ከ 13 በላይ የሚሆኑ ሀገራት በኮሮናቫይረስ ስጋት የተነሳ ከደቡብ ኮሪያ የሚመጡ ሰዎች እንዳይገቡ ገደብ መጣላቸው ተገልጿል፡፡
እንደ ሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለፃ ከሆነ እስራኤልን ጨምሮ ፤ ባህሬን ፤ አሜሪካና እንግሊዝ ይህን እርምጃዎች ከወሰዱ ሀገራት መካከል ይገኙበታል ተብሏል፡፡
እስራኤል እንዳስታወቀችው ከደቡብ ኮሪያና ከጃፓን ለጉብኝት የሚመጡ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ ከሰኞ ጀምሮ የጉዞ እቀባ ተግባራዊ ማድረጓን የአገሪቱ ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡
ባህሬንም ከአርብ ጀምሮ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዷ ታውቋል፡፡
የእስራኤል ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው ቅዳሜ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ወደ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን የሚያደርጉትን በረራዎች እንደሚያግዱ ከተገለፀ በኋላ ነው፡፡
ደቡብ ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ሰው መሞቱን ባለፈው ሳምንት መግለጿ ይታወቃል፡፡
በደረሰ አማረ
የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም
ምንጭ፦ Ethio FM
0 Comments