የኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ የተፈበረከ ሊሆን እንደሚችል የኢራን ባለስልጠናት ገለፁ




የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በአሜሪካ የተፈበረከ ወይም ከዚህ ሁሉ እልቂት ጀርባ አሜሪካ ዋናዋ ተዋናይ ልትሆን እንደምትችል የኢራኑ ብሔራዊ አብዮት ጠባቂ ሃይል ኃላፊ መግለፃቸው ተጠቆመ።

'አርቲ' (RT) የተባለው የሩሲያ የዜና ተቋም፣ የኢራን ባለስልጣናትን ፍንጭ አድርጎ እንደዘገበው የኮሮና ቫይረስ አሜሪካ፣ ኢራንና ቻይናን ለማጥፋት የፈጠረችው በሽታ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳላቸው ዘግቧል። የኢራን ባለስልጣናት ጉዳዩን ይፋ ለማድረግ ተጨባጭ ማስረጃ በማፈላለግ ላይ መሆናቸውንም ዘገባው አስታውቋል፡፡

የኢራኑ ብሔራዊ አብዮት ጠባቂ ኃይል ኃላፊ ሁሴን ሳላም እንደገለጹት ኢራን በቫይረሱ ሳቢያ ለሚደርስባት እንግልትና ስቃይ አትሸነፍም ያሉ ሲሆን የአሜሪካን ሴራ የሚያጋልጥ መረጃ እጃችን ሲገባ የበደሏን አፀፋ እንመልሳለን ሲሉም ተደምጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረሱን ትክክለኛ መነሻ ምክንያት በተመለከተ የደረሰበት ድምዳሜ የለም።

Post a Comment

0 Comments