የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ስፔን እና ፈረንሳይ ጠንከር ያለ እገዳ አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኮሮናቫይረስ  ስርጭትን ለመግታት  ስፔን እና ፈረንሳይ ጠንከር ያለ እገዳ አስተላለፉ
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ ስፔን ሰዎች ምግብና መድሃኒት ለመግዛት ወይም ወደ ሥራ ቦታ ለመሄድ ካልሆነ በስተቀር ከቤት እንዳይወጡ ከልክላለች።
በስፔን 191 ሰዎች በበሽታው ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን፥ ከጣሊያን በመቀጠል በቫይረሱ በከፍተኛ የተጠቃች አውሮፓዊት አገር ሆናለች።
ሌላኛዋ እና በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ እየተጠቃች የምትገኘው ፈረንሳይ 91 ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ ለህልፈት ተዳርገዋል።
በዚህም ካፌዎችን፣ ሬስቶራንቶችን፣ ሲኒማዎችን እና በርካታ ሱቆችን ዘግታለች።
ከቻይና ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ ዜጎቿ የሞቱባት ጣሊያን ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ዜጎቿ ከቤት እንዳይወጡ አግዳለች።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሁን ከየትኛውም አካባቢ በበለጠ አውሮፓ የወረርሽኙ የመስፋፋፊያ ቦታ መሆኗን ገልፀው አገራት ጠንካራ ርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቀዋል።
 ምንጭ፡-ቢቢሲ.

Post a Comment

0 Comments