ኮሮናን የሚመለከቱ አዳዲስ መረጃዎች


Symbolbild Corona-Virus (Reuters/D. Ruvic)

•    ኢራን ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። በ 24 ሰዓታት ውስጥ የሟቾች ቁጥር ከ 724 ወደ 853 ከፍ ብሏል ፡፡ 
•    ኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋሲ ስርጭትን ለመግታት ለ 15 ቀናት ትምህርት ቤቶችን መዝጋቷን  ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።
•    በኢትዮጵያ በሶስት ቀናት ውስጥ በኮሮና ተሕዋሲ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ደረሰ። አምስተኛው ሰው በተሕዋሲው መያዛቸው በትናንትናው ዕለት መረጋገጡን የጤና ምኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
•    ኢትዮጵያ ለሚቀጥሉት አስራ አምስት ቀናት ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎችን ከለከለች። የአገሪቱ 45 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ባሉበት ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ተብሏል።
•    ጀርመን ከዛሬ ጠዋት አንስቶ የኮሮና ተህዋሲ ስርጭትን በመስጋት የሚያዋስንዋትን የአምስት ሃገር ድንበሮች ዘጋች።

Post a Comment

0 Comments