
ቻይና የኮሮና ቫይረስ በሀገሬ የተቀሰቀሰው በአሜሪካ ወታደራዊ ሴራ ሊሆን ይችላል አለች፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በትዊተር ገጻቸው እንዳሉት በሁዋን ከተማ ገዳዩ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው በአንዳች የአሜሪካ ወታደራዊ ሴራ ነው ብለዋል፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዛሆ ሊያን እንዳሉት አሜሪካ በቫይረሱ የተጠቃችበትን ሁኔታና ከተያዙት ሰዎች አንፃር ሲታይ ጣታችንን ወደ ፔንታጎን እንድንቀስር ያደርጋል ብለዋል።
ሌላው ቀርቶ የአሜሪካ የማግለያ ሆስፒታሎች ስያሜ በራሱ የሚጠቁመው ነገር አለ ነው የሚሉት ቃል አቀባዩ፡፡
ከቀናት በፊትም በደቡብ አፍሪካ የቻይናው አምባሳደር ቻይና ቫይረሱን ሆን ብላ አሰራጭታለች መባሉን አስተባብለዋል፡፡
ይሁንና የአሜሪካው ሮክስ ኒውስ እንደሚለው ቻይና ቫይረሱን አሜሪካ ናት የምታሰራጨው የሚለው የአለማቀፍ ዘመቻዋ አካል ነው ብሏል፡
0 Comments