በኢትዮጵ ቆይታ አድርጎ ወደ ዋሸንግተን የተመለሰ አንድ የአሜሪካ የባህር ሃይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ተገልጿል።


በኢትዮጵ ቆይታ አድርጎ ወደ ዋሸንግተን የተመለሰ አንድ የአሜሪካ የባህር ሃይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ተገልጿል።

ወታደሩ በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ በሚገኘው የቤልቪየር ጣቢያ ምርመራ ሲደረግለት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ቶክ ኒወስ የተሰኘ የሚዲያ ተቋም የአሜሪካ መከላከያን መግለጫ ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።

እንደ ኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ለመኖሩ የሚሳይ ምንም ሪፖርት የለም፡፡

ኢትዮጵያ በጣም ቀልጣፋ ከሚባሉት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎች አንዷ በመሆኗ በ COVID-19 ሊከሰት የሚችል ወረርሽኝ ቀድማ ለመከላከል ዝግጁ መሆኗን እና ይህንንም እየተገበረች መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

በኮሮና ቫይረሱ የተያዘው ግለሰብም ቤልቪየር በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት መሆኑ ተጠቅሷል።

ይህ ወታደር ከኢትዮጵያ ተነስቶ ዋሸንገተን ከመድረሱ በፊት ደቡብ ኮሪያ እና ጣሊያን ላይ ቆይታ እንደነበረው የተገለጸ ሲሆን ቫይረሱ በነዚህ አገራት እያለ ሳያጠቃው እንዳልቀረ ተገምቷል።

በትግስት ዘላለም

መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም

ምንጭ፦ Ethio FM

Post a Comment

0 Comments