
የኮሮና ቫይረስ በቻይና ከመከሰቱ በፊት በአሜሪካ በቫይረሱ ተጠቅተው የሞቱ መኖራቸው ተረጋገጠ። ይህንን ያረጋገጡት የአሜሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማዕከል (CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድ ናቸው። ዳይሬክተሩ እንዳሉት ይህ የታወቀው በኢንፍሉዌንዛ በሞቱ ሰዎች ላይ በድጋሚ በተደረገ ምርመራ ነው።
በተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎች በተደጋጋሚ ሲነገር እንደቆየው የኮሮና ቫይረስ የተጀመረው በቻይና ዉሃን ከተማ እንደሆነ ነበር። ለበሽታው መነሻም የተለያዩ መላምቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። አንዱ መላምት ከእንስሳት ወደ ሰው ነው የተላለፈው የሚል ነው።
ለዚህም እንደ ማስረጃነት የሚቀርበው ቻይናውያኑ የሚበሉት፣ “እርጥብ ገበያ” (wet market) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከባህር የሚገኙ ማንኛውም የአሣ ዝርያ እስከ የሌሊት ወፍ፣ እባብ፣ ውሻ፣ ሸለምጥማጥ፣ የዱር ድመት፣ ዓይጠመጎጥ፣ ወዘተ እየታረዱና እየተከተፉ የሚሸጡበት በደም፣ በፈርስና በመሳሰሉ የአራዊቱ ፍሳሾች የተበከለ በመሆኑና በሽታው የተነሳው እነዚህን እንስሳት ከመብላት ነው የሚል ነው።
ሌላኛው መላምት ደግሞ በቻይና ዉሃን ከተማ ድብቅ የባዮሎጂካል መሣሪያ ማምረቻ ጋር የተያያዝ ነው። መላምቱ፣ በፋብሪካው የኮሮና ቫይረስ ለማምረት ሙከራ ሲደረግ ስለነበር ቫይረሱ ከዚያ አፈትልኮ የወጣ ነው የሚል ነው። ይህም በሽታው የተዛመተው ከእንስሳት ወደ ሰው ሳይሆን፣ በቅድሚያ ሰዎች ተይዘው ነው ወደ እንስሳቱ የተዛመተው ለሚለው መከራከሪያ እንደ ማስረጃ ይቀርባል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ መላምቶች የሚቀርቡ ሲሆን በሚዲያ ብዙም ትኩረት ሳያገኝ የታለፈው ጉዳይ ግን በሽታው በቻይና ከመከሰቱ በፊት በአሜሪካ የኢንፍሉዌንዛ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የሞቱ ሰዎች እንዳሉ መገለጹ ነው።
ይህ የሚዲያ አውታሮች በሚገባው መጠን ጆሮ የከለከሉት ወይም እንደ ጉዳዩ ግዝፈት ሰፊ ሽፋንና ትኩረት ያልሰጡት ጉዳይ ይፋ የሆነው የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ማርች ፲፩ በተወካዮች ምክርቤት ለውይይት ተጠርተው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነበር።
የምክርቤቱ ኦቨርሳይት ኮሚቴ (Oversight Committee) የማዕከሉን (CDC) ዳይሬክተር ዶ/ር ሮበርት ሬድፊልድን ጠርቶ ባወያየበት ወቅት ጥያቄዎችን አቅርቦላቸው ነበር። በውይይቱ ወቅት ሃርሊ ሮውዳ የተባሉ የካሊፎርኒያ እንደራሴ ባለፉት ወራት አንዳንድ ኢንፍሉዌንዛ ወይም ፍሉ በሽተኞች በርግጥ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እንደነበሩና ምናልባትም በትክክል ሳይመረመሩ እንደቀሩ ለዳይሬክተሩ ጥያቄ ያቀርባሉ።
ዳይሬክተሩ ሲመልሱም “ባለው መደበኛ አሠራር የመጀመሪያው ምርመራ የኢንፍሉዌንዛ ምርመራ ማድረግ ነው፤ በኢንፍሉዌንዛ ከተያዙ ፖዘቲቭ ይሆናሉ (ወይም ኢንፍሉዌንዛ ይዟቸዋል ይባላል)” ብለዋል።
እንደራሴው በመቀጠልም ባለፉት ወራት ኮሮና ይፋ ከመሆኑ በፊት በኢንፍሉዌንዛ የሞቱትን አሁን ከሞቱ በኋላ ኮሮና እንደነበረባቸው ምርመራ ስለመደረጉ ይጠይቃሉ።
ዳይሬክተሩ ሲመልሱም “በሁሉም ከተማ፤ በሁሉም ጠቅላይ ግዛት እና በሁሉም ሆስፒታል ባይተገበርም ማዕከላችን በሳምባ ምች የሞቱ ሰዎችን የሚከታተልበት ስልት አለው” ይላሉ።
ይህንን ምላሽ ተከትለው እንደራሴው እንዲህ በማለት ሌላ ጥያቄ ያቀርባሉ፤ “ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች በአሜሪካ በኢንፍሉዌንዛ የሞቱ ናቸው ያልናቸው እንደተባለው ሳይሆን በርግጥም የሞቱት በኮሮና ቫይረስ ነው ሊባል ይችላል” በማለት ጥያቄያቸውን አጠናክረው ያቀርባሉ።
ዳይሬክተሩ ሲመልሱም፤ “አንዳንድ ኬዞች በርግጥ በዚያ መልኩ በአሜሪካ ለመከሰታቸው በምርመራ ታውቋል” ብለዋል።
በአሜሪካ የኢንፍሉዌንዛ (የፍሉ) ወቅት የሚባለው የሚጀምረው በኦክቶበር (ጥቅምት) አካባቢ እንደሆነና ዲሴምበር (ታህሣሥ) ላይ ከፍ እያለ መጥቶ እስከ ማርች (መጋቢት) ድረስ አንዳንዴም እስከ ሜይ (ግንቦት) እንደሚዘልቅ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከሉ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ከሴፕቴምበር ፳፱ ጀምሮ እስከ ፌብሩዋሪ ፲፱ ባለው ጊዜ ውስጥ 250,000 አሜሪካውያን ከፍሉ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል ገብተው እንደነበርና ከእነዚህም 14,000 በዚህ የኢንፍሉዌንዛ ወቅት መሞታቸውን የኢንፌክሽንና የአለርጂ በሽታዎች ብሔራዊ ማዕከል አስታውቆ ነበር። ከሞቱት ቁጥር ውስጥ ስንቱ በኮሮና ቫይረስ እንደሞቱ በውል አልታወቀም።
እንደራሴው አጥብቀው ላቀረቡት ጥያቄ የማዕከሉ ዳይሬክተር የሰጡት ምላሽም ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። ዳይሬክተሩ ያሉት በመደበኛ ኢንፍሉዌንዛ ሞቱ ከተባሉት ውስጥ ከሞት በኋላ (posthumous) በተደረገ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ታውቋል የሚለውን ነው ያረጋገጡት።
ጉዳዩ ይህ ከሆነ በቻይና ዉሃን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ከመሞታቸው በፊት አሜሪካ ውስጥ ሞተዋል የሚለውን የሚያረጋግጥ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ በሽታው አስቀድሞ አሜሪካ ተከስቶ ነበር ወደሚለው ድምዳሜ ይወስዳል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በቻይና እና ጃፓን የሚገኙ የሚዲያ ውጤቶች እያነሱ ያለው ጥያቄ በአሜሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ተጠቂ የሞተው መቼ ነው? እስካሁን ስንት ሞተዋል? በሽታው በአሜሪካ የጀመረው መቼ ነው? ወዘተ የሚሉ ሆነዋል። እነሱ ይህንን ቢሉም ራሳቸው የአሜሪካን ሚዲያ አውታሮች ግን ይህንን ታላቅ ጉዳይ ዝም ማለታቸው ለምን ይሆን የሚለው ግን ከቫይረሱ የመከላከያ ክትባት ባልተናነሰ ምክንያቱ የመታወቁ ጉዳይ ልዩ ምርምር ያሻዋል።
0 Comments