በቻይና የኮሮና ቫይረስ ለይቶ ማከሚያ የነበረው ሆቴል ተደረመሰ በቻይና የኮሮና ቫይረስ ለይቶ ማከሚያ የነበረ ሆቴል ህንጻ በመደርመሱ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 29 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ ተነግሯል።
ሆቴሉ በትላንትናው ዕለት የተደረመሰ ሲሆን፤ የአደጋው መንስኤ አለመታወቁም ተገልጿል በሆቴሉ ውስጥ ከነበሩት 71 ሰዎች 38ቱን ማውጣት መቻሉን የአገሪቱ አደጋ መከላከል አስተዳደር ሚኒስትር አስታውቋል።
የቻይና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀው ሆቴሉ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ህመምተኞች ጋር ቅርብ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች ላይ ክትትል የሚደረግበት ማዕከል ነበር በቻይና በኮሮና ቫይረስ በየዕለቱ ከሚያዙት 99 ሰዎች አርብ እለት ወደ 44 መቀነሱ ተገልጿል።
0 Comments