ዶ/ር ቴድሮስ የኮሮናቫይረስ አስደንጋጭ የስርጭት ፍጥነትን ይፋ አደረጉ





የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
Image caption: የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮናቫይረስ ስርጭት ፍጥነት እጅጉን እየጨመረ መሆኑን ተናገሩ።
ዶ/ር ቴድሮስ ከደቂቃዎች በፊት በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ላይ፤ “በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ሪፖርት ከተደረገ በኋላ፤ የመጀመሪያዎቹ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 67 ቀናት ወስደዋል” ብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው ጨምረውም፡ “ቀጣዮቹ 100ሺህ ሰዎች የተያዙት በ11 ቀናት ውስጥ ሲሆን፤ ሦስተኛ 100ሺህ ሰዎች የተያዙት ግን በ4 ቀናት ውስጥ ነው” በማለት የቫይረሱን ስርጭት ፍጥነት አመላክተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሁን ካለውም ሊከፋ እንደሚችል አስጠነቀቀ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ300 ሺህ በላይ መድረሱን ተከትሎ ቁጥሩ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በ67 ቀናት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ሁለተኛው 100 ሺህ ደግሞ በ11 ቀናት ውስጥ የተመዘገበ ሲሆን ሶስተኛው 100 ሺህ በ4 ቀናት ብቻ ተመዝግቧል፡፡

ይህም ቫይረሱ በጣም በጥቂት ቀናት ውስጥ የመዛመት እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ እና ከዚህ በላይ የከፉ ቁጥሮች ሊመዘገቡ እንደሚችሉ ድርጀቱ አስታውቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር እንጂ አሁንም ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ተስፋ አለን ብለዋል፡፡

አገራት ጠንካራ የፍተሻ ልምድን ካሳደጉ እና የፍተሸ መሳሪያዎችን በአግባቡ ተጠቅመው ምርመራ ካደረጉ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም ቫይረሱን ተዋግቶ ለማሸነፍ ሁሉም ንክኪዎችን ማስወገድ፣ የእጁን ንፅህናን በአግባቡ መጠበቅ እንዲሁም በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችን ቶሎ ወደ ለይቶ ማቆያ ክፍል ማስገባት እና በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚያፈልግ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Post a Comment

0 Comments