ስለ ሰሞነኞቹ ክሪፕቶዎች (ክፍል ሁለት)

የአውሬው ገንዘብና የcashless society አጀንዳ

እነዚህ ክሪፕቶዎች የመጨረሻ ግባቸው አዲስ አይነት የግብይት ስርአትን መፍጠር ነው። አሁን የመጡት ማለማመጃ ናቸው። ሰው ዘንድ እምነትን ለማግኘት እና በድግግሞሽ ውስጥ ሰው እንዲላመዳቸው ለማድረግ ታስቦ ነው። ልክ ከዓመታት በፊት ፌክ ቦቶች ሪፈራል ሊንክ እየላኩ ሲያሰለቹን የነበሩት፣ አሁን ግን ሪፈራል ተለምዶ ሰው ሁሉ የሚያደርገው እንደሆነው ማለት ነው። ከዚህም በኋላ ቀስ በቀስ ወርቅም የወረቀት ገንዘብም ሁሉም ጠፍቶ ዲጂታል ገንዘብ ብቻ ያለበት ስርአት ይመጣል።

ይህም እጅግ አደገኛ ስርአትና ሰዎች የግል ሚስጥራቸውና መረጃቸው (privacyያቸው) በፍጹም የተጣሰ የሚሆንበት ስርአት ነው።

ሁሉም ሰው የፈጸማት እያንዳንዷ ግብይት፣ ያደረጋት እያንዳንዷ ድርጊት ተመዝግባ ትቀመጣለች። በአደባባይ ማለት ነው። ከዚያም ያ ሰው ስርአቱ ከሚያዘው ትእዛዝ አንዲት ሴንቲሜትር አለፍ ሲል ያለው ገንዘብ ይወሰድበታል። ሌላም ቅጣት ይደርስበታል። የሚቀጣው ቅጣትም በአደባባይ ሁሉም እያየ ነው። ምክንያቱም የገንዘብ ስርአቱ በዛ መልኩ የተዘጋጀ ስለሆነ።

ይህ ስርአት አዲሱ የዓለም ስርአት ነው። በሶቪየት ህብረትና፣ በማኦ ዜዶንግ፣ በደርግ የነበሩትን ስርአቶች የሚያስንቅ፣ እጅግ አምባገነን፣ እጅግ ኢ-ሰብአዊ፣ እጅግ ጨካኝና ርህራሄ ቢስ የሆነ ስርአት ነው። ዜጎችን በሙሉ በእያንዳንዱ ቦታና ጊዜ በያንዳንዱ ስርቻ ካሜሪ ደቅኖ፣ የዜጎችን መረጃ በሙሉ ልብ ምታቸውን ደም ግፊታቸውን የpersonality typeኣቸውን የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን ሳይቀር... የጣት አሻራ፣ የዓይን (iris) አሻራቸውን የፊት ቅርጻቸውን ሳይቀር መዝግቦ የሚይዝ፣ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ መዝግቦ በአንድ የዳታ ማዕከል የሚያስቀምጥ እጀግ አስፈሪ ስርአት ነው። በዚህ ስርአት ውስጥም ገንዘብ ለማግኘት፣ ምግብ ለመብላት ቤት ለማግኘት፣ ስራ ለመቀጠር፣ የስርአቱን አይዲዮሎጂ ሙሉ በሙሉ መቀበል አለበት። ያንን የማያደርግ አንድም ዜጋ በግዛቱ ውስጥ ፈጽሞ አይኖርም፣ ይሳደዳል ይያዛል። ማስተማርያ እንዲሆንም ተደርጎ ይቀጣል።

ይህ ልቦለድ ወይም ፊልም አይደለም። አሁንም ጭምር እያየነው ያለነው ነገር እንጂ። በቻይና ውስጥ በየቦታው ካሜራዎች ተደቅነው አሉ። ከካሜራ ቁጥጥር ውጪ የሆነ የለም። ካሜራዎቹም የሰውን ፊትና የዐይን አሻራ ጭምር እስካን ማድረግ ይችላሉ። ቻይና የህዝቧ ዳታ በሙሉ ተመዝግቦ አለ። በማዕከላዊ ዳታቤዝ ውስጥም ተቀምጧል። የዳታ አቀማመጡና ቁጥጥሩም በከፍተኛ ደረጃ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የተደገፈ ነው። በዚህም ቻይና የራሷን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የዓለምን ህዝብ ጭምር ትሰልላለች። ቲክቶክ እጅግ በሚያስደነግጥ መልኩ የሰዎችን ዳታ የሚሰበስብና በቻይና መንግስት እጅ ላለ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ የሚመግብ ነው። የሰዎችን ልብ ምት ሳይቀር መለካት ይችላል ቲክቶክ።

እሱን ትተን እነ ፌስቡክ ትዊተርን እንኳ ብናይ በቂ ነው። ሰዎች ፎቶአቸውንና መላ ህይወታቸውን ፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ ዘርዝረው ያስቀምጣሉ። ነገር ግን መረጃቸው በሙሉ ተመዝግቦ ወደ አንድ ዳታቤዝ እንደሚቀመጥ አይረዱም። ፌስቡክ ዋትሳፕ እና ኢንስታግራምን የገዛው ሰዎችን በምን ያህል ደረጃ ሊሰልል እንደሆነ፣ በምን ደረጃ የሰዎችን privacy ሊጋፋ እንደሆነ ብዙዎች አያስተውሉም።

የሚገርመው የአሜሪካ መከላከያ የተራቀቁ ምርምሮችን የሚሰራው DARPA ይሰራው የነበረው ፕሮጀክት በተቋረጠ በዛው እለት ፌስቡክ መጀመሩ ነው። ፕሮጀክቱ የዜጎችን የህይወት እንቅስቃሴ ሙሉ መዝግቦ ለማስቀመጥ የታሰበ ነበር። ያ ፕሮጀክት በተቋረጠ በዛው እለት ፌስቡክ ሲለቀቅ ብዙዎች አላስተዋሉም። ለብዙሃኑ የተለቀቀው ትርክት አንድ ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ አቋርጦ የወጣ ጂኒየስ ተማሪ እንደጀመረው ነበር። እናም ትርክቱ በጣም ስለተራገበና ፊልም ሁሉ ስለተሰራለት ሁሉም አምኖ ተቀበለው። ነገር ግን ይህ ስርአት የአውሬው አገዛዝ ዓለምን ውጦ በፍጹም አምባገነንነት ለመግዛት የነበረውን እቅድ መፈጸሚያ አንድ እርምጃ (step) ነበር።

ከርዕሳችን አልወጣንም። ክሪፕቶ ከረንሲም ይህንኑ የአውሬው ስርአት ማስፈጸሚያ መንገድ ነው። ሰዎች ለስርአቱ እንዲገዙ ለማድረግ ዋናው መቆጣጠሪያ ገንዘብ ነው። ስለዚህ ሰዎችን በገንዘብና በግብይት መንገዶቻቸው ሁሉ ከፍተኛ ቁጥጥር ለመፈጸም ይህ መንገድ አንዱ ነው። የክሪፕቶ ከረንሲ የሚሰራበት መንገዱ ደግሞ የሁሉም ሰው ግብይት ልክ እንደ ሶሻል ሚዲያው ሁሉ በአደባባይ ስለተቀመጠና የግል ሚስጥር የሚባል ነገር ስለሌለ፣ ሁሉም ዜጋ የስርአቱ አካል እንዲሆን ለማድረግ እጅግ አመቺ ነው። ግለሰቡ ስርአቱ ከሚፈልገው አስተሳሰብ በጥቂቱ እንኳ ወጣ ካለም፣ ከሂሳብ ደብተሩ ላይ ገንዘቡ ተቀንሶ በአደባባይ ይታያል። ሲስተሙም በብሎክቼን ስለሚሰራ የሰውየው ገንዘብ የተቀነሰው በአደባባይ ስለሚታይ ማስተማርያ ይሆናል።

ይህንን ስርአት ማንም ከስሩ ማምለጥ የማይችልበትና ሁሉንም የምድር ክፍል ያዳረሰ እጀ ሰፊ፣ ሁሉንም የሚያይ (all seeing eye) የሆነ ስርአት የማምጣት ሂደት ነው። በዚህ ስርአትም ሰዎች በእጃቸውና በጭንቅላታቸው ላይ የተገጠሙ QR Code ወዘተ በመጠቀም እጃቸውንና ግምባራቸውን እስካን እየተደረጉ ግብይት የሚፈጽሙበት ስርአት ይሆናል።

ይቀጥላል

Post a Comment

0 Comments