ሳሂህ ኢማን
1.ጀዋር ሙሐመድ
የፋኢዝ አባይ ብዕር
የጻፈውን ደግሜ ብጽፈው መልካም መስሎ ታይቶኛል፡-
"ስሙ
'የሙስሊም' በመሆኑ ብቻ የሚናገራቸውንና የሚሠራቸውን ተግባራት ለማጣጣል የሃይማኖት ዱላ ተመዞበት ዱብዳ እየወረደበት የሚገኘው…"፡፡
እንዲህ ዐይነት
ፍጹም እብለት አጋጥሞኝ አያውቅም፤ ምን አይነት አንባቢን የሚንቅና የሚሸመጥጥ ልብ ነው ያለው? እንደሚመስለኝ የጃዋር ሜንጫ ፋኢዝም
ቤት አለ፣ ወይም ጃዋርን በሕዝብ እንዲገፋ ያደረገው ሐሳብ ፋኢዝም ውስጥ በሙላት አለ፡፡ ስለዚህ "አገሬ አገሬ"
የሚለው ለሽንገላ እንጂ አገር ልቡ ውስጥ ስላለች አይደለም፡፡ ወይም ደግሞ ጅሃድን ከመደገፊያ 44 መንገዶች መካከል አንዱ የሆነውን
"ለሙጅሃዲኖች ጠበቃ መሆንና እነርሱን መደገፍ"1 የሚለውን ጅሃዳዊ ሥርዐት እየፈጸመም ሊሆን
ይችላል፡፡ ፋኢዝ "ጂሃድ" ላይ ነው ማለት ነው፡፡
ለማንኛውም ጃዋር
ላይ "ጥላቻ" የሚለው የመጣው እርሱ ለክርስቲያኖችና ለክርስትና ካለው ከኢስላም ልብ ከሚመነጭ ጥልቅ ጥላቻ የተነሣ
መሆኑን አገር ያውቀዋል፡፡ ይህ እየታወቀ መዋሸት ለምን አስፈለገ? ማስታወሻ ማድረግ ይቻላል፤ ራሱም በጥላቻው ጥላ ውስጥ ስላለ፡፡
ጃዋር በአደባባይ አሜሪካን አገር በሚኖሩ ሙስሊም ኦሮሞ ወንድሞቹ መካከል ምን እንደተናገረ እያወቀ፣ ሰዎችም የሰሙት ጉዳይ ሆኖ
እያለ ሽምጥጥ ማድረግ ፊደል ከዘለቀ ራሱን "MSc, MA, Ph.D. candidate" ብሎ ካስተዋወቀ ሰው እንዴት
ይጠበቃል? "ሙስሊም ከሆንክ ኦሮሞ ነህ፣ ኦሮሞ ከሆንክ ደግሞ ሙስሊም ነህ" በሚል ጥርት ባለ ንግግር ክርስቲያን
የሆኑትን ኦሮሞዎችንም እንደሚጠላቸውና በኦሮሞነት እንደማያውቃቸው አሳይቷል፡፡ ይህም አልበቃውም፤ ሁሉን አድማጭ ባስደመመ መንገድም
"እኛ አካባቢ 99 በመቶ ሙስሊም ነው፤ ቀና እላለሁ ቢል ዐንገቱን በሜንጫ ነው የምንለው" በማለት የተናገረ ሰው
ነው፡፡ በዚህ አባባሉም ኢስላማዊ ተልእኮ ይዞ እንደተነሣ ታምኗል፡፡ ከዚህም የተነሣ በእውነተኛ ክርስቲያን ኦሮሞዎች ሳይቀር ተወግዟል፡፡
ይህን እውነት ሸምጥጦ "የሙስሊም ስም ስላለው ውግዘት እንደደረሰበት" ብሎ ማለት በጣም ማነስ ነው፡፡ አሳፋሪም
ነው፡፡ አንባቢን መናቅና በሐሰተኛ መረጃ ለማታለል መሞከር ነው፡፡ መቸም አንድ ራሱን የ "Ph.D.
candidate" ያለ ሰው ፀሓይ የሞቀውን እውነት አልሰማሁም ብሎ የሚሸመጥጥ ከሆነ ደግሞ ምን ያክል ለመረጃ ባእድ የሆነ
ዕውቀት እንዳለው በስሱም ቢሆን ይጠቁማል፡፡
ጃዋር
"ኢስላማዊ ተልእኮ አለው" ከ100 በላይ ሰዎች ባለቁበት በጥቅምት 2012 ቱ የኦሮሚያ ሁከት በግልጽ ታይቷል፡፡
ሆኖም "ኢስላማዊ ተልእኮውን" ለመሸፋፈን ፋኢዝ ያቀረበው ማስረጃ እንዲህ የሚል ነው፡-
"ጃዋር
እስላማዊ መንግስት ይቅርና እስላማዊ ቤተሰብ የመመስረት ፍላጎት እንኳን እንደሌለው ፕሮቴስታንት ባለቤቱንና ኦሮሞ ልጁን መመልከቱ
በቂ ነበር፤ በተጨማሪም መሠረታዊ የሃይማኖቱን ድንጋጌዎች አለመከተሉን አክለንበት ማለት ነው፡፡…."2
ይገርማል! የተመታ
ማስተባበያ ነው፤ "ለማያውቅ መታጠን" ይሻላል፡፡ አላዋቂን ማታለል ይሻላል፤ ግን ደግሞ ዐልፎበታል፡፡ ጃዋር የትኞቹን
የሃይማኖት ድንጋጌዎች ይሆን የጣሰው? ፋኢዝ እንዲህ ይበል እንጂ አንዱንም ጥሰት አልጠቀሰም፡፡ ለምን? ሐሰት ነዋ! ምናልባት እንደ
ማሳያ የተጠቀሰው ቤተሰቡን ለማለት ከሆነም ከሃይማኖቱ ዝንፍ ሳይል እንዳደረገው ቁርአን እንደሚመሰክር ራሱ ፋኢዝ ምስክር መሆን
ይችላል፤ ብዕሩ አበለ እንጂ፡፡ ቁርአን እንዲህ ይላል፡-
ሱረቱል አል-ማኢዳ
5 ፡ 5
ዛሬ መልካሞች ሁሉ
ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ
ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም "ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር
ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን
1 Anwar_Al_Awlaki, 44 Ways to
Support Jihad, # 12.
2 ዝኒ ከማሁ ገጽ 103
በሰጣችኋቸው ጊዜ
(ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡
እንዲህ ዐይነት
ተግባር በርሱ አልተጀመረም፤ ከነቢዩ ሙሐመድ የተማረው ነው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድ የተነሡለትን ዐላማ ከግቡ ለማድረስ ሲሉ የዘጠኝ ዓመት
ሕጻን ሳይቀር ፖለቲካዊ ጋብቻ ፈጽመዋል፡፡ የከሊፋ አቡበከርን ልጅ አይሻን፣ የከሊፋ ኡመርን ልጅ ሀፍሳን፣ ሁለት ሴት ልጃቸውን
ለከሊፋ ኡስማን ድረዋል፣ ለከሊፋ አሊ ደግሞ ፋጡማን ድረዋል፡፡ አይሻ ከኩዮቿ ጋር ዥዋ ዥዌ ከምትጫወትበት ቦታ እናቷ ወስዳ ለነቢዩ
ስትሰጣቸውና እርሳቸው የ 54 ዓመት ጎልማሳ ሆነው እያለ ወሲብ ሲፈጽሙባት ገና የዘጠኝ ዓመት ሕጻን ነበረች፡፡3
ስለዚህ ጃዋር ፋኢዝ
እንዳለው ሳይሆን ፍጹም ሃይማኖተኛ መሆኑንም ወደ አገር በተመለሰ ማግስት ሙስሊሞች ዐቅም ካላቸው አንድ ጊዜ ሊያደርጉት የሚገባውን
የአላህን ቤት መጎብኘቱንም "ሃጅ" በማድረግ በሌላኛው መልኩ አስመስክሯል፡፡ ታዲያ ጃዋር የትኛውን የሃይማኖት ሕግጋት
ይሆን የተላለፈው? ደግሞስ ለሃይማኖቱ ጥቅም እስከሆነ ድረስ ቢጥስ የሚከለክለው የትኛው የቁርአን አንቀጽ፣ የትኛው የሸሪአ ሕግ፣
የትኛው የነቢዩ ሱና ነው? በሃይማኖቱ የተከለከሉ ሕግጋት ለኢስላም ሲባል እስከምን ድረስ ሃላል ሊደረጉ እንደሚችሉ ግርጌ ላይ ያለውን
ሊንክ ከፍተው ቢመለከቱ ይደርሱበታል፡፡4 በተጨማሪም ኢማም ኢብኑ ካሲር በሱራ 3 ፡ 28 ላይ ከሰጡት ማብራሪያ ቀንጨብ
አድርጌ ላሰስነብብ፡-
(unless
you indeed fear a danger from them) meaning, except those believers who in some
areas or times fear for their safety from the disbelievers. In this case, such
believers are allowed to show friendship to the disbelievers outwardly, but
never inwardly. For instance, Al-Bukhari recorded that Abu Ad-Darda' said,
"We smile in the face of some people although our hearts curse them.''
Al-Bukhari said that Al-Hasan said, "The Tuqyah is allowed until the Day
of Resurrection.''
Tuqyah5፡- ማለት ምን
ማለት ይሆን?
- the
practice of denying one's religion, permissible when one is faced with
persecution, especially by Sunnites: regarded as a means of protecting the
religion.
- Taqiyah
Precautionary denial of religious belief in the face of potential persecution.
Suessed by Shii Muslims, who have been subject to periodic persecution by the
Sunni maiority. The concept is based on Quran 3: 28 and 16:106 as well as
hadith, tafsir literature, and furidical conrmentaries.
በተጨማሪም ፋኢዝ
ጃዋርን እስላማዊ ተልእኮ እንዳለው አድርጎ መናገር ሊያስከትል ስለሚችለው ውጤት በማስፈራራት እንዲህ ብሏል፡-
"የምፈራው
ግን በቅጡ ሳያስቡበት እያራገቡት ያለው አጀንዳ ወደ ፊት 'እስላማዊ ኦሮሚያን' አማራጭ የሚያደርግ ትውልድ እንዲመጣ የሕዝቡን ጀሮ
እያለማመዱት እንዳይሆን ነው፡፡"6
3 Narrated Aisha: The Prophet
engaged me when I was a girl of six (years). We went to Medina and stayed at the home of Bani−al−Harith bin
Khazraj. Then I got ill and my hair fell down. Later on, my hair grew (again)
and my mother, Um Ruman, came to me while
I was playing in a swing with some of my girlfriends. She called me, and I went to her, not
knowing what she wanted to do to me. She caught me by the hand and made me
stand at the door of the house. I was breathless then, and when my breathing
became All right, she took some water and rubbed my face and head with it. Then
she took me into the house. There in the house I saw some Ansari women who
said, "Best wishes and Allah's Blessing and a good luck." Then she
entrusted me to them and they prepared me (for the marriage). Unexpectedly
Allah's Apostle came to me in the forenoon and my mother handed me over to him,
and at that time I was a girl of nine years of age. (Sahih
Al-Bukhari vol 5, hadith # 234.)
4 https://youtu.be/ryE-5a1D-9Y
5 በአጭር ቃል "ማታለል" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
6 ሙስሊም-ጠልነት ገጽ 103
በዚህ ውስጥ ሁለት
ሐሳቦች አስገርመውኛል፤ አንደኛው ፋኢዝ 'የምፈራው' ያለው ነው፡፡ እውነት ፈርቷል ወይስ ስላቅ መሆኑ ነው? ለምንድን ነው የሚፈራው?
'የምፈራው' ማለቱ ሙስሊም ስለሆነ ከኢስላም ተልእኮ አንጻር እንዴት ይታረቅለታል? ነቢዩ ሰው ሁሉ እስልምናን ካልተቀበለ ምን ማድረግ
እንዳለባቸው አላህ ምን እንዳዘዛቸው አልሰማምን?፡-
Narrated
Abu Huraira: Allah 's Apostle said, " I have been ordered to fight with
the people till they say, 'None has the right to be worshipped but Allah,' and
whoever says, 'None has the right to be worshipped but Allah,' his life and
property will be "saved" by me except for Islamic law, and his
accounts will be with Allah, (either to punish him or to forgive him.)"
(sahih Al-bukhari vol 4, hadith # 196) ማሰለም ወይም መግደልንና መዝረፍን የታዘዘ ሰው እዛ ሳይደርስ በአጭር
የሚሰልም ትውልድ ሲያገኝ ምን ያስፈራዋል?
ሁለተኛው ሐሳብ
‘ኢስላሚክ ኦሮሚያ’ ያለው ነው፡፡ ሐጅ ሙፍቲ ኡመር በቅርብ በጃዋር ምክንያት በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ሁከት በባሌና በአርሲ ክርስቲያኖችን
በሃይማኖታቸው ምክንያት ስለ ተፈጸመባቸው ግድያ ሲናገሩ "ሃይማኖት ምርጫ ነው" አሉ፡፡ ሌላውን እንተወውና የሃይማኖት
ዋና ዐላማ ሰዎችን ከሞት በኋላ ለሚጠብቃቸው ሕይወት ኑሯቸው በገነት እንዲሆን መርዳት ነው፡፡ አይደለም ድፍን የኦሮሚያ ትውልድ
መላው ዓለም ኢስላም ገነት ያደርሰኛል ብሎ ካመነ መንጎድ ይችላል፡፡ መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት፡፡ ክርስቲያኖች በዕውቀትም ይሁን
ያለ ዕውቀት የሰዎችን እስልምናን መቀበል ለመከላከል የሚሞክሩትና ከኢስላምም ሰዎችን ወደ ክርስትና የሚጣሩት ሰው በኢስላም ሆኖ
ገሃነም እንዳይገባ ለመርዳት እንጂ ለምንም አይደለም፡፡ ፋኢዝ እንደሚያውቀው በኢስላም ምንም ዐይነት የዘላለም ሕይወት ተስፋ የለም፡፡
ቁርአን እንደተናገረው ነቢዩም እንዳጸደቁት ሁሉም ሙስሊም ገሃነም ይወርዳል፡-
ሱረቱል መርየም
19 ፡ 71
ከእናንተም ወደ
እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ (መውረዱም) ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፡፡
وَإِن مِِّنكُمْ
إِالَّ وَارِدُهَا كانَ عَلَىٰ رَبِِّكَ حَتْمًا امقْضِيًّا ] ١٩:٧١ ]
ስለዚህ ለዚህ ሌላ
ትርጉም መስጠትና ማስፈራራት፣ መፍራትም አያስፈልገውም፡፡
2. አቶ ታማኝ
በየነ
ያስገረመኝና ያስደመመኝ
ካለቀሰው ጋር የሚያለቅሰው፣ ከታመመው ጋር የሚታመመው፣ ከሚደሰተው ጋር አብሮ የሚደሰተው ታማኝ በየነ ስሙ ተጠቅሶ ስመለከት ነው፡፡
ውድ ፋኢዝ ተው አይመጥነውም፡፡ ምናልባት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በተመለከተ ላሰማው ድምጽ ውለታ እንዲሆን አስበህ
ከሆነ እርሱ እንዳልኩት ዐይነት ሰው ስለሆነ ያደረገው ነው፡፡ ስለ ኢስላም ያደረገው አይደለም፤ ስለ ሰው ያደረገው ነው፡፡ አሕመዲን
ጀበል ቂሊንጦ እያለ ታመመ ሲባል እኮ እልፍ ሆነን ድምጻችንን አሰምተናል፡፡ የኢስላምን ማንነትና እርሱን አጥተነው ሳይሆን ወንድማችን
ስለሆነ ያደረግነው ነበር፡፡ ምናልባት የዚህ መጽሐፍ ይዘት ቢያስታውስ ሊመጥን የሚችለው ሃይማኖት እየለዩ እጃቸውን ለሚዘረጉና ለሚጮሁት
ለአቡበከር አሕመድና ለካሚል ሸምሱ ነበር፡፡
አቡበከር ከእስር
የተፈታበት ወቅት ኢትዮጵያ አንድ ብርቱ ሐዘን ወድቆባት ነበር፡፡ በቆሼ የቆሻሻ ክምር ተንዶ ከ 20 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ዐልፎ
ነበር፡፡ በዛ ወቅት ትውልድ ሃይማኖት፣ ዘር፣ ቋንቋ ሳይለይ የተጎዱትን ለመርዳት ተንቀሳቅሷል፡፡ አቡበከር አሕመድ "ድምፃችን
ይሰማን" ወክሎ የዘየረው (የጎበኘው) እና በገንዘብ የደገፈው ሃይማኖት እየለየ ምንም ያልተጎዱ የአካባቢውን ሙስሊሞች ብቻ
ነበር፡፡ ከትውስታ ማህደራችን እንዲህ ያሉትን እየመዘዙ መጠቃቀስ ይቻላል፣ ብቻ ልተወው፡፡
ሌላው ስለ ታማኝ
እንዲህ በማለት ነበር ያስታወሰው፡- "‘አሏሁ-አክበር’ ማለት ‘ምታው’ ማለት ነው በተባለበት ዓመት ‘አሏሁ-አክበር’ ማለት
‘እግዚአብሔር ታላቅ ነው’ ማለት ነው በማለት…"፡፡ በእርግጥ ፋኢዝ የሚጽፍለትን ሕዝብ ያውቀዋል? አሰኝቶኛል፡፡ ሙስሊም
አሏሁ-አክበር በማለቱ ሌላው ሥጋት ተሰምቶት የሚያውቀው መች ይሆን? ቢያንስ ቃሉ በቀን አምስት ጊዜ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን
እስከ ደቡብ ሲታወጅ እየሰማው ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የመጽሐፉ ወይም የጸሓፊ ሥነ-ልቡና ምን ሊሆን እንደሚችል የዕውቀት ቁልፉን
እንካችሁ ይላል፡፡ ለማንኛውም ግን መጽሐፉ ሚዛናዊነት የሌለውና በጉድፍ የተሞላ በመሆኑ ታማኝን በዚህ ማቆሸሽ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም፡፡
3. መጭው አገር
ተረካቢው ትውልድ
ፋኢዝ መጽሐፉ አገር
ተረካቢውን ትውልድ እንዴት ይመጥንልኛል ብሎ አሰበ? መች እውነት ነገራቸውና ሃይማኖትና ዘር ሳይለዩ፣ ሳይለያዩም ጠንክረው አገርን
እንዲጠብቁ ይጠይቃቸዋል? የእርሱ እስልምናስ በሃይማኖትና በዘር አለመለያየትንና እኩልነትን ይሰብካልን? በኢትዮጵያ "ሙስሊም-ጠልነት"
አለ፣ ነበርም ብሎ ካመነ ምክንያቱን ለምን ከምንጩ አልተናገረም? እውነትን ለምን ይደብቃል? እርሱ ‘ታሪክ ተበላሽቶ ተላልፏል’
ብሎ ሌላውን እየከሰሰ እንደገና ራሱ በዛው ወንጀል ተጠላልፎ ከተገኘ እንዴት ለአገር ተረካቢ ትውልድ "እንዲህም አለ"
ሊል ይችላል? ትውልዱ እንዲህ ዐይነት ክፉ ትርክቶች ተጭነውት እርሱን የሚያራግፍለትና ሕሊናውን የሚያነጻለት ይፈልጋል እንጂ ተጨማሪ
በደል ቆጣሪ ምን ይሠራለታል፡፡ አገሪቱን ወደ አዘቅት እየመራት ያለው ያልተፈጸሙ በደሎችን እንደተፈጸሙ አድርጎ በመቁጠር እርሱን
ማኘክ አይደለምን? ወዳጄ ትውልዱ ደክሞታል፣ ከብዶታል ሌላ የሚንጠው ሸክም አትጨምርለት፡፡ ወይስ ሐሰተኛ የበደል ትርክቶች አሁን
ያለንበት የዘር ጦርነት ውስጥ ከቶናል፤ አንተም በዚህ ሐሰተኛ የበደል ትርክትህ ሃይማኖታዊ ጦርነት እንዲነሣ ትፈልጋለህ?
ለማንኛውም አገራችን
አንዱ ገደለ፣ ሰረቀ፣ በደለ ተብሎ ከስልጣን ሲወገድ ያስወገደው ተመልሶ እዛው ተረኝነት ላይ የሚገኝባት እንዲያውም በብዙ እጥፍ
የሚተገብርባት አገር ናት፡፡ ትውልዱ ይህ እያንገፈገፈው ባለበት ሌላ የንትርክ መድረክ አትፍጠርበት፡፡ ለትውልዱ የሚያስፈልገው ከዚህ
ካለበት አዙሪት የሚያወጣ ፍቅርን፣ ምሕረትን፣ ይቅርታን የሚሰብክ እንጂ ጀሮውን ሞልቶ እየፈሰሰ ያለውን ሚዛናዊ ያልሆነ የበደልን
መአት የሚተርክለት አይደለም፡፡ ለዛውም መረጃ እየተደበቀ፡፡ ለአገር መልካም አስባለሁ የሚል እንዲህ ዐይነት መጽሐፍን ለአገር ተረካቢ
ትውልድ ማስታወሻ ሊያደርግ አይችልም፡፡ አይመጥንም፡፡
ጉድፍ ሁለት፡-
ፋኢዝ በመግቢያው
አገራችን ሥልጡን እንደነበረች ነገር ግን ካለፉት ዘመናት ጀምሮ ከነበረው የፖለቲካ አስተዳደር ችግር የተነሣ መጠላለፍ የበዛበትና
ያንን ሥልጣኔ ማስቀጠል ሳይቻል ቀርቶ ለዜጎቿ የማትበቃ አገር አድርጓታል፤ ለዚህ ተጠያቂው ደግሞ "ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት"
መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡ ይህንን ሥርዎ መንግሥት "አግላይ" ብሎታል፡፡ ያገለለው ማንን ነው? ሲባል አጠቃላይ
መጽሐፉ እንደሚነግረን ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ፋኢዝ የዚህን ሥርወ መንግሥት አስተሳሰቦች ለመተቸት በቁርጠኝነት
እንደተነሣሣም ይናገራል፡፡ ለዚህ ደግሞ የኮሪያ ዘማቹ አያቱ፣ በምስራቅ (ሶማሌ) በሰሜን (ኤርትራ) በርሃዎች የታገሉት አባቱ፣
በተመሳሳይ ግምባሮች የተሰለፈው አንድ አጎቱ፣ እንዲሁም በዘመቻ ፀሓይ ግባት ሌላው አጎቱ ባደረጉት ተጋድሎ በደም ሥሩ የጨመሩበት
አገር ወዳድነት ከእነርሱም የወረሰው አገራዊ አደራ ግድ እንደሚለው ይገልጻል፡- "
"እኔም
ታዲያ እንደ አንድ አገሩን እንደሚወድ ዜጋ በተለያዩ ዘርፎች ወደፊት ወገኔን ለማገልገል ካለብኝ ኃላፊነት በተጨማሪ ይህን
"አግላይ" ትርክት በመተቸት ዳግም እንደዚህ አይነት ትብታብ ተከስቶ ትውልዱን መቀመቅ ውስጥ እንዳይገባ የምችለውን
ለማድረግ ኃላፊነት እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ እንደዚሁም ከቤተሰብ የተረከብኩት አገራዊ አማና (አደራ) ሁሌም እንቅልፍ የሚያስተኛ
አይደለም"
በእውነት የአገራችን
ፖለቲከኞች ከአገር ወዳድነት ጎጥ አፍቃሪነት ላይ ተፈናጠው ትንሽ በሆኑበት በዚህ ዘግናኝ ዘመን አገር ወዳድ፣ ለትውልድ ተቆርቋሪና
ባላደራ ሰው ማግኘት እንዴት መታደል ነው፡፡ ያውም ዘርና ሃይማኖት ሳይለዩ ተባብረውና ጠንክረው አገራቸውን የሚጠብቁ መጭ ትውልድ
ማየት የሚናፍቅ ከመታደል በላይ ነው ወዳጄ፡፡ ነገር ግን ፋኢዝ ያ ሰው እንዳልሆነ መጽሐፉ በግልጽ ያሳብቃል፡፡ እነዚህ የጦር ሜዳዎች
ጀግኖች አባቶቹ አባቶቻችን ክብራችን ናቸው፤ ሃይማኖት፣ ዘር ሳይለዩ ለሁላችንም ንጹሕ ፍቅራቸውንና ልባቸውን ቆርሰውልናል፡፡ እናመሰግናለን!!!
ፋኢዝ ግን የእነዚህን የጀግኖች አባቶቹን ንጹሕ ልብ ዐይነት ልብ ስሌሌለው ሊቆርስልን አይችልም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከእውነት እርቆ
ጭፍን በደል ቆጣሪ ነውና፡፡
ያለፉት ሥርዎ መንግሥታት
አግላይነት የለባቸውም ብዬ ልሟገትላቸው ነውን? በፍጹም አይደለም፡፡ የትኛውም ሥርዎ መንግሥት ወደራሱ የሚያስጠጋው እንዳለው ሁሉ
የሚያገለውም እንደሚኖረው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በነቢዩ ሙሐመድም ግለ ታሪክ ውስጥ እንዲሁ እንደነበር ራሱም ያውቀዋል፡፡ ከዚህ
የጸዳ ሥርዐት በየትኛውም ዘመን አልነበረም፣ አሁንም የለም፣ ወደፊትም አይኖርም፡፡ ታዲያ እነዛ ያላቸው ሥርዎ መንግሥታት የገፉት፣
ያገለሉት አንድን ወገን ለዛውም ሙስሊሙን ብቻ ነውን? ለሚለው መልሱ ሐሰት ነው፡፡ ሌሎቹም መገለል ደርሶባቸዋልና፡፡ ብዕሩ እውነትን
ማቅለም ፈጽሞ አልተቻላትም፡፡ አትችልም፡፡ ምክንያቱም የፋኢዝ ልብ የአባቶቹ ሳይሆን የኢስላም ልብ ነው፡፡ የአባቶቹ ልብ ስለሌለውም
የአባቶቹን አደራ ያልማል እንጂ ሊፈጽመው አይቻለውም፡፡ ሙስሊሙ መገለል ደርሶበታል፣ ተበድሏል ካለም ያ ለምን ሊሆን እንደቻለ ፋኢዝ
ያልጠቀሳቸውን ምክንያቶች በስተመጨረሻ በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡
ይቀጥላል….
0 Comments