
በቻይና ተከስቶ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የኮሮናቫይረስ አልጄሪያ መግባቱ ታውቋል፡፡
አፍሪካዊቷ አገር አልጄሪያ የኮሮና ቫይረስ ከጣልያን ወደ አገሯ እንደተዛመተ አስታውቃለች።
የኮረና ቫይረስ በአውሮፓ ከጣልያን ባሻገር በኦስትሪያ፣ ክሮኤሺያ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጀርመን ሪፖርት ያደረጉ አገራት ሲሆኑ፤ ቫይረሱ ከጣሊያን በመጡ ሰዎች ወደ አገራቸው እንደገባ ገልፀዋል።
ኑሮውን በብራዚል ያደረገው ግለሰብም ቫይረሱን ከጣሊያን ወደ መኖሪያ አገሩ በመውሰድ በላቲን አሜሪካ የመጀመሪያው ኮሮናቫይረስ ሊመዘገብ ችሏል።
በጣሊያን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 300 የደረሱ ሲሆን 11 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል።
የጣሊያን ጎረቤት አገራት ከጣሊያን ጋር የሚያዋስናቸውን ድንበር ሊዘጉ ይችላሉ የሚል መላ ምት በስፋት ቢነገርም፤ የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ድንበርን ክፍት በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 78 ሺህ 064 ሲሆን በቻይና ብቻ ወደ 2715 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት መሞታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
0 Comments