ
👉ቪታሚን ኢ መቶ በመቶ ይወገዳል
👉ካልሲየም ሃምሳ በመቶ
👉ፎስፎረስ ሰባ በመቶ
👉 ብረት ወይም አይረን ሰማንያ በመቶውን
👉 ማግኒዥየም ዘጠና ስምንት በመቶ
👉ከ 50 እስከ 80 ፐርሰንት ከ B ቫይታሚኖች እናም ብዙ ተጨማሪ የምግብ ይዘቶች ይሞታሉ ግን ሁሉንም መዘርዘር ይከብዳል።
ነጩ ዱቄት ታሪኩ በዚህ ቢያበቃ መልካም ነበር።


እንዴት እንደሚሠራ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?


ገና ወደ ዱቄቱ ሳንመጣ አብዛኞቹ የንግዱ ስንዴ ምርቶች በሚያሳዝን ሁኔታ "ፀረ-ተባይ መድሃኒት" በፀረ-ፈንገስ መድሃኒት የተዳከሙ ናቸው። ስንዴው ከደረሰ በኋላም በሆርሞንና ፀረ ተባይ መድሃኒቶች ይረጫሉ።

ይህ ገና ከጅምሩ የስንዴነቱን ባህሪ ያጣው እህል በሚያሳዝን ሁኔታ በኃይለኛ ኬሚካሎች በማንጣት ሂደት ውስጥ ያልፋል። የቀሩት ንጥረ ነገሮች በሌላ የኬሚካል መገደል ሂደት ውስጥ ያልፋሉ ብላችሁ መውሰድ ትችላላችሁ።

ክሎሪን ጋዝ (ክሎሪን ኦክሳይድ) እንደ ማንጫነት ያገለግላል. ይህ ጋዝ ማለት በትንፋሽ ወደ ውስጥ ቢገባ ገዳይና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ጅምላ ጨራሽ ጋዝ የተፈረጀ ነው። እንግዲህ አስቡት በዚህ ጋዝ የተዋሃደ እህል ምን ጠቃሚ ንጥረ ነገር እንደሚቀረው።

ሌሎች ጥቅም ላይ ከሚውሉ ኬሚካሎች ውስጥ የናይትሮጅን፣ናይትሮሲል እና ቤንዞይል ፖርኦክሳይድ ከተለያዩ የኬሚካል ጨዎች ጋር ይቀላቀላሉ።

የሚያሳዝነው ግን እህሉ ጥቅሙን ማጣቱ አይደለም ለጥቅም አልባ እህል ብለን ለመርዛማ ኬሚካል መጋለጣችን እንጂ!

እንዴት?

ክሎሪን ጋዝ ኦክሳይድ ለማንጣት ኦክሲዴሽን የሚባል reaction ከተወሰኑ የስንዴው ፕሮቲኖች ጋር ሲያካሄድ Alloxan (አሎግዛን) የተባለ ኬሚካል እንደ ተረፈ ውሃድ ይፈጠራል።

ፋብሪካዎቹን ብትጠይቁ ምንም ተረፈ ምርት የለውም

Post a Comment

0 Comments