ጉድፍ አምስት፡-
ምዕራፍ አንድ፡-
በዚህ ምዕራፍ ፋኢዝ ቢያንስ
ሦስት ጉዳዮችን ያነሣል
1. "ሙስሊም-ጠልነት"ን
ይተረጉማል
2. ለሙስሊም-ጠልነት አስተዋጽኦ
ያደረጉ አመለካከቶችና መንስኤዎቻቸውን ይዘረዝራል
3. የሙስሊም-ጠልነት መዘዙንና
የመፍትሔ ሐሳብ የተባሉትንም ያመላክታል
ፋኢዝ ሙስሊም-ጠልነትን
እንዲህ ይተረጉመዋል፡-
"ሙስሊሞችን ወይም
የእስልምና ሃይማኖትን አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መሥጋት)፣ መጥላት እና መጥፎ አመለካከትን በውስጥ
መሰነቅ"
ሙስሊም-ጠልነት ማለት ይህ
ከሆነ በትርጉሙ ውስጥ ሦስት ነጥቦች በግልጽ ይታያሉ፡-
• አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መስጋት)
• መጥላት
• መጥፎ አመለካከትን በውስጥ መሰነቅ የሚሉ ናቸው
ታዲያ በምን ሒሳብ ይሆን
ሙስሊም ጠልነት ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ለማለት የተሞከረው? በትርጉሙ ውስጥ ጠልነት አለመኖሩን ለማየት እንዴት አልቻለም? ለማንኛውም
ወንድሜን እኔው ልርዳው፡፡ ከመጀመሪያው ነጥብ እንጀምር፡፡
❖ አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ)
ምክንያት መፍራት (መሥጋት)
በኢትዮጵያችን እስልምና
ሥጋት የሚሆንባቸው ከቁጥር ያለፉ "አሳማኝ ምክንያቶች" ስላሉን (ሙስሊሞችን ወይም የእስልምና ሃይማኖትን አሳማኝ
ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መሥጋት))ሙስሊም-ጠልነት በአገራችን የለም እላለሁ፡፡ እስልምና ለየትኛውም ማኅበረሰብ
"አሥጊ" "ሥጋት" እንደሆነ ከበቂ በላይ የሚጨበጡና የሚዳሰሱ አሳማኝ ማስረጃዎች ለመኖራቸው ራሱ
ፋኢዝ ሊመሰክር ይችላል፡፡ እስልምና ሥጋት እንደሆነ ወይም "ሊሠጋ" የሚገባው እንደሆነ (ሊፈራ የሚለውን ልተወው)
የሚያሳብቁ ማስረጃዎች አንድ ብለው የሚጀምሩት ለሙስሊሞች የማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የሃይማኖታዊ፣ ወዘተ… አስተሳሰብ
ምንጭ ከሆነው ከቁርአን ነው፡፡ ለዚህ ምሳሌዎችን ማንሣት ይቻላል፡-
1. ከእርሱ ውጭ ያሉትን እንደ ጠላት የሚቆጥርና ጊዜን ጠብቆ የመበቀል ባሕሪ ስላለው እርሱን መሥጋት አሳማኝ ምክንያት
ነው፤ ስለዚህ ሙስሊም-ጠልነት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም የሚለው እውነት ነው፡-
2. እንደምታስታውሱት የሙስሊምና የክርስቲያን ግንኙነት ምን መምሰል እንደሚገባው አላህና ነቢዩ የተናገሩትን፣ እንዲሁም
ከአላህንና ከነቢዩ ትእዛዝ ላይ በመቆም ሊቃውንቱ የተናገሩትን ቀደም ብለን በመግቢያው ምልከታ ላይ ተመልክተነዋል፤1
ጨምሮም ቁርአን እንዲህ ይላል፡-
ሱረቱል አል-በይናህ
98 ፡ 6
እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች
የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡
እነዚህ አላህ
"ከፍጥረት ሁሉ ክፉ" ያላቸው ወገኖች በሌላ የቁርአን አንቀጽ ለእርሱና ሙስሊሞች ጠላቶች እንደሆኑም ተናግሮ እናነባለን፡-
ሱረቱል አል-ሙምታሃና
60 ፡ 1
እናንተ ያመናችሁ ሆይ!
ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡ ከእውነቱ የመጣላችሁን ሃይማኖት በእርግጥ የካዱ ሲኾኑ ውዴታን ወደእነርሱ
ታደርሳላችሁ፡፡ …2
እናም አላህ ጠላቶቼ ብሎ
የፈረጃቸውን ወገኖች ጊዜ እየጠበቀ ያጠቃና ያስጠቃ እንደ ነበር ቁርአንና የነቢዩ ግለ ታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ፡-
ሱረቱል አል-በቀራ 2 ፡
109
ከመጽሐፉ ባለቤቶች ብዙዎች
እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በኾነው ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ሊመልሱዋችሁ ተመኙ፡፡ አላህም
ትዕዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ይቅርታ አድርጉ፤ እለፏቸውም፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ ነውና፡፡3
እነዚህ የተጠቀሱ የቁርአን
አንቀጾች 'የአምላክ ቃል' ከሆኑ በየትኛውም የዓለም ጥግ የሚኖር ከኢስላም ውጭ ያለ ሰው ሁሉ ሙስሊሞችንና ኢስላምን ለመሥጋት በቂ
ከበቂም በላይ ምክንያት አለው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም ጠልነት የለም፡፡
2. ክርስቲያኖችና አይሁዶች
በአላህና በነቢዩ ሙሐመድ ካፊር እና ሙሽሪክ መባላቸው በራሱ እስልምናን ለመሥጋት አሳማኝ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም-ጠልነት
ኢትዮጵያ ውስጥ የለም
ሱረቱል አል-ተውባ 9 ፡
30-31
አይሁድ ዑዘይር የአላህ
ልጅ ነው አለች፡፡ ክርስቲያኖችም አልመሲሕ የአላህ ልጅ ነው አሉ፡፡ ይህ በአፎቻቸው (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ
በፊት የካዱትን ( كَفَرُو ا ) ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡ አላህ ያጥፋቸው (4
قَاتَ لَهُ مُ )፡፡ (ከእውነት) እንዴት ይመለሳሉ! ከእርሱ በቀር ሌላ
አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ
ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ( يُشْرِكُونَ ) ሁሉ የጠራ ነው፡፡
የእስልምና ሊቃውንቱም ይህንን
የቁርአን አንቀጽ መሠረት አድርገው በፈትዋቸው እንዲህ ብለዋል፡-
Majmoo’
Fataawa al-Shaykh Ibn Baaz, 4/274
The Jews and
Christians are both kaafirs and mushrikeen. They are kaafirs because they deny
the truth and reject it. And they are mushrikeen because they worship someone
other than Allaah.
እናም አላህና ነቢዩ ሙሐመድ
እነዚህን ካፊርና ሙሽሪክ የሆኑትን እስልምናን እስካልተቀበሉ ድረስ እንዲገድሉ ሙስሊሞች ታዝዘዋል፡፡ እማኝ የሚሆኑኝ የቁርአን አንቀጾች
የትየለሌ ቢሆኑም እነሆ አንዱን፡-
ሱረቱል አት-ተውባ 9 ፡
5
የተከበሩትም ወሮች ባለቁ
ጊዜ አጋሪዎቹን ( الْمُشْرِكِيَ ) በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው (فَاقْ تُ لُواُ )፡፡ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣
ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
በሁሉም ሙስሊም ሰባኪያን
ልምድ እንደሆነው ፋኢዝም ሱራ 9 ፡ 5ን በመሸምጠጥ የማምለጫዋን የሱራ 9 ፡ 29 ን ካርድ ሊመዝ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ
ነው፡፡ ይህ የቁርአን አንቀጽ 'የዚማ' አንቀጽ ተብሎ ይታወቃል፡-
"ከእነዚያ መጽሐፍን
ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን፣ አላህና መልክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውነተኛውንም
ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን (الِْْزْيَةَُ
) በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው ( قَاتِلُو 8_<*______ا )፡፡"
'ዚማ' በሙስሊም ማኅበረሰብ
መካከል ወይም በኢስላማዊ መንግሥት አገር የሚኖሩ ክርስቲያኖችና አይሁዶች መጠሪያ ነው፡፡ ክርስቲያኖችና አይሁዶች በኢስላማዊ አገር
ሲኖሩ (ዜጋውንም ይጨምራል) ግብር (ጅዚያ) በውርደት መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ አስ-ሲዩጢ "የተዋረዱ ሆነው" የሚለውን
ሲያብራሩ እንዲህ ነበር ያሉት፡-
(state of abasement)
(صَاغِرُونَُ ) Ibn 'Abbas said: they
are pushed. Ibn Abi Hatim transmitted that. It is transmitted that al-Mughira
told Rustam, "I call you to Islam or else you must pay the jizya while you
are in a state of abasement." He said, "I know what jizya means, but
what does 'a state of abasement' mean?" He replied, "You pay it while
you are standing and I am sitting and the whip hanging is over your head."
Abu'sh-Shaykh related that Sa'id ibn al-Musayyab said, "I prefer that the
people of the dhimma become tired by paying the jizya since He says, 'until
they pay the jizya with their own hands in a state of complete
abasement.'" It is used as a proof by those who say that it is taken in a
humiliating way, and so the taker sits and the dhimmi stands with his head
bowed and his back bent. The jizya is placed in the balance and the taker
seizes his beard and hits his chin.
ምን ይህ ብቻ ከሊፋ ኡመር
ለዚማዎች እንዲህ የሚል የውል ስምምነት አዘጋጅቶ ያስፈርም እንደነበር የነቢዩ ሐዲሳትና የተለያዩ የቁርአን ተንታኞች እንዲህ ተናግረዋል፡-5
The scholars
of Hadith narrated from `Abdur-Rahman bin Ghanm Al-Ash`ari that he said,
"I recorded for `Umar bin Al-Khattab, may Allah be pleased with him, the
terms of the treaty of peace he conducted with the Christians of Ash-Sham: `In
the Name of Allah, Most Gracious, Most Merciful. This is a document to the
servant of Allah `Umar, the Leader of the faithful, from the Christians of such
and such city. (ሰሪያ ላይ በነበረች ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ የሚቆም አልነበረም) When you (Muslims)
came to us we requested safety for ourselves, children, property and followers
of our religion. We made a condition on ourselves that we will neither erect in
our areas a monastery, church, or a sanctuary for a monk, nor restore any place
of worship that needs restoration nor use any of them for the purpose of enmity
against Muslims. We will not prevent any Muslim from resting in our churches
whether they come by day or night, and we will open the doors of our houses of
worship for the wayfarer and passerby. Those Muslims who come as guests, will
enjoy boarding and food for three days. We will not allow a spy against Muslims
into our churches and homes or hide deceit or betrayal against Muslims. We will
not teach our children the Qur'an, publicize practices of Shirk, invite anyone
to Shirk or prevent any of our fellows from embracing Islam, if they choose to
do so. We will respect Muslims; move from the places we sit in if they choose
to sit in them. We will not imitate their clothing, caps, turbans, sandals,
hairstyles, speech, nicknames and title names, or ride on saddles, hang swords
on the shoulders, collect weapons of any kind or carry these weapons. We will
not encrypt our stamps in Arabic, or sell liquor. We will have the front of our
hair cut, wear our customary clothes wherever we are, wear belts around our
waist, refrain from erecting crosses on the outside of our churches and
demonstrating them and our books in public in Muslim fairways and markets. We
will not sound the bells in our churches, except discretely, or raise our
voices while reciting our holy books inside our churches in the presence of
Muslims, nor raise our voices with prayer at our funerals, or light torches in
funeral processions in the fairways of Muslims, or their markets. We will not
bury our dead next to Muslim dead, or buy servants who were captured by Muslims.
We will be guides for Muslims and refrain from breaching their privacy in their
homes.' When I gave this document to `Umar, he added to it, `We will not beat
any Muslim. These are the conditions that we set against ourselves and
followers of our religion in return for safety and protection. If we break any
of these promises that we set for your benefit against ourselves, then our
Dhimmah (promise of protection) is broken and you are allowed to do with us
what you are allowed of people of defiance and rebellion.'''6
ስለ እግዚአብሔርም ሰላምታም
ቢሆን ነቢዩ እንዲህ ሲሉም ሙስሊሞችን አዝዘዋል፡-
Do not
initiate the Salam to the Jews and Christians, and if you meet any of them in a
road, force them to its narrowest alley. (Sahih Muslim 4 : 1707, Sahih Bukhari
Book 25, Number 5389) This is why the Leader of the faithful `Umar bin
Al-Khattab, may Allah be pleased with him, demanded his well-known conditions
be met by the Christians, these conditions that ensured their continued
humiliation, degradation and disgrace.
ይህንን የመሰለ የሰዎችን
ሁለንተና ገፋፊ ሥርዐት አይታችሁ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ኢስላም ብቸኛው ነው፡፡ ታዲያ ይህንን የሰዎችን ሰብአዊ መብት ገፋፊና በአምላክ
ስም ወደ ጥልቅ ባርነት የሚወስድ ሃይማኖት መሥጋት ምክንያታዊነት አይደለምን? እንዴታ! ምክኒያታዊነት ነው እንጂ ወዳጄ!! ስለዚህ
ሙስሊም-ጠልነት (አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መሥጋት)) ኢትዮጵያ ውስጥ የለም እልሀለሁ፡፡
3. ኢትዮጵያ ከኸሊፋ ኡመር
ዘመን ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ ኢስላም ያደረሰባትና እያደረሰባት ያለው ሰቆቃ ኢስላምን ለመሥጋት ምክኒያታዊነት ነው፡፡ ስለሆነም
ሙስሊም-ጠልነት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳልነበርና አሁንም ላለመኖሩ ተጨባጭ ማሳያ ነው፡፡
ባለፉት ዘመናት የደረሱት
ሰቆቃዎች ስለሚታወቁ አንድ ሁለት እያሉ መዘርዘር አስፈላጊ አይደለም፡፡ እንደ ፋኢዝ መሆን ነው፡፡ በሙስሊሙም በክርስቲያኑም ዘንድ
የሚታወቁም ናቸው፤ የዘመናችን ሙስሊም ጸሓፊያን ሌላ ስም እየሰጧቸው ቢሆንም፤ ከኢስላም ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ያንን ሁሉ የሰቆቃ
ዶፍ ሳይቆጥር ወንድሜ እያለ በአብሮነት እየኖረ ባለበት
በዚህ ጊዜ አሁን ላይ ያንን
ዘግናኝ ሰቆቃ ለመድገም ያቆበቆበ ደም የጠማው ኢስላማዊ ትውልድ፣ የአህመድ ግራኝ ትውልድ፣ ቤተ ክርስቲያን አቃጣይ፣ ንብረት ዘራፊ
ትውልድ እየተመለከትን ነው፡፡7 በምድረ አሜሪካ የሚኖር ኢትዮጲያን
እንደ ሶሪያ የማድረግ እቅድ ያለውን ትውልድ መግለጫ የምንረሳው አይደለም፡፡ ሐጅ ነጅብ በቢቢኤን ሬዲዮ በኩል ሐሳቡን በተወሰነ
ደረጃ ተቃውመው የሰጡትን መግለጫ ያደመጠ ሁሉ አይረሳውም፡፡ ሁለት ዓመት አለፈው ልበል? ታዲያ ከሌሎች ስጋቶች ይልቅ ኢስላም ሥጋት
የማይሆንበት ከኢስላም ውጭ ያለ ኢትዮጵያዊ ማን ነው? ይህስ ሥጋቱን ምክኒያታዊ አያደርገውምን? ለማንኛውም ሙስሊም-ጠልነት
_______ኢትዮጵያ ውስጥ ያለመኖሩ ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡
"አሳማኝ ባልሆነ
(ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መስጋት)" ስለ ሚለው የሙስሊም-ጠልነት ትርጉም የአንድን ሰው ጽሑፍ ላስነብባችሁና
ወደ ሁለተኛው ልሻገር፡፡ ጽሑፉ በምዕራቡ ዓለም ሙስሊም-ጠል አመለካከት እንዲጎለብት አድርገዋል ተብለው ከተዘረዘሩት አንዱ የሆኑት
የዳግላስ ሙሬይ ነው፡፡8 "Islam-ophilia" ከተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ
ነው ያገኘሁት፤ ለፋኢዝና ለመሰሎቹ በምዕራቡም ይሁን በሌላው ዓለም ሙስሊም-ጠልነት (አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት
መፍራት (መሥጋት)) ላለመኖሩ ጥሩ ማሳያ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡-
"The word
is applied to anything which could be deemed offensive to any Muslim, anytime,
any place, anywhere. Personally, I think the word is a crock – for a lot of
reasons, but not least among them that a ‘phobia’ is an irrational fear. There
is nothing ‘irrational’ about fearing parts – though certainly not all – of
Islam.
For example,
it would be rational to be ‘phobic’ of the 7/7 bombers and the 9/11 hijackers.
It is rational to be ‘phobic’ about Islam if you are a Dutch film-maker, or an
American ambassador in Benghazi or, as we now know, a soldier in south London.
The perpetrators were all people who acted in the name of Islam. They may have
been right in believing this, or they may have been wrong. But being ‘phobic’
of such things is a perfectly rational instinct – indeed, one might call it a
survival instinct.9
❖ ሁለተኛው የትርጉም ሐሳብ
"መጥላት" የሚለው ነው፡፡
በመንደርደሪያዬ ላይ ጥላቻን
በተመለከተ የተወሰነ ብያለሁ፡፡ አሁንም ልድገመው ሙስሊሞችን መጥላት አለ ብሎ ማለት አባይነት ነው፡፡ ሙስሊም ግን 'ጠል' አምላክ
ያለው፣ 'ጠል' ነቢይ የሚከተል፣ ለሕይወቱ አጠቃላይ ዘይቤም የ'ጠል' ነቢይ ሕይወት ምሳሌ የሆነለት፣ በመሠረተ እምነቱ እንዲጠላ
የታዘዘና ለመጥላት ቃል የገባ ነው፡፡ በጥላቻ ጢም ብሎ እየኖረ የምጠላው፣ ለእግዚአብሔር ሰላምታም እንኳን ቀድሜ ሰላም የማልለው፣
ወደ ጠባቡ ጭንቅ የምገፋው ለጥላቻዬ እንዴት ጥላቻ ይመለስልኛል ብሎ በምን ሞራል ሊጠይቅ ይችላል? ስለዚህ ሙስሊሙ ኢትዮጵያ ውስጥ
በክርስቲያኑ ይጠላል ተብሎ የሚታመን ከሆነ ጥላቻው ምክኒያታዊ ስለሚሆን ሙስሊም-ጠልነት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም የሚለውን ያረጋግጣል፡፡
7 ለፋኢዝ ይህ የግለሰብ ሙስሊም ተግባር ነው፤ ግለሰብ ክርስቲያን
የሚፈጽመው የቤተ ክርስቲያንና የሰለሞን ሥርዎ መንግሥት ውርስ ይሆናል
❖ ሦስተኛው "መጥፎ አስተሳሰብን
በውስጥ መሰነቅ" የሚለው ነው፡፡
ይህም ቢሆን እብለት ነው፡፡
ለኢስላም መጥፎ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ ከኢስላም ውጭ ያለ ሰው የሚያደርገው ነገር የሚጠቅመው እንኳን ቢሆን ለእርሱ መጥፎ
ነው፡፡ ባህሪው ከማንም አይገጥምም፡፡ ይታወቃል፡፡ እርሱ በጥላቻ የነቀዘ ማንነት ስላለው ሌላው ሁሉ እንደ እርሱ የሚያስብ፣ ተግባሩም
እንደዛው ይመስለዋል፤ አይገርምም! የኢትዮጵያ ክርስቲያን ስለ ሙስሊሞች ያለውን ሐሳብ በዕውቀትም ሆነ ያለ ዕውቀት ይግለጥ የሚያስበው
በጎ ነው፡፡ የተፈጸመበትን ክፉ ነገር ለመርሳትና አብሮነትን ለማስቀጠል ቅርብ ልብ አለው፡፡ ለዛውም እስከ መንግሥተ ሰማይ፡፡
ምድር ላይ ያለው እውነት
ይህ ሆኖ እያለ በኢትዮጵያ ባለው ክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ ሙስሊሙን በተመለከተ መጥፎ አስተሳሰብ ተሰንቋል ተብሎ የሚታመን ከሆነ
ቀደም ብለን ካየናቸው ዝርዝር ማስረጃዎች የተነሣ ምክኒያታዊ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሙስሊም-ጠልነት በምድራችን ፈጽሞ የለም የሚለውን
እርግጥ ያደርገዋል፡፡
በዚህ በምዕራፍ አንድ ውስጥ
ካሉት ንኡስ ርዕሶች መካከል ሁለቱ ላይ ምልከታዬን ልቀጥል፡-
1. የምዕራቡ ዓለም የምሁራን ሚና የሚለው ነው
በዚህ ርዕስ ሥር በምዕራቡ
ዓለም ለሙስሊም-ጠልነት መስፋፋት አስተዋጽኦ ካደረጉ አስተሳሰቦች ዋና ዋና የተባሉት ተዘርዝረዋል፡-
• እስልምና አሃዳዊ ባህልን የሚያራምድ ሃይማኖት ተደርጎ መታመኑ
• እስልምና ከሌሎች ሃይማኖቶች አንጻር ፍጹም የተለየ (የተቃረነ) ተደርጎ መገመቱ
• የጥላቻ ሃይማኖት ተደርጎ መለፈፉ
• የጅሃድ ጽንሰ ሐሳብ ከአክራሪነትና ሽብርተኝነት ጋር መያያዙ
• እስልምና በአጠቃላይ ሴቶችን ይጨቁናል ተብሎ መታመኑ፤ በተለይ ሒጃብ ሴቶችን መጨቆኛ መሳሪያ ተደርጎ መታየቱ
• እስልምና ለምዕራቡ ዓለም የማይመጥን ፣ የበታች፣ የኋላ ቀርነትና የፀረ-ስልጣኔ መገለጫ ተደርጎ መታየቱ
• እስልምና በፖለቲካው ረገድ አማራጭ የሌለውና ታጋሽ አይደለም መባሉ ናቸው ሲል ይዘረዝራል
ይህ የእንግሊዝ ሙስሊሞች
ኮሚሽን ረኒሜድ ትረስት ሪፖርት በመባል በሚታወቀው ዘገባው Islamophobia: a challenge for us all በማለት በዳሰሰው
ጥናቱ የዘረዘራቸው እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል "እንደነዚህ አይነቶቹን ለሙስሊሞችና ለሃይማኖታቸው የተዛቡና አሉታዊ
አመለካከትን ሊፈጥሩ የሚችሉትን መንስኤዎች ደግሞ ምሁራን በሦስት ከፍለው ይዘረዝራሉ፡-
1) ቀጥተኛ የሆነ የግንኙነት
ተሞክሮ አለመኖር ወይም ተሞክሮው አሉታዊ ብቻ መሆን
2) ከቤተሰብ፣ ከቅርብ
ዘመድ፣ ከመምህራን፣ ከወዳጅና ከመገናኛ ብዙሃን ስለ ሙስሊሞች (ወይም እስልምና) አሉታዊ መልዕክትን በተደጋጋሚ ሲሰሙ ነው፡፡…
3) ስለ ሙስሊሞችና እስልምና
ያለው ዕውቀት በጣም አነስተኛ ወይም የተዛባ ከሆነ፣ ስለ እስልምና የገነቡት የተሳሳተ እምነት፣ ለሙስሊሞች (እና ለሃይማኖቱ) ያላቸው
አመለካከት አሉታዊ ይሆናል በማለት ይዘረዝራሉ"10 ሲል ጠቅሷል፡፡
ፋኢዝ ሙስሊም-ጠልነት ኢትዮጵያ
ውስጥ እንዳለ ለማሳየት እንደመንደርደሪያ የተጠቀመው የምዕራቡን "ሙስሊም-ጠልነት" የሚሉትን ነው፡፡ እንዲያ ከሆነ
ታዲያ ለጠልነት መንስኤ የተባሉት ነጥቦችና ለጠልነት አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉት ሐሳቦች በምዕራፉ መግቢያ በተሰጠው የጠልነት
ትርጉም መሠረት ሲገመገሙ እውን ያንን ያሳያሉ? ወይስ ተቃራኒውን? ተቃራኒውን ነው የሚያሳዩት በኢትዮጵያ ጠልነት እንደሌለ ሁሉ
በምዕራቡም ዓለም ቢሆን ጠልነት እንደሌለ በራሳቸው ትርጉም እያረጋገጡልን ይገኛሉ፡፡
የመጀመሪያው ለሙስሊም-ጠልነት
አስተዋጽኦ አደረጉ የተባሉትን አስተሳሰቦች ስንመለከት "እስልምና በፖለቲካው ረገድ አማራጭ የሌለው" ከሚለው በስተቀር
ሁሉም የኢስላም መገለጫዎች መሆናቸውን ማንም የሚክደው አይደለም፤ እውነት ናቸው፡፡ ኢስላምን በማወቅ ላይ የተገነቡ አስተሳሰቦች
ናቸው፡፡ በስተመጨረሻ በሰፊው የምገልጸው ቢሆንም በፖለቲካውም ረገድ የተለየ አማራጭ ያለው የፖለቲካ ተቋም እንደሆነ ሊቃውንቱ በሰፊው
የሚናገሩት ነው፡፡11 ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ኢስላማዊ መጽሐፍትም ወደ አማርኛችን
እየተተረጎሙ (በተለይ በአምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ) ከተሰራጩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ እንግዲህ እነዚህ አስተሳሰቦች ኢስላምን
ከገለጡትና ባሕሪዎቹ ከሆኑ "ስጋቱን" ምክንያታዊ ያደርጉታል ማለት ነው፡፡ ዳግላስ ሙሬይ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡12
ስለዚህ ምዕራቡ ዓለም ውስጥ "ሙስሊም-ጠልነት (አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት
መፍራት (መሥጋት)፣ መጥላት እና መጥፎ አመለካከትን በውስጥ መሰነቅ)" አለ ብሎ መናገር እብለት ነው፡፡ የፋኢዝን ዐላማ
ወደ ግቡ ለማድረስ ወደ ኢትዮጵያችን የሚያንደረድረው ድልድይ ሰባራ ነው ማለት ነው፡፡
ሁለተኛ መንስኤዎቹም ቢሆኑ
በበርካታ ምክንያቶች ለሙስሊም-ጠልነት በምዕራቡ ዓለም እንደ መንስኤ ሊጠቀሱ የሚገባቸው አይደሉም፡፡ ለምሳሌ የመጀመሪያውን ሁለቱን
ለጊዜው አቆይተናቸው ሦስተኛውን ማየት እንችላለን፡-
❖ ለጠልነት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ የተባሉት
አስተሳሰቦች የኢስላም መገለጫዎች መሆናቸው ምዕራቡ ዓለም ላይ በትክክለኛ ዕውቀት ላይ የተመሠረተ መረዳት እንዳለ አመላካች ነው፡፡
❖ በምዕራቡ ዓለም ሙስሊም-ጠልነት ተጀመረ
ተብሎ ከተጠቀሰው ወቅት ብዙ ዓመታት ቀድመው የኖሩና የኢስላምን ታሪክ፣ የነቢዩ ሙሐመድን ግለ ታሪክ፣ የቁርአንን ታሪክ የጻፉና
አሁን ድረስ በኢስላማዊ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች መጽሐፍቶቻቸው የታወቁ ማስተማሪያ የሆኑላቸው የሳውዲ አረቢያ ኢማሞች ሳይሆኑ ምዕራባውያኑ
ሊቃውንት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ፋኢዝ ይህንን የሚያስተባብል አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ኢስላምን በተመለከተ በምዕራቡ ዓለም ሊቃውንት
ዘንድ የተዛባ ዕውቀት አለ ብሎ ማለት ስህተትነው፡፡ ለኢስላም ስለማይመች መቀበል ሊከብዳቸው ቢችልም፡፡ ስለዚህ መንስኤዎቹ ለምዕራቡ
ዓለም ዕውቀት የሚሠሩ አይደሉም፡፡ ታዲያ "ሙስሊም-ጠልነት (አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መስጋት)፣
መጥላት እና መጥፎ አመለካከትን በውስጥ መሰነቅ)" እንዴት ሊኖር ይችላል? የለም፡፡
2. "መዘዙና የተጠቆሙ
መፍትሔዎች" የሚለው ነው
በዚህ ንኡስ ርዕስ ሥር
የተለያዩ ጸሐፍት ሐሳብ ተጠቅሷል፡፡ የሚኮነኑትም እየተኮነኑ፣ ሙስሊሙ በጠሎች ደረሰበት በሚባለው ላይ ትችታቸውን የሰነዘሩ እየተሞገሱ
ከገጽ 29-43 ይዘልቃል፡፡ በንጽጽር እየተዋዛ ደጋግሞ የሚነሣው በአክራሪነት፣ በሽብርተኝነትና በጽንፈኝነት ስም ሙስሊሙ በጠሎች
መገፋት እየደረሰበት ነው የሚሉ ናቸው፡፡ በሙስሊሞች የተፈጸመ የሽብር ተግባር ከሌሎቹ ጋር በንጽጽር ሲታይ በቁጥር አናሳ ነው፤
ነገር ግን የሌሎቹ ሳይወሳ ከ9/11 በኋላ በስፋት በሚዲያዎች የሚላመጠው የሙስሊሞቹ ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ ለጠልነቱ ታላቅ ግብአት
ሆኗል፡፡ ይህ ወደ ፊት የሚያስከትለው መዘዝ ደግሞ በአጭሩ የማያባራ ጠላትነትን ይሆናል የሚል ማሳሰቢያ አለው፡፡ የመፍትሔ ሐሳቡ
እስልምናን ያስደስተዋል ወይስ አያስደስተውም የሚለው አነጋጋሪ ስለሆነ ለጊዜው ይቆይና ስለ ሁለቱ እንነጋገር፡፡ ለጠልነቱ መንስኤ
ስለሆነው 'ሽብር'ና 'የማያባራ ጠላትነት' ስለተባለው መዘዙ፡፡
• የማያባራ ጠላትነት፡-
ከእስልምና ውጭ ያሉ የሙስሊም-ጠልነት
ተሟጋቾች "የማያባራ ጠላትነትን" እንደ መዘዝ መጥቀሳቸው ያለ ዕውቀት የሚሉትን እያሉ እንዳሉ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በእስልምና እና ከእስልምና ውጭ ባሉት ዘንድ የማያባራ ጠላትነት ከታወጀ በአላህ ሁሉን ከመፍጠሩ በፊት በመጽሐፍቶች እናት ላይ ከትቦታል
በነቢዩ ሙሐመድ ደግሞ 1440 ዓመታት ዐልፎታል፡፡ ይህንን ቀደም ባሉት ምልከታዎቼ ለማሳየት ሚክሬያለሁ፡፡ ታዲያ አዲስ 'የማያባራ'
የሚባል ያልነበር አዲስ ጠላትነት ከየት ሊመጣ ይችላል? ስለዚህ መዘዝ የሚባል አዲስ ነገር አይመጣም የነበር፣ ያለም ነው፡፡ ጥላቻው
የሚያባራው ከእስልምና ውጭ የሉት ወገኖች እስልምናን ተቀብለው ከሰለሙ ብቻ ይሆናል፡፡13
ሱረቱል አት-ተውባ 9 ፡
5
የተከበሩትም ወሮች ባለቁ
ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው፡፡ ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ ቢጸጸቱም፣
ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
አላህ አንድ ግብ አስቀምጧል፡፡
እርሱ እስከሚሳካ ድረስ፣ የአላህና የሙስሊሞች ጠላቶች እስካሉ ድረስ ጠላትነት አይቆምም፡-
ሱረቱል አል-አንፋል 8
፡ 39
ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም
ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
• ሽብር
ስለ ሽብርና ሽብርተኝነት
መንስኤዎች ከፕ/ሮ መስፍን ወ/ማርያም "አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ" ከሚለው መጽሐፋቸው የተወሰደ ሐሳብም
ተጠቅሷል፡፡ የሙስሊም-ጠልነት ተሟጋች ምሁራንን ሐሳብ ጠቅለል አድርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ ወደ ተጠቆመው መፍትሄ ለመሻገርም
ጥሩ መንደርደሪያም ይሆናል፡፡ ምልከታዬ እርሱ ላይ ቢሆን ሁሉን ያሳይልኛል ደግሞም የራሴ ናቸውና ለአገራዊው ጠልነት ለተባለው ማሳያ
የእርሳቸው ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ መርጨዋለሁ፡፡ እንዲህ የሚለው ነው የተጠቀሰው፡-
"ሽብርተኛነትን
ከዓረብነት፣ ከጥቁርነት እና ከእስላምነት ጋር የሚያያይዙት ሰዎች ዋነኛ መሠረቱን፣ ሁለተኛ ሙሉ እውነትን አለመገንዘብ ወይም ለመገንዘብ
ካለመፈለግ ሆኖ ነው እንጂ በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ በክርስትና ተወልደው ያደጉ ነጮች በየጊዜው የሚፈጽሙት የሽብር ተግባር ተረስቶ
ሊሆን አይችልም፡፡ ሽብርተኛነት ከጭቆና ከጥቃት ከተዛባ አስተዳደርና ከፍትህ መጓደል የሚመነጭ ነው፡፡"14
የብዙዎቹ ሐሳብ ከዚህ ጋር
ይመሳሰላል ሆኖም ይህ ግማሽ እውነት ነው፡፡ ሁሉም እውነቱን (ሙስሊም ጸሐፍትን አይመለከትም) ስተውታል፡፡ አሁንም ኢስላምን በተመለከተ
በምሁራኑ ዘንድ ጥልቅ ዕውቀት አጠርነት አለ፤ ስለማያውቁት እርግጠኛ ሆኖ መናገር ደግሞ መዘዙ ከበድ ይላል፡፡ ለፋኢዝ ግን ትልቅ
ግብአት ሆነውለታል፡፡
ከሕግ አንጻር ሽብርና አሸባሪ
በትርጉሙና በይዘት ከአገር አገር ሊለያይ እንደሚችል ለእርሳቸውም ሆነ ለፋኢዝ መንገር አይጠበቅብኝም፡፡ እንደተባለው ሽብር ከዓረብነት
ጋር፣ ከጥቁርነት፣ ከነጭነት ጋር ላይገናኝ ይችላል፡፡ ሽብር ከጭቆና፣ ከጥቃት፣ ከተዛባ አስተዳደርና ከፍትህ እጦት ሊመነጭ እንደሚችልም
እሙን ነው፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች የሚፈጸም ሽብር ከምድር፣ ለምድርና በምድር የሚከናወኑ ሲሆኑ መልስ በማግኘት ወይም በኃይል ብልጫ
ሊቆሙ ይችላሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ በቡድንም ይሁን በተናጠል የሚፈጸሙ ሽብሮች ቁጥር በሙስሊሞች ከሚፈጽሙት የበለጡ ሊሆኑ ይችላሉ
(ስሌቱ አጠያያቂነቱ እንዳለ ሆኖ)፡፡ ችግር የሚሆነው እነዚህን በመሠረታቸው የሚለያዩትን ሽብሮች በአንድ መነጽር ማየቱ ላይ ነው፡፡
በኢስላም የሚፈጸሙ ሽብሮችና በሌላ ኀይል የሚፈጸሙ ሽብሮች መሠረታቸው አንድ አይደለም፡፡ የኢስላም የተለየ ነው፡፡ "ሽብር"
ከኢስላም ጋር ዘላለማዊ ትስስር ያለው፣ ከአላህ፣ በአላህና በሙስሊሞች፣ ለአላህ የሚከወን፣ አምላካዊ የውጊያ ስልት፣ በእርሱም ፈቃድ
የሚከናወንና ለሠራተኞቹም ልዩ ምንዳ የሚያስገኝ የማጥቂያ መሳሪያ መሆኑን ፕ/ሮ መስፍን ሆኑ ሌሎቹ ከኢስላም ውጭ ያሉ የሙስሊም-ጠልነት
ተሟጋቾች አያውቁ ይሆናል፡፡ ሽብር በኢስላም፡-
❖ የሽብር ጀማሪና ፈጻሚ መላእክቱን በመጠቀም
ራሱ አላህ ነው፡፡ በነቢዩ ሙሐመድ የመጀመሪያው የዘረፋ የጅሃድ ጦርነት ላይ አላህና መላእክቱ የተገበሩት የትግል ስልት ነበር
ሱረቱል አል አንፋል 8
፡ 12
ጌታህ ወደ መላእክቱ እኔ
(በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ፡፡ በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን ( الرُّعْ ب ) (terror) በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ፡፡ ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ
ሁሉ ምቱ፡፡ ሲል ያወረደውን (አስታውስ)፡፡15
በዚሁ ምዕራፍ በሌላም አንቀጽ
ሙስሊሞች ለማሸበር የሚሆኑ ዘመኑ ያፈራቸውን ምርጥ መሳሪያዎችን እንዲሰበስቡ የራሳቸው እንዲያደርጉ በአላህ ታዝዘው እንመለከታለን፡፡
በዚህም ምክንያት እሽቅድምድሙን ማንም የሚገነዘበው ነው፡-
ሱረቱል አል-አንፋል 8
፡ 60
ለእነሱም ከማንኛውም ኃይልና
ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን
(መናፍቃን) የምታሸብሩበት ( تُ رْهِبُو ن ) (to strike terror) ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡
ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው ወደናንተ በሙሉ ይሰጣል፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡
አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን
ታጁ በተረጎሙት "ሪያዱ አስ-ሷሊሒን" በተሰኘው መጽሐፍ በጅሃድ ምዕራፍ እንዲህ የሚለው የነቢዩ ቃልና የሊቃውንቱ
ማብራሪያ ሰፍሯል፡-
"የአላህ መልእክተኛ
ሚንበር ላይ ቆመው የሚከተለውን ሲናገሩ ሰምቻለሁ በማለት አቡ ሐምማድ አስተላልፈዋል፡- ከኃይል የቻላችሁትን ተዘጋጁላቸው፡፡ አዋጅ!
ኃይል ጦር ውርወራ ነው፡፡ አዋጅ! ኃይል ጦር ውርወራ ነው፡፡ አዋጅ! ኃይል ጦር ውርወራ ነው፡፡
ከሐዲሱ የምንማረው ቁምነገር
• የሙስሊሙን ሕብረተሰብ እምነትና ባሕል ለመጠበቅ ተገቢውን የኀይል ዝግጅት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ቁርአን ይህንን
ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
• ከዚህ የኀይል ዝግጅት ውስጥ ጦር ውርወራ ይገኝበታል፡፡ ጠላትን ማጥቂያ መሣሪያ ነው፡፡ ከዘመን ዘመን ዐይነቱና
ብቃቱ ሊለያይ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሙስሊሞች በዘመኑ የተሻለውን የጦር ስልትና ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡"16
"የተሻለውን"
ኒኩሌይር፣ ሚሳኤሎች፣ ቦምቦች፣ ባዮሎጅካል የጦር መሳሪያዎች፣ ወዘተ ማለት ነው፡፡ እነዚህ የሽብር አንቀጾች የተጠቀሱት ከጅሃድ
ጋር ወይም የጅሃድ አንድ የውጊያ ስልት ሆነው ነው፡፡ ስለዚህ ሽብር በራሱ ጅሃድ ነው፡፡ ጅሃድ ደግሞ ለአንድ ሙስሊም ከጭቆና፣
ከጥቃት፣ ከተዛባ አስተዳደርና ከፍትሕ መጓደል ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ጅሃድ ለአንድ ሙስሊም ከአላህ ጋር የሚገበያይበት
መድረክ፣ ብቸኛው የጀነት በር ነው፡-
ሱረቱል አት-ተውባ 9 ፡
111
አላህ ከምእምናን ነፍሶቻቸውንና
ገንዘቦቻቸውን ገነት ለእነሱ ብቻ ያላቸው በመኾን ገዛቸው፡፡ በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፡፡ ይገድላሉም፤ ይገደላሉም፡፡ በተውራት
በኢንጅልና በቁርኣንም (የተነገረውን) ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ፡፡ ከአላህም የበለጠ በኪዳኑ የሚሞላ ማነው? በዚያም በእርሱ በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ፡፡ ይህም እርሱ
ታላቅ ዕድል ነው፡፡
ሱረቱል አስ-ሶፍ 61 ፡
10-12
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ!
ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የኾነችን ንግድ ላመላክታችሁን?» (በላቸው)፡፡ (እርሷም) በአላህና በመልክተኛው ታምናላችሁ፣ በአላህ
መንገድም በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ትታገላላችሁ ( وَتَُُاهِدُو
ن )፣ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ኃጢኣቶቻችሁን
ለእናንተ ይምራል፡፡ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ያገባችኋል፡፡ በመኖሪያ ገነቶችም በሚያማምሩ ቤቶች ውስጥ (ያስቀምጣችኋል)፡፡
ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
ነቢዩ ሙሐመድም እንዲህ
ብለው እንደነበር ሐዲሳቸው ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡-
"አቡ በክር አቡ
ሙሳ አል-አሸዐሪይ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፤ የአላህ መልዕክተኛ፡- 'የጀነት በሮች ከሰይፎቻችሁ ጥላዎች ሥር ናቸው' ሲሉ መስማቱን
አባቴ በፍልሚያ መስክ ላይ ተናገረ፡፡ የነተበ ልብስ የለበሰ አንድ ሰው ተነሳና፡- 'አቡ ሙሳ ሆይ! የአላህ መልዕክተኛ ይህን ሲናገሩ
አንተው ራስህ ሰምተሃልን?' ሲል ጠየቀ፡፡ አባቴም 'አዎ' አለ፡፡ ወደ ባልንጀሮቹ ተመለሰና፡-'ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ' በማለት
(ተሰናበታቸው)፡፡ ከዚያም የሰይፉን ሽፋን ሰብሮ ጣለና ሰይፉን ይዞ ወደ ጠላት አቅጣጫ ገሰገሰ፡፡ እስኪገደል ድረስም ተዋጋ፡፡"
(ሙስሊም) ይህም እንደ አላህ እቅድ ለእስልምና እንቅፋት የሚሆኑ አካላት የማይገኛባት ዓለም እስከምትቋቋም የሚቀጥል ይሆናል፡-
ሱረቱል አል-አንፋል 8
፡ 39
ሁከትም ( فِتْ نَ ة )17 እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ
ተመልካች ነው፡፡
ስለዚህ ሙስሊም-ጠልነት
(አሳማኝ ባልሆነ (ሆን ተብሎ በተዛባ) ምክንያት መፍራት (መሥጋት)፣ መጥላት እና መጥፎ አመለካከትን በውስጥ መሰነቅ) አለ በሎ
ማለትና ስለመዘዝ መተንተን ስህተት ነው፡፡ በኢትዮጵያችንም ሙስሊም-ጠልነት አለ ብሎ ለመናገር መንደርደሪያ ሊሆን አይችልም፡፡
ይቀጥላል……
1 "… ይህንን ነጥብ ከተረዳን በኋላ አንድ ሰው ከእስልምና ውጭ
ላሉት ጠላትነቱን ካላወጀ፣ ለእነርሱ ያለውን ቁጣና ተቃውሞ ግልጽ ካላደረገ በስተቀር እርሱ "ላ
ኢላህ ኢለላህ" ብሎ
ቢመሰክርም እንኳ ሙስሊም ነው ብለን ለመናገር መብት እንደሌለን እንገነዘባለን፡-
ሱረቱል አል-ሙጃደላ
58 ፡
22
በአላህና በመጨረሻው ቀን
የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው
ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ …"
2 Imam
Ibn Kathir, Tafsir Ibn Kathir vol 9, page 585-589
3 ከእሁድ ጦርነት በኋላ በመዲና አካባቢ የነበሩትን አይሁዳውያን በሙሉ
ተበቅሏል፡፡ ትግስቱና ምህረቱ እስከዛ ቀን ድረስ ብቻ ነበር፡፡ በአላህና በጅብሪል ትእዛዝ የበኑ ቁሬይዛን ጎሳ በአንድ ቀን በመዲና
ገበያ ላይ ጅምላ መቃብር በማስቆፈር 900 የሚሆኑ ወንዶችን ነቢዩ ራሳቸው አሳርደዋል፡፡
4 (قَاتَ
لَهُمُُ ) የሚለው
ቃል በተለያዩ ቁርአንን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ በመለሱ ሰዎች እንዲህ ተብሎ ተተርጉሟል፡- destroy, curse be on
them, የአማርኛው ያጥፋቸው በማለት ይረግማል፤ በሌሎች የቁርአን አንቀጾች ቃሉ 'ግደሏቸው' ተብሎም እንደተተረጎመ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ከሱራ 9 ፡ 5 ጋር ማነጻጸር ይቻላል፡፡
5 ኡስታዝ አምባሳደር ሐሰን ታጁም "ሙስሊም
ያልሆኑ ወገኖች በሙስሊም ማኅበረሰብ ውስጥ"
በሚል ርዕስ የዶ/ር
ዩሱፍ አል-ቀረዷዊን
መጽሐፍ ተርጉሞ አስነብቦናል፡፡ ምናልባት ኢስላማዊ መንግስት ኢትዮጵያን ናፍቆ ይሆን ቀድሞ መተዳደሪያችንን ሊያስተዋውቀን የፈለገው?
6 Imam
Ibn Kathir, Tafsir Ibn Kathir vol 4, page 406-407.
8 ሙስሊም-ጠልነት በኢትዮጵያ ገጽ 15
9 Douglas
Murray, Islam-ophilia, page 5
10 ሙስሊም-ጠልነት በኢትዮጵያ ገጽ 14-15
11 …ኢስላም በዴሞክራሲና በንጉሳዊ አገዛዝ መካከል ያለም የአገዛዝ ስርአት
ያቀርባል፤ በሁለቱ አገዛዞች ያለን ጉድለት ያስወግዳል፡፡…. (https://www.alquranclasses.com/difference-between-deen-and-religion) (በአብዱልሐቅ ጀሚል፣ ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን? መቸስ ተጀመረ?፣ ገጽ 19-20)፡፡
12 "The
word is applied to anything which could be deemed offensive to any Muslim,
anytime, any place, anywhere. Personally, I think the word is a crock – for a
lot of reasons, but not least among them that a ‘phobia’ is an
irrational fear.
There is nothing ‘irrational’ about fearing parts – though certainly not all – of Islam.
For example, it would be rational to be ‘phobic’ of the 7/7 bombers and the
9/11 hijackers.
It is rational to be ‘phobic’ about Islam if you are a
Dutch film-maker,
or an American ambassador in Benghazi or, as we now know, a soldier in south London. The
perpetrators were all people who acted in the name of Islam. They may have been
right in
believing this, or they may have been wrong. But being ‘phobic’ of such things
is a perfectly rational instinct – indeed, one might call it a survival instinct.
13 Narrated
Ibn `Umar: Allah's Apostle said: "I have been ordered (by
Allah) to fight against the people until they testify that none has the right
to be worshipped but Allah and that Muhammad is Allah's Apostle, and offer the prayers
perfectly and give the obligatory charity, so if they perform a that, then they
save their lives an property from me except for Islamic laws and then their
reckoning (accounts) will be done by Allah." (sahih al-Bukhari vol 1, # 25, page 66)
14 ሙስሊም-ጠልነት በኢትዮጵያ ገጽ 38
15 12.
(Remember) when your Lord revealed to the angels, "Verily, I am with you,
so keep firm those who have believed. I will cast terror into the hearts of those who
have disbelieved, so strike them over the necks, and smite over all their
fingers and toes.'' (Tafsir Ibn Kathir sura 8 : 12)
16 ሪያዱ አስ-ሷሊሒን ቅጽ 2፣ ሐዲስ ቁጥር 1332፣ ገጽ 229
17 ( فِتْ نَة ) ፊትነቱን ምንድን ነው ለሚለው
ሊቃውንቱ፡- Fitnah (disbelief and polytheism, i,e, worshipping beside Allah)

0 Comments