ሳሂህ ኢማን
ጉድፍ ሦስት፡-
ፋኢዝ አለ፡-
"ይህ መጽሐፍ
ስለ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ቢዳስስም "እንደዚህ ተደረግን" "ተበደልን" "ተጨቆንን"
የሚል ብሶትን ለማሳመንና የበለጠ ቂምን ለመቆስቆስ አይጥርም …"
"ወዶ አይስቁ!"
አሉ አበው፡፡ ምን ዐይነት ሸንጋይ ሰው ነው? ከዚህ በላይ ምን ሊያደርግ ይችል ነበር? የአባቶቹ ልብ የለውም ያልኩት ለዚህ ነው፡፡
እርሱ የጠቀሰውን ሥርዎ መንግሥት ዘመን እናቆየውና ያለፉትን 50 ዓመታት የኢትዮጵያን ፖለቲካ የተገነባው እንዲህ ዐይነት
"ተበደልን ተጨቆንን" የሚሉ በሬ ወለድ ስብከቶች አይደሉምን? በእነዚህ በሬ ወለድ የተበደልክ ትርክቶች ቂመኛ፣
ይቅርታ የማያውቅ፣ ጨካኝ፣ ሰይጣን ክፋት የሚበደረው አውሬ እንዲሆን ለተደረገ ትውልድ ይህም በደል ደርሶብሃል፤ ነገር ግን ተበድለሃል
ልልህ አይደለም እንዴት ይለዋል? ይህ ነው በ"ቡርሃን" አባባል መንደርደሪያዬን እንድጀምር ያደረገኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ
በአገር ወዳድ ልብ የተገፋች ብዕር የከተበችው ሳይሆን ባለው የብሔር እሳት ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣትና
የጃዋርን ሜንጫ ለመሳል የተተፋ የቀለም ሞረድ ነው፡፡
ጉድፍ አራት፡-
የመጽሐፉ መግቢያ
ቢያንስ መጽሐፉ ሦስት ዐላማዎች እንዳሉት ይተርካል፤ እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡-
ዐላማ አንድ፡-
"በአገሪቱ
ጉዳይ ወሳኝ የሆኑት ውስን ግለሰቦች ወይም ስብስቦች (ሙስሊም ያልሆኑ ማለቱ ነው) ብቻ ሲወስኑ ስለተመለከተና ይህ ደግሞ አገርን
ሊሰነጥቅ የሚችል ቁርሾ በመሆኑ እርሱን ለማከም"
ለዚህ መፍትሄ እንዴትና
ከየት ሊያመጣ ይችላል? በየትኛው መንገድስ ቁርሾን ሊያስወግድ ይቻለዋል? ያን ለማድረግ ቁርአናዊ መርህስ አለውን? ውሃ ቢውቅጥ
ይቀለዋል፡፡ መጽሐፉ አገር ለመሰንጠቅ የሚዳርግ በደልን ይቆጥራል እንጂ ከዛ ሊያድን የሚችል የሐሳብ ቀመር አላየሁበትም፡፡ ወገንተኛ
ሳይሆኑ ያነበቡት ሁሉ የሚመሰክሩት ነው፡፡ ኢስላም የሚፈልገው የበላይ በመሆን ሌላውን እየረገጠ ብቻውን መወሰን እንጂ ለሌሎች ሥልጣንን
ማጋራትና ከሌሎች ጋር ተማክሮ መወሰን በባሕሪው ውስጥ የለም፡፡ ስለዚህ አባባሉ ለሽንገላ እንጂ ለደኅንነት የታለመ አይደለም፡፡
ሱረቱል አት-ተውባ
9 ፡ 33
እርሱ ያ አጋሪዎቹ
ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡1
ዐላማ ሁለት፡-
1 ኢማም ኢብን ከሲር "ከሃይማኖት ሁሉ በላይ"
የሚለውን ሲፈቱት እንዲህ የሚል ነው ያሰፈሩት ሳልተረጉም ይኸውና፡- (to make it (Islam) superior over
all religions) It is recorded in the Sahih that the Messenger of Allah said,
(Allah made the eastern and western parts of the earth draw near for me ﴾to see﴿, and the rule of my Ummah
will extend as far as I saw.) Imam Ahmad recorded from Tamim Ad-Dari that he
said, "I heard the Messenger of Allah saying, (This matter (Islam) will
keep spreading as far as the night and day reach, until Allah will not leave a
house made of mud or hair, but will make this religion enter it, while bringing
might to a mighty person (a Muslim) and humiliation to a disgraced person (who
rejects Islam). Might with which Allah elevates Islam (and its people) and
disgrace with which Allah humiliates disbelief (and its people).) Tamim Ad-Dari
﴾who was a
Christian before Islam﴿ used to
say, "I have come to know the meaning of this Hadith in my own people.
Those who became Muslims among them acquired goodness, honor and might.
Disgrace, humiliation and Jizyah befell those who remained disbelievers.''
"እስልምናን
እና ሙስሊሞችን በተሳሳተ መንገድ በመረዳት ለዘመናት በማግለል ላይ የተመሠረተ ትርክትና ፖሊሲ በመኖሩ ተባብረንና ተፈቃቅረን ሁላችንም
የምንኖርባት ሰፊ አገርን እንጂ የምንናቆርባት ጠባብ ኢትዮጵያን ላለመገንባት በትርክት ደረጃ ቀድመን ማስተካከል ያለብን ለመጠቆም"
ይህም ቢሆን ውሃ
የማይቋጥር ዐላማ ነው፡፡ ፋኢዝ እያታለለ ካልሆነ በስተቀር በየትኛው የቁርአንና የሱና መሠረት ነው ሙስሊም ከሙስሊም ውጭ ያለን
ሰው ሊያፈቅር የሚችለው? እንዲህ የሚለውን የቁርአን ቃል ምን ሊያደርገው ነው?
ሱረቱል አል-ማኢዳ
5 ፡ 51
እናንተ ያመናችሁ
ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች (أَوْلِيَاءََ ) (አውሊያ)2 አድርጋችሁ አትያዙ፡፡
ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች
አያቀናም፡፡
ታዲያ እንዲህ አይነት
አግላይና ነጣጣይ መጽሐፍ የሚያምንና የሚከተል ሰው እንዴትና በምን መንገድ ተችሎት መፈቃቀርን ሊያመጣ ይችላል? ሌላው ይቅር ቁርአን
ወርዶ በቤተሰብም መካከል መነጣጠልንና ጠላትነትን እንደሚዘራ አያውቅምን?
ሱረቱል አት-ተውባ
9 ፡ 23
እናንተ ያመናችሁ
ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች (أَوْلِيَاءََ ) (አውሊያ) አድርጋችሁ
አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው፤
ሌላ ልጨምር፡፡
አንድ ሰው እስልምናን ሲቀበል ከሚናገረው የምስክርነት ቃል (ሸሀዳ) ጋር በተያያዘ አስተሳሰቡ በዓለም ሙስሊሞች ዘንድ የናኘው የሳውዲው
ኢማም ሙሐመድ ኢብን አብዱልወሀብ ከተናገረው አንድ ልጨምር፡-
"… ይህንን
ነጥብ ከተረዳን በኋላ አንድ ሰው ከእስልምና ውጭ ላሉት ጠላትነቱን ካላወጀ፣ ለእነርሱ ያለውን ቁጣና ተቃውሞ ግልጽ ካላደረገ በስተቀር
እርሱ "ላ ኢላህ ኢለላህ" ብሎ ቢመሰክርም እንኳ ሙስሊም ነው ብለን ለመናገር መብት እንደሌለን እንገነዘባለን፡-
ሱረቱል አል-ሙጃደላ
58 ፡ 22
በአላህና በመጨረሻው
ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም
ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ …"3\
እንግዲህ ፋኢዝ
ሙስሊም ነው፤ ለእነዚህ አንቀጾች መለኮታዊ ቃልነት ጥርጣሬ የለውም፤ ሁልጊዜ በእያንዳንዱ የሰላ ወቅትም አብዝቶ እየደጋገመ በሚናገረው
ሸሀዳም ከኢማሙ ጋር ይስማማል፡፡ ከሙስሊም ውጭ ያሉትን "አውሊያ ( أوْلِيَاءََ )" ማድረግ እንደነርሱ መሆን እንደሆነና በአላህ
ላይ እንደ "ማመጽ" ከተቆጠረ፣ ቁጣንና ጠላትነትን አለማወጅና ግልጽ አለማድረግ ካለመስለም ጋር እኩል ከሆነ፣ ዐላማውን
በምን መልኩ ማሳካት ይችላል? የአላህን ቃል መታዘዝ አቁሞስ ከማያምኑት እንደ አንዱ መሆን እንዴት ይቻለዋል? ሙስሊሞቹንስ ወደዚህ
ሐሳብ መሣብ እንዴት ይቀልለታል? ጠል አምላክ እየተከተለ እና እያመነ መፈቃቀርን መስበክስ እንዴት ይቻላል? ገፊና አግላይ አምላክ፣
አግላይ ቃል፣ አግላይ ነቢይ፣ አግላይ ልብ ያለው ሰው እንዴት ተችሎት ተገለልኩ፣ ተገፋሁ ሊል ይችላል? ለዛም አይደል ተጀምሮ እስኪጨረስ
በደል ቆጣሪ ብዕሩ ይህንን መጽሐፍ ከትባ ያበረከተችልን፡፡
ዐላማ ሦስት፡-
2 ‘Awliya’ means:- helpers, friends, allies, patrons, protectors, legal
guardians (A word for word meaning of the Quran, vol 1, page 355)
3 Shaykh Muhammad Saeed al‐Qahtani, Al‐Wala’ wa’l‐Bara’ According to the
Aqeedah of the Salaf Part 1, page 16
"በአገር
በቀል ደረጃ ሙስሊም-ጠልነት መኖሩን ለማብራራት"
"አገር
በቀል ሙስሊም ጠልነት መኖሩን ለማብራራት" ነው ያለው? ይገርማል! ይህንን መጽሐፍ ባገኘሁ ቅጽበት አንድ ወዳጄ ጋር ተገናኘሁ፡፡
ስሜቱን ለመረዳት አስቤ መጽሐፉን አንሥቼ ርዕሱን አስነበብኩት፡፡ "ውሸት! አክራሪ-ጠልነት እንጂ ሙስሊም-ጠልነት ኢትዮጵያ
ውስጥ የለም" አለኝ፡፡ እኔም ልድገመው ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ሙስሊም-ጠልነት አለ’ ብሎ ማለት በአጭር ቃል እልፍ ጊዜ ሐሰት
ኩሸትም ነው፡፡ የለም፣ አልነበረም፣ አይኖርም፡፡ ፋኢዝ ጠልነቱ አለ ብሎ የሚያምን ከሆነም "ለምን?" ለሚለው ምላሽ
ያልሰጠ በመሆኑ መጽሓፉን የእንቶ ፈንቶ ወሬ ስብስብ አድርጎታል፡፡
ይቀጥላል…..
0 Comments