በዚህ ጽሁፍ ለረጅም አንድ ብዙም ያልተነሳ ታሪክን እናነሳለን። የቴምፕላሮች ታሪክ፣ ከሰሎሞን ቤተመቅደስ ጋ የነበራቸውን ቁርኝት እና በኋላ ለተነሱት "የምስጢር ማህበራት" ያስተላለፉትን ታሪክ እናያለን።
በመጀመርያ ዛሬ ላይ ያለውን ሁኔታ እንይ። የጭለማው ሰራተኞች የመጨረሻ ግብ እየሆነ ያለው መካከለኛውን ምስራቅ አድቅቀው እና አውድመው፣ ፍልስጤምን አጥፍተው፣ ከግዮን እስከ ኢፍራጥስ ያለውን ምድር መቆጣጠር ነው። ከዚያም ሶስተኛውን የሰሎሞን ቤተመቅደስ መገንባት ነው። ይህ ህልም ከየት መጣ ብለን ወደ ኋላ ስናይ ከላይ ከላይ ለሁሉም ማየት የሚፈቀደው በቲዮዶር ሄርዝል የተመራው የዛዮኒስት ንቅናቄ መሆኑን፣ እነሱም የናዚን ጭፍጨፋ እና የአሜሪካን ፖሊቲካዊ ሃይል ተጠቅመው ሃገራቸውን እንደመሰረቱ ሁሉም ነው። ከሱ ትንሽ ባሻገር ስናይ ደግሞ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ማግስት የሮዝቻይልድ ቤተሰብ የፍልስጤምን መሬት በገፍ እንደገዙ፣ ከዚያም ነባር ነዋሪዎቹን አፈናቅለውና ገለው በቦታው እንደሰፈሩ፣ የሰሎሞን ቤተመቅደስን እንዳይገነቡ ደግሞ በቦታው ላይ ሙስሊሞች መስጊድ ሰርተው ኖሮ፣ ያ ትልቅ እንቅፋት እንደሆነባቸው እናያለን። በዚህ መስጊድ ምክንያትም እጅግ አስከፊ ጦርነት መነሳቱ እንደማይቀር እንረዳለን።
ያንን ወደኋላ ትተን ግን ስለቤተመቅደሱ እናውራ። ይህን ቤተመቅደስ መገንባትን ለምን እንደ አባዜ ያዙት። የመጀመርያና የመጨረሻ ህልማቸው ለምን አደረጉት የሚለውን ስናይ ያው ፖለቲካዊ መልሱ ጥንት ሮማውያን አንድ ጊዜ ባቢሎናውያንም አንድ ጊዜ ስላፈረሱባቸው አሁንም መልሰው መገንባት ስለሚፈልጉ ነው ልንል እንችላለን። ግን ያ ብቻ ነው ወይ? ብለን አለፍ ብለን ስንጠይቅ አንዳንድ ነገሮችን ማየት እንጀምራለን። የሮዝቻይልድ ቤተሰብ ሃብት ንብረታቸውን አፍስሰው የእስራኢን መመስረት የቤተመቅደሱንም መገንባት የዚህን ያህል ለምን ይደግፋሉ እንላለን። ከዚህ በፊት እንዳነሳነው ወደኋላ ታሪክ አላቸው ወይ?
በሌላ መልኩ ስናይ ደግሞ የቴምፕላሮች ታሪክ ምንጩና መነሻውም ጭምር እነዛ 9 ወታደሮች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ቤተመቅደሱ የነበረበት ስፍራ ላይ ሆነው ጠባቂው እንሁን ብለው መጠየቃቸው፣ ከዚያም ለዘመናት በቦታው ላይ ብዙ የታሪክ ቅርሶችን፣ ቅዱሱን ጽዋ እና የቃልኪዳኑን ታቦት መፈለጋቸው ነው። በኋላ ላይ ልቅ የሆነ ግብረሰዶማዊነት፣ ጸረ ክርስትና እና ጣኦት አምልኮ ላይ እንደሚሳተፉ ሲታወቅ በፈረንሳዩ ንጉስ ተለቅመው ተገደሉ። ጥቂቶቹ ግን ወደ እስኮትላን አመለጡ። ከዚያም በኋላ ላይ የነሱ ተተኪ ትውልዶች ሲንክሌር የሚባል ቤተክርስትያን ሰርተው ልክ የሰሎሞን ቤተመቅደ እንደነበረው፣ አድርገው ብዙ ምልክቶችን ሰሩበት። ግን ለምን? ይህን ያህል የሰሎሞን ቤተመቅደስ ጋር እንደ አባዜ የሆነባቸው ነገር ምንድን ነው?
እንደገና ወደፊት ስንሄድ ደግሞ የሮዝቻይልድ ቤተሰብንም ታሪክ እንይ። ቤተሰቡ ትልቅ ዳይናስቲ ከመሆኑ የተነሳ የዳይናስቲው መስራች ሜየር አምሼል ሮዝቻይልድ በአለም የምንጊዜም የፋይናንስ ተጽዕኖ ፈጣሪ እስከመባል ደርሷል። በሁሉም የሚታወቀው የቤተሰባቸው ታሪክ የሚነሳው በ 16ኛው ክፍለ ዘመን በአንድ አይሁዳዊ ሰው ነው ይባላል። ነገር ግን ይህንን የሚጻረር ሌላ መረጃም አለ። ይኸውም፣ የቤተሰባቸው ስም ሲነበብ Roth+Schild የሚለው በጀርመንኛ ቀይ ጋሻ ስለሆነ የዳዊት ጋሻ የሚሉትን ባለ ስድስት ጨረሩን ኮከብ ነው ይባላል። ነገር ጊን በሌላ መልኩ ሲነበብ Roths+Child የሚል ይሰጠናል። Roths የሚለውም Rothes ወደሚለው ይቀርባል እና ያንን ሰርች ስናደርግ የምናገኘው በስኮትላንድ የሚገኝን አንድ አከባቢ ነው። ይህንንም አከባቢ ስናጠናው፣ Leslie የተሰኘ የመኳንንት ዘር ይገዛው እንደነበር እናያለን። ያንንም ወደኋላ ስናየው ደግሞ sinclair ቤተሰብ የነሱ መነሻ እንደሆነ እናያለን። ሲንክሌር የሚለው ሴንት ክሌር ከሚለው የመጣ ሲሆን በተለምዶ ወደ ሲንክሌር ተቀይሮ ነው። እነዚህ ሲንክሌር የሚባሉት ደግሞ መነሻቸው ኖርማንዲ ከሚባለው የፈረንሳይ ግዛት የሆኑ በከፊል የቫይኪንግ ዝርያ ያለባቸው የመኳንንት ዘር እንደሆኑ እናያለን። በሌላ በኩል ደግሞ ከነዚህ ቤተሰብ ውስጥ ካተሪን የተሰኘችውን የቴምፕላሩ መሪ ሁስ ደ ፔይነስ አግብቷት እንደነበር እንደርስበታለን።
ቴምፕላሮች ከእስኮትላንድ ገዢዎች ጋር ቁርኝት ስለነበራቸው እስኮትላንድ ከኢንግሊዝ ተገንጥላ ጦርነት ውስጥ ስትገባ ቴምፕላሮቹ የውጊያ ልምዳቸውን ተጠቅመው ተዋገተውላቸዋል። እናም በኋላ ላይ የፈረንሳዮች ንጉስ ቴምፕላሮችን አሳድኖ ሲያስገድል እና ከሮማው ፖፕ ጋር አዋጅ ሲያሳውጅ፣ መላው አውሮፓ ኢንግሊዝን ጨምሮ በቫቲካን ሃገረ ስብከት ስር ስለነበር ያንን አዋጅ ተቀብሎ ቴምፕላሮችን በያሉበት ያድናቸው ነበር። እስኮትላንድ ግን ይህ ህግ በነሱ ዘንድ አይሰራም ነበር ከኢንግሊዝ ጋር በነበራቸው የመንገንጠል ሁኔታ። በዚህም ምክንያት የቫቲካን ህግ እዛ አይሰራም ነበር። በዚህም ምክንያት የተወሰኑ ቴምፕላሮች ወደ እስኮትላንድ አምልጠው ከሲንክሌር ነገስታት ቤተሰብ ጋር ተጠለሉ። በኋላም ላይ የነገስታቱ ጥበቃ ወደመሆን ተቀይረው ማህበራቸውን አስቀጠሉ። አብረውም አምልኮ ጣኦታቸውን እና ሰይጣናዊ ግብራቸውንም አስቀጥሉ። በጊዜ ሂደትም የእስኮትላንዱን ፍሪሜሶንሪ መሰረቱ። ማህበሩም ተስፋፍቶ በየጊዜው ብዙ ሰዎችን ወደ ውስጡ ማስገባት ጀመረ። በሂደትም በአውሮፓ ያለ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ የጥበብ ሰው፣ ባለሃብት ሁሉ እነሱን መቀላቀልን እንደ ተለየ ክብር ቆጠረ።
በዚህም ሂደት ፍሪመሶንሪዎች የዘመናዊውን ሳይንስ፣ የአብርሆት ዘመንን እሳቤ፣ የ"ዘመናዊነት"ን ጽንሰ ሃሳብ ጭምር ፈልስፈው፣ የዓለምን ነገስታት እየገለበጡ አዳዲስ የዓለምን ስርዓት መመስረት ጀመሩ። ይህንንም የጀመሩት አንደኛ በፈርንሳይ ነበር። ንጉሱን እና ሚስቱን አንገታቸውን ከቀሉ በኋላ የንጉሱን አንገት ከፍ አድርገው ይዘው፣ ይህ ለሞተው ቴምፕላር ለሂዩስ ደ ፔንስ ደም ምላሽ ነው ብለው እንዳወጁ ይነገራል። ይህ ታዲያ በ14ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ ለተፈጠረ ድርጊት በ18ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ደማቸውን ሲመልሱ ነው። ይህን ያህል ዘመናትን እና ትውልዶችን የሚሻገር አስተሳሰብ፣ እቅድ አና አላማ ይዘው፣ ፍጽም አምልኮ ሰይጣንን አንግበው ነበር መላውን ዓለም ወደ መግዛት እና "አዲሱ የዓለም ስርዓት" ያሉትን ወደ ማምጣት የሄዱት። የዚህ ሁሉ እቅዳቸው መደምደምያ ደግሞ በኢየሩሳሌም የሰሎሞንን ቤተመቅደስ ገንብተው፣ ከሚሶፖታሚያ (ኢራቅ) እስከ ግብጽ፣ ሱዳን ኢትዮጵያን አልፈው፣ እስከ ኡጋንዳና ታንዛኒያ፣ የቪክቶርያ ሃይቅ መነሻ እስካለበት ድረስ ያለውን መሬት ይዘው ከፍተኛ የጂኦፖለቲካ ተጽዕኖ ማሳደር እና እነሱ ባለሙት እና ባቀዱት መልኩ ፍጹም ፋሺስት እና ኮሚዪኒስት የሆነ የዓለም ስርዓትን መዘርጋት፣ እምነትን በተለይ ክርስትናን ፈጽሞ ከምድር ላይ ማጥፋት ነው ግባቸው።
እናም እንዳልነው የታሪካቸው መነሻና መደምደምያ፣ ማጠንጠኛውም የሰሎሞን ቤተመቅደስ ነው። ግን ቤተመቅደሱ ይገባቸዋል ወይ? ቅዱሱ ጽዋ ይገባቸዋል ወይ፣ ታቦቱ ይገባቸዋል ወይ? የታቦቱ ባለቤት፣ የጽዋው የቤተመቅደሱም ባለቤት ለነሱ ይሰጣቸዋል ወይ? ለነሱ አይነት ሰይጣን አምላኪ፣ ጸረ ክርስቶስ፣ ለሆኑ ሰዎች እንዲሰጥ ይፈቅዳል ወይ? መልሱ አይፈቅድም፣ እቅዳቸውም እንዲሳካ አይፈቅድላቸውም፣ በእጃቸው እንዲገባም አያደርግም፣ እቅዳቸውም በእጃቸው እንዲበተን እንዲበላሽ ያደርጋል።
0 Comments