መናፈቅ ማለት በግዕዝ ናፈቀ ተጠራጠረ ከሁለት ቦታ ተከፈለ ማለት ነው። መንፈቀ ዓመት መንፈቀ ሌሊት ስንል ግማሹን መጥቀሳችን ነውና የመናፍቅ መንፈስም ልብን ከሁለት ቦታ መክፈል ከዛም አየከፋፈለ መሄድ ሥራው ነው። ፍጻሜው ግን ጭልጥ ያለ ክህደት ማስጨበጥ ነው። በገላትያ 5 ቁጥር 19 የሥጋ ሥራዎች ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱ "መናፍቅነት" ነው።" በ2ኛ ጴጥ2:1 ደግሞ አስተምህሮአቸውን "ኑፋቄ" ይለዋል።
ጌታችን በማቴ 24:4 "ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ" ያለው እነዚህን ነው። ከቤተ ክርስቲያን የወጡና የተወገዙ ስለሆነ በየጊዜውና በየዘመኑ የራሳቸው የሆነ ማምለኪያ ቦታ ይሠራሉ።
ስለዚህ ጌታችን "በዚያን ጊዜ ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፡ ወይም፦ ከዚያ አለ፡ ቢላችሁ አትመኑ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።” “እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።እንግዲህ፦ ‘እነሆ፥ በበረሀ (በጫካ በወንዝ) ነው’ ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ ‘እነሆ፥ በእልፍኝ (በአዳራሸ) ነው’ ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤ በማለት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶናል ማቴ24:23-26።
በልዩ ልዩ የመናፍቃን አምልኮ ቦታዎች ልዩ ልዩ አጋንንት በሀሰተኛው ኢየሱስ ነኝ በሚለው መንፈስ እየታዘዙ እዛው ካለው ሰው ወጥተው እዛው ወዳለ ሰው ወደ ፈለጉት መርጠው ይገባሉ። ወደ ሲኦል ግባና ታሰር የሚላቸው ስልጣነ ክህነትና መስቀል የጨበጠ ካህን ስለሌለ ( ይህ ያለው በተዋህዶ ሃይማኖት ብቻ ነውና) ።
የመናፍቃን አጋንንት የትም አይሄዱም። ወደ መጣህበት ሂድ ተመለስ ሲሏቸው ተመልሰው ወደ ጠንቋዩ ወደ ቡዳውና ወደ ዛራቸው ሰው ወይም ወደ ለከፉበት ቦታና ወንዝ በረሃ ይሄዳሉ። በዚህ ጊዜ የአንዱ በሽታ ወደ አንዱ የአንዱ ስኬት ወደሌላው የዘዋወራል። ሰዎች ምሰጢሩን ስለማይረዱ የተፈወሱ ይመስላቸዋል። በሽታቸው በሌላ በሽታ ችግራቸው በሌላ ችግር መቀየሩን ቆይተው የሚረዱ ጥቂቶች ናቸው።
የመናፍቅ መንፈስ ብዙ የዝሙት ሠራዊተ አጋንንት አሉት። ፖስተሮችን በዚህ ይጥላቸዋል። ሴቶችን ሌሊት ፓስተር ተመስለው ይገናኟቸዋል። ወንዶችም በሴት ዝሙት አጋንንት የተጠቁ ይሆናሉ። ሌላው የመናፍቀየ መንፈስ በጣም ገንዘብ ወዳድ ያደርጋቸዋል። ያጠራቀሙትንም በአላሰቡት መንገድ አጥፍቶ በረከተ አልባ ያደርጋቸዋል። ስለዚህ ሁል ጊዜ የሀብታምን ስጦታ እንዲመኙ ያመየ የጌታ በረከት እንዲመስላቸው ያደርጋል። ጤናቸውን በማወክ ለሕክመና ወጪ ይዳርጋቸዋል። አዳል ሞቲ በቤተሰብ ያለባቸውን በውርስ ያጣላቸዋል። ከአንዱ ምንፍቅና ወደ ሌላው ያስቀይራቸዋል። ጠቋር አይናቸውን ቃሉ እንደገባቸው በማስጨፈን ህሊናቸውን በግድ የተመሰጠ በማስመሰል ዘዴ አአምሮአቸውን ይቆጣጠራል። መሬት ጥሎ ያንከባልላል። ደም ስለሚወድ ያስፈነክታል። ሌሎች የጨለማ አጋንንቶች ዓይን ጨፍኖ አሜን ሃሌሉያ በሚልበት ቅስበት የጨለማ አጋንንቱ ወደ ነፍሳቸው ይገባሉ። ከዚያም ሊይንቀጠቅጧቸው ሊየስለቅሱአቸውም ሆነ ሊያንፈራፍሩአቸው ወይም መቶ በመቶ ሰውረው በዝሙት መንፈስ ሳይታዩ ሊደፍሯቸው ይችላሉ። ሰይጣናቱ በአደሩባቸው ላይ ሆነው ልሳን በሚሉት በገዛ ቋንቋቸው ይጮሃሉ። ያን ግዜ ልሳን ወረደለኝ በልሳን ተናገርኩኝ ሰበኩኝ ዳንኩኝ ይላሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን በእምነቱ የሚገኙ የድርጅቱ ፓስተሮች በከፍተኛ አለቅነት የሚሰሩት ሁሉ ጠቀም ያለ ገነዘብ ከውጭ ግንኙነት ይላክላቸዋል። ሲስተሙ ከአጋንንት ጋር የተዛመደ ስለሆነ ምድራዊ ኑሮአቸውን የሚበለጽጉበት መተዳደሪያ ፈንድ ይለቀቅላቸዋል።
በአጭሩ የሚደረገው ነገር ሁሉ ልክ ሰይጣናዊና ለገንዘብ (ለቢዝነስ) ሲባል የተዋቀረ ነው።
ለገንዘብ ብሎ ከአጋንንት ጋር ድርድርና ውል ማድረግ ማጂክ ቀለበት ገዝቶ ማድረግ፣ ቀለማዊ ከረባት ማጥለቅ ነጭ መሃረብ አውጥቶ ማፍዘዝ፣ ወዘተ በውጭ አገር ካሉት ሃሰተኛ ፓስተሮች የተኮረጀና በስልጠና የሚገኝ ነው።የነጭ ሀሰተኛ ነብያት ዋና አላማ ገንዘብ ማካበት ነው። ሁሉም በህብረት ሲኦል እንደሚወርዱ ያውቁታል። ሆኖም በነፍስ ተጎድተው በገንዘብም መጎዳት አይፈልጉምና ከሁለቱ ጌቶች ያላቸው እድል አንዱን መምረጥ ነው ። ጌታን አስመስለው ገንዘብን መርጠዋል። የገንዘብና የሰይጣን መንፈስ የኪዳን ባሪያዎች ናቸው። የተቸገሩትን በገንዘብ ማሳት የተመረጡትን በምትሃት አሠራር ማሳት ከጥንት ጀምረው ተጠቅመውበታል። እነሱን መከተል ጥቅሙ ምንድን ነው? ወደ አንዲት ቅድስት ቤተክርሰቲያን ወደ አንዲት ጥምቀት እንመለሰ።
0 Comments