
የቻይና ብሔራዊ ጠና ኮሚሽን እንዳረጋገጠው የሟቹ ቁጥር አሁን 908 ድርሷል ፡፡
በፊሊፒንስና በሆንግ ሆንግ ከተከሰተው ሞት ጋር ሲደምር ደግሞ የሟቾቹ ቁጥር አሁን 910 መድረሱ ተነግሯል፡፡
ሲኤን ኤ እንደዘገበው በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ወደ 40 ሺህ ያደገ ሲሆን አብዛኛው በቫይረሱ የተጠቁት ሰዎች ቻይናዊን ናቸው፡፡
ቻይና ውስጥ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ቁጥር አሁን ከ 37 ሺህ 200 በላይ ደርሷል፡፡
እ.ኤ.አ. በ 2002 እና በ 2003 ሳርስ የተባለው ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 774 ነበር።
ይህም እስካሁን ከነበሩ ተመሳሳይ ወረርሽኞች ብዙ ሰዎች የሞቱበት ወረርሽኝ ያደርገዋል ተብሏል።
በሌላ ዜና የአለም የጤና ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎችን ወደ ቻይና ልኳል፡፡
የድርጅቱ ዳሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት በቻይና ለተከሰተው ወረርሽን እገዛ የሚያደርግ የባለሙያ ቡድን መላኩን ተናግረዋል፡፡
የቫይረሱ መነሻ ነች በምትባለው ውሃን ግዛት በቀን 97 ሰዎች ህይወታቸውን በአንድ ቀን አጥተዋል፡፡
ምንጭ፦ ETHIO FM 107.8
0 Comments