ሰዎችን ገልብጠው እንዲያስቡ በማድረግ ወደ አጋንንትነት መለወጥ


✍ ሃሌ ሽራሕያ ሉያ

ሰዎችን ገልብጠው እንዲያስቡ በማድረግ ወደ አጋንንትነት መለወጥ ይቻላል። ጥሩውን መጥፎ ብለው እንዲያስቡ መጀመሪያን መጨረሻ እንዲሉ አድርግን አታድርግ ማሸነፍን መሸነፍ ነው ብለው የተገላቢጦሽ እንዲያስቡ ተደረጉ ማለት አጋንንት ሆነዋል ማለት ነው። ሰዎች ወደ አጋንንትነት መለወጥ የሚችሉ ሁለገብ ፍጡራን ናቸው አንዳንዶቹ ሰው አምላክ ሆነ የሚባልለት ማእረግ ላይ ደርሰዋል እስኪባል ሲከብሩ አንዳንዶቹ ሰው እንስሳ ሆኗል ከሚባለውም ደረጃ ርቀው ሄደው አጋንንት ይሆናሉ።ሰው እንዴት ከሰውነት ወጥቶ ወደ አጋንንት እንዴት መለወጥ ይችላል ቢባል የፈጣሪን አስተምህሮ በተቃራኒው በመኖር ክፉ ደጉን የሚታወቅበት የፈጣሪን አስተምህሮን ገልብጦ በመረዳት የፈጣሪን በተቃራኒው በመገንዘብና በማሰብ ወደ አጋንንትነት መቀየር ወይም መለወጥ አለ።ሰዎች ነፍስን ለሰይጣን የመሸጥ ሥራ እየሠሩ ነው ይላሉ ግን ከዚህም የባሰ ጭራሽ ሰውን ራሱ ወደ አጋንንትነት የመለወጥ ሥራ ነው እየተያያዙት ያለው።አብዛኛው የዓለም ሕዝብ አደጋ ውስጥ ነው ነፍሱን ለአውሬው እንዲገብር የሚያደርግ አሠራር እየዘረጉ ነው ይላሉ ግን እውነታው ከዚህም ባሻገር ጭራሽ ሰውን ወደ አጋንንትነት እንዲለወጥ የሚያደርግ እቅድ ተነድፎ እየተሠራ ነው።ለዚህም ይረዳ ዘንድ በመጀመሪያ እውነተኛውን የፈጣሪ አስተምህሮ እንዲዳከም በማድረግ ስለሰይጣን ማንነት ራሱ ሰይጣን ያስተማረው አስተምህሮ በማስተማር ስለ እግዚአብሔርም እንዲሁ ከሰይጣን ትምህርትና ምስክርነት በመውሰድና በመማር ቀስ በቀስ የፈጣሪ ተቃራኒ እንዲሆን ገልብጦ እንዲያስብ የፈጣሪን አስተምህሮ የሰይጣን ተብሎ የሰይጣን አስተምህሮን የፈጣሪ አስተምህሮ ነው ተብሎ ትውልዱ እንዲማር ስለተደረገ ገልብጦ ማሰብ በመጀመሩ እንዲቀየር ሆኗል።አዲስ አስተሳሰብ አዲስ መረዳት አዳዲስ አካሄድ በመፍጠር የተገላቢጦሽ እንዲያስብ ቀስበቀስ በመለወጥ ነው።ለምሳሌ በቀላሉ ለመረዳት በዘመናችን ማሸነፍን መሸነፍ መሸነፍን ግን ማሸነፍ ተብሎ እንዲቆጠር እየተሠራ ያለውን ሥራ በምሳሌ እንመልከት። ለምሳሌ አንድ ሥልጣንና ሀብት ያለው ሰውዬ የሆነ ሰውን ሃሳቤን ከተቀበልክ ብዙ ነገር እሰጥሃለሁ ነገር ግን ከእኔ ጋር ካልተባበርክ እጎዳሃለሁ ቢለውና ምርጫ የቀረበለት ሰውዬ የማላምንበትን ነገር ለጥቅማጥቅም ብዬ ሕሊናዬን አልሸጥም ካንተ ጋር ለጥቅም ብዬ በመጥፎ ነገር አልተባበርም ሃሳብህን አልቀበለውም ቢለውና ባለሥልጣኑ እንዴት እሺ አትለኝም ለምን ሃሳቤን አትቀበልም ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ነው ብሎ ቢያስፈራራውም ቢደልለውም ቢለምነውም በየትኛውም መንገድ እሺ ባለማለቱ አሰቃይቶ ገደለው ቢባል እዚህ ጋር ይህን በዘመናችን አስተሳሰብ መሠረት አሸናፊው ሰው የሚባለው ገዳዩን ሰውዬ ነው እንቢ ስላለው አሰቃይቶ ገደለው ስለዚህ አሸናፊ ነው ይባላል ግን እንደ እውነታው እንደ ትክክለኛው የማሸነፍ ትርጉም ከሆነ አሸናፊው ሰው ገዳዩ ሳይሆን ሟቹ ነው።ምክንያቱም ገዳይ ያሰበው ሃሳቡ አልተፈጸመም ሃሳቡ አላሸነፈም ቢያሸንፍ ኖሮ የሟችን ሃሳብ ማስቀየር በቻለ ነበር።ነገር ግን ሟቹ ላመነው ነገር እስከሞት ድረስ ዋጋ ከፈለለት የገዳዩ ሃሳብ ሳይሆን የራሱ ሃሳብ ተፈጸመ ተከናወነ የገዳዩ ጉዳይ ግን አልተፈጸመም አልተከናወነም ምክንያቱም ያልተከናወነውና ያልተፈጸመው ስለተሸነፈ ነው።ሰዎች ገልብጠው እንዲያስቡ በማስተማር ወደ አጋንንትነት እንዲቀየሩ ማድረግ ይቻላል።በዚህም የተነሳ ነውርን ክብር ክብርን ነውር ጥሩውን መጥፎ መጥፎውን ጥሩ ድህነትን ሃብት ሃብትን ድህነት ባዶነትን ሙሉነት ሙሉነትን ባዶነት ተብሎ እንዲቆጠር የተገላቢጦሽ እንዲታሰብ ቀስ በቀስ ትውልዱን በማስተማርና ትውልዱን በመቀየር ትውልዱ ሳይታወቀው ወደ ጋኔንነት ይለወጣል።ያኔም በዓለመ መላእክት ሰይጣን አጋንንት እንደተሳሳቱና አጋንንትና ሰይጣን መሆናቸውን የታወቀው እግዚአብሔር የመጣ ጊዜ ብቻ ነበር ከዚያ በፊትማ እነ ሚካኤል ሁላ በስሁታኖቹ ስሁታን ተብለው ነበር።

Post a Comment

0 Comments