በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተከናወኑ ተግባራት ጊዜ ጠብቀው እየወጡ ነው። ዛሬ ከወደሮም የተሰማው ዜና በወቅቱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒዩስ 12ኛ በአይሁዳውያን ላይ ሆሎኮስት በመባል የሚታወቀው እልቂት ሲፈፀም ዝምታን ለምን መረጡ የሚለውን የሚያሳይ መረጃ ቫሪካን ይፋ ልታደርግ መሆኑን ያመለክታል።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የተከናወኑ ተግባራት ጊዜ ጠብቀው እየወጡ ነው። ዛሬ ከወደሮም የተሰማው ዜና በወቅቱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ፒዩስ 12ኛ በአይሁዳውያን ላይ ሆሎኮስት በመባል የሚታወቀው እልቂት ሲፈፀም ዝምታን ለምን መረጡ የሚለውን የሚያሳይ መረጃ ቫሪካን ይፋ ልታደርግ መሆኑን ያመለክታል። ፒዩስ 12ኛ ከጎርጎሪዮሳዊው 1939 እስከ 1958 በመንበሩ ቆይተዋል። የሰነዶቹ ቆጠራ 14 ዓመታትን የወሰደ ሲሆን 200 የሚሆኑ ተመራማሪዎች ይህን መረጃ የያዙ ሰነዶችን ለማገላበጥ እና ለመመርመር ጥያቄ አቅርበዋል። በምርምሩ ለመሳተፍ ወደ ሮም ካመሩት መካከል ጀርመናዊው የሃይማኖት ታሪክ ተመራማሪ ሁበር ቮልፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከናዚዎች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በተመለከተ የጠለቀ እውቀት እንዳላቸው ነው የተነገረው። እሳቸው እንደሚሉትም ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዓይን እና ጆሮ የነበሩት 70 አምባሳደሮቻቸው የስድስት ሚሊየኑን አይሁዳውያን እልቂት በተመለከተ በማስታወሻቸው ምን ጽፈው እንደሆነ ለማየት ጓጉተዋል። በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት የጣሊያን የመከላከያ ሚኒስትር የፋሺስት ጣሊያን ሠራዊት በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሁለት ሺህ ገደማ መነኮሳትን የጨፈጨፉበትን ስፍራ እንደሚጎበኙ መናገራቸው ተሰምቷል። ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ጣሊያን በጎርጎሪዮሳዊው 1937 የጦር ወንጀል መፈፀሟን የሚያመለክት መጽሐፍ ሲመረቅ ነው።
ተኽለእግዚ ገብረ ኢየሱስ
ሸዋዬ ለገሠ
ምንጭ፦ DW Amharic
0 Comments