አገሪቱ በቀጣዩ ክረምት ልታስተናግድ የነበረዉን የኦሎምፒክ ዝግጅቷን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ልታራዝም አልያም ለመተዉ እንዳሰበች ተነግሯል፡፡
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ እንዳስታወቁት የቶክዮ ኦሎምፒክ ለጊዜዉ መራዘም አለበት ካልሆነም ሊሰረዝ ይገባል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመላዉ አለም እየተሰራጨ መምጥቱን የዘገበዉ አልጄዚራ በጃፓንም በቫይረሱ የሚያዙት ሰዎች ቁጥር እጨመረ ነዉ ተብሏል፡፡
ጃፓን በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ ዜጎችን በመርከብ ላይ እንዲቆዩ ማድረጓም የሚታወስ ነዉ፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ የዓለም ስጋት መሆኑን አውጆ የቫይረሱ ስርጭት በዚሁ ከቀጠለ ከዓለም ሀዝብ እስከ 70 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ሊያጠቃ ስለሚችል አገራት ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።
በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም
ምንጭ፦ Ethio FM
0 Comments