በሲንጋፖር አንድ የሁለት ዓመት ህጻን በማይገመት መልኩ በኮሮና ቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ።

የsingapore ምስል ውጤት
የሁለት አመቷ ህጻን በቫይረሱ መያዟን የከተማዋ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ ጨቅላዋ ከጥር 30 ጀምሮ በቫይረሱ መያዟ እስኪረጋገጥ ድርስ በለይቶ ማቆያ ስፍራ እንድትቆይ ተደርጋ እንደነበር ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

የ37 አመቷ የዚች ህጻን ወላጅ እናት ወደ ቻይና የቅርብ የጉዞ ታሪክ የሌላት ሲሆን በአገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሌሎች ዜጎች ጋርም ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራትም ተብሏል።

ይሁንና ይህች ህጻን እንዴት በኮሮና ቫይረስ ተጠቃች ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት አለመቻሉ ቫይረሱ ሊተላለፍ የሚችልበት ሌላ አድል ይኖር ይሆን የሚል ጥያቄን አስነስቷል።

የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር እንዳሳወቀው በሲንጋፖር የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር አሁን ወደ 45 ከፍ ብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ መገኛ ከሆነችው የቻይናዋ ውሃን ክልል ውጪ አሁን በ26 ሀገራት ቫይረሱ መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡

ከሰአታት በፊት ጃፓን ፤ሲንጋፖር ፤ደቡብ ኮሪያ ፤ቬናም ፤የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እንዲሁም አሜሪካ አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን እንዳገኙ አሳውቀዋል፡፡

እስካሁን በአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ 43 ሺህ 105 ሰዎች መያዛቸው ሲነገር 1 ሺህ 18 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በቻይና ከ42 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲታመሙ ከ3 ሺህ 396 በላይ የሆኑ ታማሚዎች አገግመዋል፡፡1 ሺህ 16 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል፡፡

ከቻይና ውጪ እስካሁን 467 ተጠቂዎች በ27 ሀገራት የተገኙ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በፊሊፒንስ እና ሆንግ ኮንግ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ETHIO FM 107.8

Post a Comment

0 Comments