የሄርቴጂ ፋውንዴሽን ባጠናው ጥናት ፥ ሃይማኖታዊ እና ሃይማኖታዊ ባልሆኑ አሜሪካኖች መካከል ያለውን ልዩነት አስመልክቶ እነዚህን ውጤቶች አግኝተዋል፤
1) ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን የሚጠብቁ ሰዎች ከድህነት የመውጣት ዕድላቸው ሃይማኖት ከሌላቸው ወይም ኖሯቸው ግን ሥርዓቱን ከማይጠብቁ በጣም ከፍ ብሎ ያገኙ ሲሆን፣ በተለይ በinner circle of the city በሚባለው እና ድህነት ሰፍኖ ባለበት ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ከድህነት ለመውጣታቸው ቤተክርስቲያን መሄዳቸው ትልቅ ሚና ነበረው።
2) ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ከማይሄዱ ሰዎች በላይ የማግባት ዕድላቸው ከፍ ሲል፤ የመፋታት ወይም ሳያገቡ የመኖር ቁጥሩ ቤተክርስቲያን ከማይሄዱ ሰዎች በጣም ያነሰ ነው። በትዳር ውስጥ ባሉትም ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች በትዳራቸው ከማይሄዱ ሰዎች በላይ ደስተኞች ናቸው።
3) ቤተክርስቲያን አብዝተው በሚሄዱ ሰዎች ከብዙ ማህበረሰባዊ ጠንቆች የተጠበቁ ነበሩ፤ ለምሳሌ ሱስ፣ ራስን የማጥፋት ዝንባሌ፣ ከትዳር ውጪ የመውለድ፣ ወንጀል እና ፍቺ በጣም ዝቅተኛ ነበር።
4) ቤተክርስቲያን አብዝተው የሚሄዱ ሰዎች ጭንቀት እና ዝቅተኛ የሆነ ለራስ ግምት እምብዛም ያልታየባቸው ሲሆን፣ የትዳር እና የቤተሰብ ደስታቸው ደግሞ ከፍተኛ ነበር።
5) ከተሰበረ ቤተሰብ፣ ከፈረሰ ትዳር፣ ከአልኮል ሱስ እና ከሌሎች ሱሶች ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች ቶሎ መገላገል እና መውጣት ችለዋል።
6) ቤተክርስቲያን አብዝተው የሚሄዱ አሜሪካኖች የዕድሜ ጣሪያቸው ከፍ ያለ፣ ጤናቸው ከማይሄዱ ሰዎች የተሻለ እና ከገዳይ በሽታ ብዙዎቹ የተጠበቁ ነበሩ።
ምንጭ: Book titled – Alchemy by Rory Sutherland
ለብዙ የተማሩ እና ዘመናዊ ሰዎች ሃይማኖት እና ቤተክርስቲያን መሄድ የኋላቀርነት ምልክት ነው። በሚገርም ሁኔታ እነዚህ ሰዎች ግን ከጭንቀት እና ከሱስ ለመውጣት ለሳይካትሪስቶች እና ለብዙ ዓይነት አማካሪዎች ለዘመናት ገንዘባቸውን ለመጨፍጨፍ ፍቃደኛ ናቸው። መጨረሻ ላይ እነዚህ ባለሙያዎች የሚነግሯቸው ግን ሕይወት “ከሥራ በላይ ነው” የሚል ነው። “ከአንተ በላይ የምትኖርለት ነገር ፈልግ፣ የበጎ አገልግሎት ቢያንስ በሳምንት አንዴ ጀምር፣ ማህበራዊ ሕይወት ይኑርህ፣ ዮጋ ወይም ሳልሳ ዳንስ ጀምር ምክንያቱም ዘላቂ መፍትሔው እሱ ነው” ይሉአቸዎል። የትኛው ሎጂክ እና ሲሎጂዝም እነዚህን ምክር እንዲቀበሉ እንዳደረጋቸው ባላውቅም ፥ ሕይወት ከሎጂክ እና ሲሎጂዝም በላይ ውስብስብ መሆኑን በመጨረሻ ይረዱታል። ታላቁ መርማሪ ሸርሎክ ሆምስ ነው አይደል “ሎጂክ ማሰብ ላቃተው ሰው ነው” ያለው። በሕይወት አንድ ሲደመር አንድ ሁልጊዜ ሁለት ቢሆን ፥ ይሄ ሁሉ ልፋት ባላስፈለገ ነበር።
ምንአልባት ኢዜማዎች ለኢትዮጵያ ኋላቀርነት ዘጠኙ ቅዱሳንን ሮጠው ከሚከሱ ፥ ዘጠኙ ቅዱሳንን ሰምተው የማያውቁ የሀገራችን ክፍሎች እንዴት ዘጠኙ ቅዱሳንን ለተቀበሉ ማህበረሰቦች ለብዙ ዘመን ገባር ሆነው እንደኖሩም ቢያጠኑ ጥሩ ነበር።
0 Comments