የጀርመኟ መራሂተ መንግሥት ወደ ለይቶ ማቆያ ተወሰዱ፡፡

የAmhara Mass Media Agency ምስል


የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው በመረጋገጡ ወደለይቶ ሕክምና መስጫ መግባታቸው ተሰማ፡፡
የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል የኮሮኔቫ ቫይረስ ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ በሽታው እንዳለባቸው በመረጋገጡ በለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባታቸው ታውቋል፡፡
ቻንስለሯ ወደ ለይቶ ማቆያ ከመወሰዳቸው አስቀድሞ ትናንት እሑድ ባካሄዱት ኮንፈረንስ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ አዳዲስ ርምጃዎችን ይፋ እንዳደረጉ ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል፡፡
ቃል አቀባይ ስቴፍን ሴይበርት እንዳሉት የ65 ዓመቷ ቻንስለር ሜርክል በቀጣዮቹ ቀናትም አስፈላጊው ምርመራ የሚደረግላቸው ይናል፤ ሥራቸውንም በቤታቸው ሆነው እንደሚከውኑ ነው የተገለጸው፡፡
ጀርመን የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ከሁለት በላይ ሆኖ መቀመጥም ሆነ መንቀሳቀስ እንዳይቻል እገዳ አስተላልፋለች፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ

Post a Comment

0 Comments