በኢራን ስድስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸውን ተከትሎ ኢራቅ ከኢራን የሚመጡ መንገደኞችን አላስተናግድም ማለቷ ተሰምቷል።

የiran map ምስል ውጤት









በኢራን በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 28 ዜጎች ውስጥ ስድስቱ በዚሁ ቫይረስ ምክንያት መሞታቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች መዝናኛ ስፍራዎች ተዘግተዋል።
በቻይና ደግሞ 648 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮኖ ቫይረስ እንደተያዙም ተገልጿል።

ቫይረሱ ከተገኘባት ሁቤይ ግዛት ውጪ በቻይና ስርጭቱ ቢቀንስም በአለም ዙርያ ያለው መስፋፋት ግን አሳሳቢ ሆኗል ተብሏል፡፡

ዛሬ የቻይና ብሔራዊ የጤና ኮሚሽን እንዳሳወቀው በቫይረሱ አዲስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ትናንት ከነበረው 397 ወደ 648 ከፍ ብሏል፡፡

ባጠቃላይ አሁን በቻይና በኮሮኖ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ 76 ሺህ 936 ከፍ ብሏል፡፡ 

አሁን ላይ ከሁቤይ ግዛት ውጪ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 18 ሲሆኑ የሀገሪቱ የጤና ኮሚሽን ስለ በሽታው ሀገር አቀፍ መረጃ መስጠት ከጀመረ አንስቶ ትንሹ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡ 

በቫይረሱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር በ97 ከፍ ብሎ ወደ 2 ሺህ 442 የደረሰ ሲሆን ከ 97ቱ ሟቾች ውስጥ 1 ሰው ብቻ ነው ከሁቤይ ግዛት ውጪ የሞተው፡፡ 
እንደ ሪዮተርስ ዘገባ በሁቤይ ግዛት ከቫይረሱ ከሞቱት 96 ሰዎች ውስጥ 82ቱ በመዲናዋ ውሀን ከተማ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡ 

በኢራን ስድስት ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መሞታቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች መዝናኛ ስፍራዎችን ዘግታለች። 

አገሪቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው ከ28 በላይ ዜጎች ሳይታወቅ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን እና ከዚህ ወስጥ ሰድስቱ በመሞታቸው ምክንያት ነው። 

በተመሳሳይ በኢራን በተፈጠረው ሞት የተደናገጠችው ጎረቤቷ ኢራቅ በባግዳድ አውሮፕላን ማረፊያ ከኢራን የሚመጡ መንገደኞችን አንዳያስተናግዱ የአገሪቱ መንግስት ከደቂቃዎች በፊት ትዕዛዝ አስተላልፏል። 

ከአንድ ወር በፊት በቻይናዋ ሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ እንደተነሳ የተነገረለት ኮሮና ቫይረስ አሁን ላይ በቫይረሱ የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር በመቀነስ ላይ ቢሆንም በደቡብ ኮሪያ ሲኡል ከተማ ከሚገመተው በላይ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። 

በሔኖክ አስራት 
የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም 

ምንጭ- Ethio FM

Post a Comment

0 Comments