የቢልጌትስ ፋውንዴሽን ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ የሚውል የ200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተሰማ


Baby with measles (or rubella)
ፋውንዴሽኑ የ200 ሚሊዮን የብድር ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡በሌላ ወሬ ቶታል ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የ17 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግሯል፡፡ከድጋፍ ዓይነቶቹ መካከልም አንድ መቶ ሺ ሳኒታይዘር ፣ ለአንቡላንሶችና ለህብተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መኪኖች የአንድ ሚሊዮን ብር ነፃ የነዳጅ መሙያ ካርድ እንዲሁም የእጅ መታጠቢያ መሳሪያዎች እንደሚገኙበት ኩባንያው ለሸገር ተናግሯል፡፡

በተመሳሳይ ወሬ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ ኮካኮላ ካምፓኒ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል 5.5 ሚሊዮን ብር ሰጠ፡፡ኮካ ኮላ ካምፓኒ ግምቱ 5.5 ሚሊዮን ብር የሆነ የገንዘብ ድጋፍ እና የዓይነት ድጋፍ ለተለያዩ የመንግስትና ግብረ ሰናይ ድርጀቶች መስጠቱን ሰምተናል፡፡ኩባንያው 3 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍን ያደረገው ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሲሆን ቀሪው የሳኒታይዘርና ምግብ ድጋፍ ለአዲስ አበባ እንዲሁም ኩባንያው ፋብሪካዎች ለሚገኙባቸው ባህርዳር እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች መሆኑንን ለሸገር ተናግሯል፡

Post a Comment

0 Comments