🇮🇷 ኢራን ከእስልምና እየወጣች ነው! 🇮🇷



በአለማችን አሉ ከሚባሉ እስላማዊ ሀገራት አንዷ ኢራን ናት። በመካከለኛው ምስራቅ እና በሙስሊሙ አለም ዘንድም ተጽዕኖ አላቸው ከሚባሉ ሀገራት ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2011 ዓመተ ምህርተ በተደረገው ጥናት፥ የኢራን ህዝብ ከዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት (99.5%) በላይ ሙስሊም እንደነበር ተዘግቧል።

ነገር ግን ይህ ዘገባ የኢራን መንግስት ለሀይማኖት አልበኝነት እና ለሌሎች እምነቶች ያለውን ጠላትነት የደበቀ ነው። በተጨማሪም፥ ህዝቡ ሾሾ ለሆኑ ጉዳዮች በቀጥታ መልስ መስጠት ስለማይችል ቃለ መጠይቆች የሚደረጉት በኢንተርኔት (Digital survey) ነው።

በዚሁ መንገድም፤ ኢራናውያን ሾለ ሀይማኖት ያላቸውን አስተያየት በገፍ ሊባል በሚችል መልኩ ሰጥተዋል። ውጤቱም ብዙዎችን እያስገረመ ይገኛል

♦ ይኸውም፥ በሀገሪቱ ውስጥ በግልፅ ራሳቸውን ሙስሊም በማለት የገለጹት አርባ ፐርሰንቱ (40%) ብቻ መሆናቸው ነው!

ይህ ማለት በሀገሪቱ ውስጥ ሙስሊም ያልሆነው ህዝብ ቁጥር፥ ከሙስሊሙ ይበልጣል ማለት ነው። ቁጥሮቹን እነሆ:-

1. ሺዓ ሙስሊም - 32.2%
2. እምነት አልባ - 22.2%
3. አቲይስት - 8.8%
4. ዞሮአስትሪያን - 7.7%
5. በመንፈሳዊው አለም የሚያምን -7.1%
6. አግኖስቲክ - 5.8%
7. ሱኒ ሙስሊም - 5%
8. ሱፊ ሙስሊም - 3.2%
9. ሂውማኒስት - 2.7%
10. ክርስቲያን - 1.5%
11. ይሁዲ - 0.1%
12. ሌሎች - 3.3%

የሀገሪቱ መንግስት ኢራንን እንደ ሺዓ ሙስሊም ሀገር ለመሳል ቢሞክርም፥ የሀገሪቱ ሰላሳ ሁለት ፐርሰንት (32%) ህዝብ ብቻ ነው ያንን የእስልምና አንጃ የሚከተለው። በመላው እስልምናም ብንሄድ እንኳ ወደ አርባ ፐርሰንቱ ብቻ ነው ሙስሊም። ይህ ማለት ኢራን እስላማዊ ሀገር አይደለችም ማለት ነው

ለዚህም በዋነኝነት መንስኤ ተብለው የተቀመጡት 1) ከእስላማዊው አብዮት በኋላ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው የእውቀት መጨመር (increase the rate of literacy) እና በኢንተርኔት ምክንያት ከተቀረው አለም ጋር ያለው ግንኙነት መጨመር ነው።

በ2020 ስልሳ ፐርሰንቱ የኢራን ህዝብ (60%) ብቻ ነው የረመዳንን ጾም የጾመው። ይህ በ1975 ዓ.ም ከነበረው የሰማንያ ፐርሰንት (80%) አሃዝ ጋር ሲተያይ እጅግ ሰፊ የሚባል ልዩነት ነው

✒ ነገር ግን አብዛኞቹ እስልምናን ለቀው የወጡ አራናዊያን በይፋ ከእስልምና መውጣታቸውን አይናገሩም። ምክንያቱም ኢራን በሸሪዓ ህግ የምትተዳደር እስላማዊት ሀገር ናት

በሸሪዓው ደግሞ አንድ ሙስሊም ከእምነቱ ከወጣ ቅጣቱ ግድያ ነው። ይህ በብዙ ኢስናዶች (የዘገባ ሰንሰለቶች) የተዘገበ የመሐመድ ትዕዛዝ ነው።

✏ " The Messenger of Allah said: Whoever changes his religion, #kill him. "

[ Sunan an-Nasa'i 4061 ]

✏ " የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦ ማንም ሀይማኖቱን ከቀየረ፥ #ግደሉት "

[ ሱናን አን-ናሳይ 4061 ]

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ (እንደሚቀጥልም ይጠበቃል) ሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ከእስልምና ልትወጣ እንደምትችል ተገልጿል።

🚩 የኢራን ህዝብ ሙሉ በሙሉ ከእስልምና ነጻ ወጥቶ ወደ ክርስቶስ ብርሃን ይመጣ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው!

https://theconversation.com/irans-secular-shift-new-survey-reveals-huge-changes-in-religious-beliefs-145253

Post a Comment

0 Comments