
ኮቪድ 19 የሚል ስያሜን ከዓለም የጤና ድርጅት ያገኘው ኮሮና ቫይረስ፣ ከደሴቶች ውጭ ባሉ የቻይና ግዛቶች ሰኞ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ 31 የሚሆኑ ሠዎች መሞታቸውም ተነገረ፡፡ በተጨማሪም 125 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውም ታውቋል፡፡
በሀገሪቱ ከትናንት በስቲያ 202 አዲስ ሠዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ ይህም ሠኞ እለት በቫይረሱ ከተያዙ ሠዎች ቁጥር ጋር ሲመዛዘን፣ በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ሆኖም ግን የሟቾች ቁጥር በ31 ከፍ ማለቱ ታውቋል፡፡
ሲጂቲኤን የሀገሪቱን ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በሀገሪቱ ራስ ገዝ አስተዳደር በሆኑት በሆንግ ኮንግ 100 ሠዎች፣ ማካዋ 10 ሠዎችና የቻይና ክልል በሚትገኘው ታይዋን 41 ሠዎች ትናንት ብቻ በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡
በቻይና እስካሁን 80 ሽህ 151 ሠዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ 2 ሽህ 943 ሠዎች መሞታቸውንም ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡ በመላው ዓለም በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 90 ሽህ 933 የደረሰ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 3 ሽህ 119 ደርሷል፡፡
እስካሁን በቫይረሱ ከቻይና ቀጥላ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቃችው ኢራን ስትሆን፤ ኮሮና በአፍሪካም ጥቂት በማይባሉ ሀገራት ተከስቷል፡፡ ግብፅ፣ አልጀሪያ፣ ናይጀሪያና ሴኔጋል በቫይረሱ የተያዙ ሠዎች መገኘታቸው ታውቋል፡፡
0 Comments