በናይጄሪያ በተከሰተ የላሳፊቨር ወረርሽኝ ከ 100በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

የAfrihealth TV ምስል
ላሳፊቨር የተባለው ወረርሽኝ የፈረንጆቹ 2020 ከገባ ወዲህ 586 ሰዎች በበሽታው የታመሙ ሲሆን ከነዚያም ውስጥ 103 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ኦሎሩኒምቤ ማሞራ ተናግረዋል፡፡
ላሳ ፌቨር ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት፣ የራስ ምታትና ከሰውነት ደም በትኩሳት አማካኝነት የሚወጣ ወረርሽኝ ሲሆን ቫይረሱ በናይጄሪያ ከተቀሰቀሰ 6 ሳምንታት አልፈዋል፡፡ ቫይረሱ እንስሳት ወለድ ሲሆን በምግብ እና የመገለግያ ቁሳቁሶችን በጋራ በመጠቀም ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል፡፡
በሽታው መድሃኒት እንዳለው የአለም ጤና ድርጅት ቢያረጋግጥም ቶሎ ካልታከሙት ግን ከበሽታው ለመዳን አዳጋች እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የአህጉሪቱ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ሀገር የሆነችው ናይጄሪያ መድሃኒቱን ማምረት የሚያስችል አምስት ትላልቅ ላብራቶሪዎች እንዳሏትም ተነግሯል፡፡
ላሳ ፌቨር ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው በጎርጎሮሳውያኑ 1969 በናይጄሪያዋ ላሳ ከተማ ሲሆን ወረርሽኙ በምዕራብ አፍሪካ ቀጠና ብቻ በየዓመቱ 5ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን ህይወት እንደሚቀጥፍ የተባባሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡

በሽታው ከኢቢላ እና ማርበርግ ከተባሉ በሽታዎች ጋር ተመሳሰይን ያለው ሲሆን ገዳይንቱ ግን አነስተኛ እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
ምንጭ- All African health news and WHO

Post a Comment

0 Comments