ከሰሞኑ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 13 ሰዎች በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና ከእነዚህ ውስጥም ሁለቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አስታውቆ ነበር
የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ኢትጵያውያን ወደ ሀገራቸው የቅርብ ጊዜ የጉዞ ታሪክ እንዳላቸው ከሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር መረጃዎችን ሲያሰብባስብ ነበር።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ረፋድ ላይ በትውተር ገፃቸው እንዳረጋገጡትም ሁለቱ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት መኖራቸው እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

0 Comments