የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች መከሰቱ ተሰማ



በአሜሪካ ሁሉም ግዛቶች ኮሮና ወረርሽን ተከስቷል


የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ የከተማቸውን 8.5ሚሊየን ሕዝብ በቤታችሁ ከትታችሁ ተቀመጡ ይላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው
የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ የከተማቸውን 8.5 ሚሊየን ሕዝብ በቤታችሁ ከትታችሁ ተቀመጡ ይላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው
Image caption: የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ የከተማቸውን 8.5 ሚሊየን ሕዝብ በቤታችሁ ከትታችሁ ተቀመጡ ይላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች መስፋፋቱ ተሰማ።
የዌስት ቨርጂኒያ አገረ ገዢ በትናንትናው ዕለት በግዛታቸው ስለተገኘ አንድ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው መግለጫ ሲሰጡ “እንደሚመጣ እናውቀው ነበር” ብለዋል።
ኒውዮር ልክ እንደ ሳንፍራንሲስኮዋ ቤይ ኤሪያ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴዎችን ለማቆም እያሰበች መሆኑም ተነግሯል።
በአሜሪካ እስካሁን ድረስ 108 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሲሆን 6300 ሰዎች ደግሞ መያዛቸው ተረጋግጧል።
እስካሁን ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ 200ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 8ሺህ ያህል ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በተያያዘ ዜና ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ዓለማችን ውድ ከተሞች በጎብኚ ድርቅ ተመትተዋል።
ሆንግ ኮንግ፣ ሲንጋፖር እና ኦሳካ የዓለማችን ውድ ከተሞች ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።
ይህ ግን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የሚቀጥል አልሆነም።
ከፍተኛ ገቢያቸውን ከቱሪዝም ያገኙ የነበሩ እነዚህ ከተሞች ከወረርሽኙ በኋላ ርካሽ እየሆኑ መጥተዋል ይላል።
በአንድ ወቅት የማታንቀላፋዋ የተባለችው ኒው ዩርክ የሚንቀሳቀስ አንድም ሰው የማይታይባት እየሆነች ነው ተብሏል።

Post a Comment

0 Comments