❝ስለማንኛውም ነገር እውነት ለመናገር በእኛ መንግስት እና በድርጅት መገናኛ ብዙኅን ላይ እምነት የለኝም - ሁሉም ነገር የተጭበረበረ ነው።❞ --- ዶክተር ሮበርት ማሎን
ኮቪድን ጨምሮ በዘመናዊ ክትባቶች mRNA ጂን አርትዖት ቴክኖሎጂ ውስጥ ካሉት ሳይንሳዊ አቅኚዎች አንዱ ዶክተር ሮበርት ማሎን ናቸው። እሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለቸው ሳይንቲስት ፣ ሐኪም ፣ ደራሲ እና የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው። ዶ/ር ማሎን የኤም.አር.ኤን.ኤ. ክትባት እና የዲ.ኤን.ኤ/ዘረ መል ክትባት እንደ የቴክኖሎጂ መድረኮች ዋና ፈጣሪ ናቸው። በአሜሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫዎችን ይዘዋል። ወደ ባዮሎጂካል ሳይንሶች እና ህክምና ታማኝነትን ለመመለስ የሚተጋው የማሎን ተቋም ፕሬዝዳንት ናቸው።
የእሳቸው 'Substack' ጦማር ከሦስት መቶ ሺህ/300,000 በላይ ተመዝጋቢዎች አሏቸው። በተጨማሪም፤ “መንግሥቴ የነገረኝ ውሸቶች” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ናቸው።
0 Comments