የምንኖርባት ምድር የእውነትም ጸሃይን ትዞራለች?

እለ አጽበሐ | አዲስ ምልከታ

በሰከንድ ሰላሳ ኪሎሜትር በሆነ ፍጥነትስ በ"ህዋ" ውስጥ ትምዘገዘጋለች? ይህንን ሳይንቲስቶች "አዎን፣ እንዴታ!" ይሉናል። ነገር ግን፣ እውነታው ያ ነው ወይ? መሆኑንስ እንዴት በትክክል ማወቅ እንችላለን? የሚለውን እንመልከት።

ይህ አባባል ሳይንሳዊ እንደመሆኑ በሳይንሳዊ መንገድ መረጋገጥ አለበት። ያንን ለማድረግ ትክክለኛው መንገድ ደግሞ ምንድን ነው? ይህንን ለመመለስ "የአንጻራዊነት ፍሬም" ወይም frame of reference የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ እንመልከት።

በጥንት ዘመን፣ ሁሉም ሰው፣ ግሪኮችን ጨምሮ፣ ምድር በአንድ ቦታ ረግታ እንደምትኖር ጸሐይ ጨረቃና ፕላኔቶችም ምድርን እንድሚዞሯት ያምኑ ነበር። ከዚያም ጋሊሊዮ ጋሊሌ ተነሳ። ይህ ሰው "አይ፣ ምድር ናት ጸሃይን የምትዞረው እንጂ ጽሀይ ምድርን አትዞርም" የሚል ደፋር ሃሳብ አነሳ። ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም እንዴት እንዲህ ትላለህ፣ እንዴት እንዲህ አይነት የምንፍቅና ሃሳብ ታነሳለህ ብላ አሰረችው። በእስርም ሆኖ ሞተ። ከመታሰሩ በፊት ግን በችሎት መልክ ቀርቦ ሃሳቡን ተጠየቀ። 

ከመለሳቸው መልሶችም አንዱ እንዲህ የሚል ነበር። በመርከብ ላይ ሆነን ባህሩን ስንቀዝፍ፣ መርከቧ ተረጋግታ እየሄደች ከሆነ፣ ባህሩ ላይ ለዓይን የሚታይ ነገር ከሌለ፣ ያቺ መርከብ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሆነች ማወቅ አንችልም አለ። ስለዚህ በተመሳሳይ መልኩ፣ ምድር ላይ ሆነንም ምድር ጸሀይን ስትዞር፣ ሁሉም ነገር የምድርን ከባቢ አየር ጨምሮ ከምድር ጋር አብሮ ስለሚሄድ ምድር እየተንቀሳቀሰች አይደለችም ማለት ነው። ስለዚህ ጽሃይ ረግታ ሳለች ነገር ግን የምትንቀሳቀስ መስላ ትታየናለች መሆኑ ነው።

ነገር ግን ይህ ሃሳብ ብዙ ችግሮች አሉበት። ሌሎቹን ትተን አንድ ሃሳብ ላይ እናተኩር። እሱም ምድር ራሷ እንደምትንቀሳቀስ ለማወቅ ከምድር የአንጻራዊነት ፍሬም (frame of reference) ውጪ ሆነን ምድር ራሷ ስትንቀሳቀስ ማየት አለብን የሚለው ነው። ነገር ግን ያንን ማድረግ አይቻልም፣ ተደርጎም አያውቅም። ናሳ ወይም ስፔስ-ኢክስ ያንን ማድረግ የቻሉ እለት ለመላው ዓለም ያለ ምንም ጥርጣሬ ምድር ግሎብ እንደሆነች እና ጸሃይንም እንደምትዞር ማሳየት ይችላሉ። ነገር ግን ያ አይሆንም። 

ያ ለምን እንደማይሆን ከማየታችን በፊት፣ መሆኑስ ለምን አስፈለገ የሚለውን እንይ። ይህንን በአንድ ምሳሌ እንመልከት። ከቤት ወጥተን መኪና ተሳፍረን ወደምንፈልገው ቦታ እንሄዳለን። እናም በመኪናው ውስጥ ስንሆን ቤቱ፣ ዛፉ፣ መንገዱ በራሱ ወደኋላ እንደሚሄዱ ሆነው ይታዩናል። ነገር ግን እንደዛ ሆነው አይደለም። መኪናው ሲንቀሳቀስ ከመኪናው አንጻር ወደ ኋላ ስለሚሄዱ እንጂ። ስለዚህም የመኪናው የአንጻራዊነት ፍሬም ውስጥ ሆነን ስናይ ዛፉ ወደኋላ ሲጓዝ እናያለን፣ ነገር ግን ስንወርድ ዛፉም ህንጻውም በቦታቸው ቆመው አሉ። 

ነገር ግን፣ በሆነ ምክንያት መኪናው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ባናውቅ ኖሮ፣ መኪናው ራሱ ቆሞ፣ ቤቱ እና ዛፉ ወደኋላ የሚሄዱ ብቻ ይመስለን ነበር። ይህም ምክንያቱ፣ መኪናው ውስጥ ላለ ሰው፣ የመኪናው የአንጻራዊነት ፍሬም ውስጥ ላለ ሰው፣ ሁለቱም እኩል አሳማኝ ወይም ትክክል መሆናቸው ነው። "መኪናው ቆሞ ዛፉ እየሄደ ነው" የሚለውም፣ "ዛፉ ቆሞ መኪናው እየሄደ ነው" የሚለውም እኩል አሳማኝ ናቸው። ግን እኛ አንዱ ብቻ ትክክል እንደሆነ፣ ሌላው ልክ አንዳልሆነ እናውቃለን። ለምን? ምክንያቱም መኪናው እየሄደ እንደሆነ በትክክል ስለምናውቅ። 

እንዴት አወቅን? አንደኛ፣ ሰውነታችን በራሱ እንቅስቃሴን መለየት ስለሚችል ነው። የጆሮአችን ውስጣዊ ክፍል ውስጥ ያለ አካል፣ ቆመን ሳለን እና ስንንቀሳቀስ ያለውን ልዩነት ለይቶ፣ በምንንቀሳቀስ ወቅት መንቅሳቀሳችንን ለአእምሮአችን ማሳወቅ ይችላል። ስለዚህ መኪናው እየሄደ መሆኑን ማወቅ እንችላለን። ይህ በራሱ፣ ምድር ስትንቀስቀስ እንቅስቃሴዋን ለምን አናውቅም ወይም አይሰማንም ይሆን? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ግን ለጊዜው እሱን እንተወው።

ሁለተኛውና ለርዕሳችን ዋናው የሆነው ነጥብ ደግሞ፣ እኛ ከመኪናው ውጪ ነበርን የሚለው ነው። መኪናው ቆሞ ሳለ አይተናል፣ ውስጥ ገብተን ጥቂት ጊዜ ቆሞ አይተናል፣ ከዚያም መኪናው ተነስቶ ሲሄድ አይተናል። ስለዚህ ከውጭ ያለው ዛፍ እና ህንጻ መጀመርያም ቆሞ እንደነበር ስለምናውቅ፣ ከመኪናው የእይታ መነጽር አንጻር ሲታይ መኪናው ስለሚሄድ እንጂ ዛፉ ስለሚሄድ እንዳልሆነ በትክክል እናውቃለን። 

ይህንንም፣ "ከመኪናው የአንጻራዊነት ፍሬም (frame of reference) ውጪ መሆን" ብለን መጥራት እንችላለን። ስለዚህ፣ በአንድ የአንጻራዊነት ፍሬም ውስጥ ሆነን የሚንቀሳቀሱ አካላትን ስናይ፣ "ያ አካል ነው የተንቀሳቀሰው" የሚል እና "እኛ ነን የተንቀሳቀስነው" የሚል ሁለት እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ፣ የአንዱ መኖር አንዱን እንዳይኖር የሚያደርጉ ሃሳቦች (contradictory and mutually-exclusive) ያጋጥሙናል። በዚህም ጊዜ ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ እንገደዳለን። ምክንያቱም፣ ሁለቱም እንዳንመርጥ፣ ሁለቱም በተመሳሳይ ጊዜ እውነት መሆን አይችሉም። 

ታዲያ ይህንን ለመመለስ፣ በትክክል አሳማኝ ማስረጃ ያስፈልገናል። ያም ማስረጃ፣ በዚህ አውድ የሚሆነው፣ ከአለንበት የአንጻራዊነት ፍሬም ወጥተን ማረጋገጥ ነው። ልክ የአንድን ሰው ስሜት ለመረዳት ከኛ ጫማ ውስጥ ወጥተን በዛ ሰው ጫማ ማየት እንደሚጠቅመው፣ ወይም እኛ ነገሮችን ከምናይበት አንግል ወጥተን ሌላው ሰው ከሚያይበት አንግል እንደምናየው፣ ወይም ከአንድ ሰው ጋ በምንጣላበት ወቅት በኛ በኩል ያለውን ታሪክ ትተን በዛ ሰው በኩል ያለውን ታሪክ መስማት እንደሚጠቅመው ሁሉ

ከታክሲው ወጥተን ታክሲውን ራሱን ማየትም፣ ትክክለኛው እውነታ፣ ታክሲው እየሄደ፣ ዛፉ እና ቤቱ እየቆሙ መሆኑን እንጂ፣ የዛ ተቃራኒ አለመሆኑን ያሳየናል። 

በተመሳሳይ መልኩም ከምድር frame of reference ወጥተን ምድርን ራሷን በ"ስፔስ" ውስጥ ስትሄድ እስካላየን ድረስ፣ ምድር እየሄደች ጸሃይ ቆማለች ወይስ ምድር ቆማ ጽሀይ እየሄደች ነው የሚለውን መለየት አንችልም። ሁለቱን ተቃራኒ ሃሳቦች ለይተን እውነተኛውን ለማወቅ እንቸገራለን። ስለዚህ በግሎብ የሚያምን ሰው መጥቶ፣ ምድር በቦታዋ ረግታለች፣ ጸሀይ ግን በሰማይ ላይ ተሄዳለች ሰትሉት እንደሞኝ ወይም እብድ ከቆጠራችሁ፣ ያ ሰው እራሱ ያለው ሁኔታ አልተረዳውም ማለት ነው። 

ይህ ግን ለኛም ሙሉ በራስ መተማመን አይሰጠንም። ምድር ረግታ እንዳለችስ በምን አወቅን የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ያንን ግን እኛ በተለያየ መንገድ መመለስ አንችላለን። አንደኛ ሃይማኖታችን ያንን እውነት ያስተምረናል። በእምነታችን ቢስቁብን ወይም ባያምኑን ችግር የለውም፣ እኛ በዚያ ማፈር የለብንም። ሳይንስ በራሱ አንድ ሃይማኖት ስለሆነ፣ በርሱ የሚያምን ሰው የናንተን እምነት መጠራጠርና መካድ ከሱ የሚጠበቅ ነው።

ያም ሆኖ ግን በሳይንሳዊውም መንገድ ስንሄድ፣ እነ ሚከልሰን-ሞርሊ ያሉ ሳይንቲስቶች በሰሩት ሙከራ ምድር ፈጽሞ እንደማትንቀሳቀስ አረጋግጠዋል። ያም በፊዚክሱ ዓለም ትልቅ ቀውስ ፈጥሮ አልፏል። ያንንም ለማስተባበል ባደረጉት ጥረት ነው የአልበርት አንስታይን ሪለቲቪቲ ቲዮሪ የተፈጠረው። ቲዮሪውም ቢሆን አልበርት የራሱ አይደለም፣ ከሱ በፊት ሄንድሪክ አንቶን ሎሬንዝ እና ሄንሪ ፖኢንካሬ የተሰኙ ሰዎች አቅርበውታል። እንዲያውም የሚከልሰን ሞርሊን ሙከራ/ኢክስፐርመንት ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት የተጠቀሙበት ፎርሙላ፣ "lorentz transformation" የሚባል ሲሆን አልበርት አንስታይን ያለ ምንም ሃፍረት እነዚህን ፎርሙላዎች በራሱ የሪሌቲቪቲ ቲዮሪ ውስጥ ተጠቅሟቸዋል። 

ነገር ግን ሪሌቲቪቲ በራሱ በውዝግቦች የተሞላና ሆን ተብሎ ሰው ግራ ለማጋባት የተፈጠረ ቲዮሪ እንደሆነ ይታውቃል። ይህ በራሱ አንድ እጅግ ሰፊ ርዕስ ነው፣ ምናልባት ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። ነገር ግን ለአሁን፣ እንደው ምድር ግሎብ ሆና ቢሆን እና ጸሀይን እንደ ፕላኔት እየዞረች ቢሆን ያንን ለማረጋገጥ ትክክለኛው መንገድ ምንድነው? የሚለውን እንመልስ።

መልሱ የሚሆነ፣ መንራኩር ሰርተው፣ ከምድር ወጥተው፣ የምድር "ኦርቢት" ወይም ምህዋር ከሚባለው አልፈው ከሄዱ በኋላ፣ ከሩቁ፣ ምድርን ከነ ሙሉ መልኳ እና ሰውነቷ፣ በ "ህዋ" ውስጥም ስትቀዝፍ፣ ቪዲዮ ቀርጸው፣ በቀጥታ ስርጭት፣ ማንንም በተቀናበረ ቪዲዮ ለማታለል ሳይሞክሩ፣ ማሳየት ይኖርባቸውል። ነገር ግን ችግሩ፣ ያንን ማደረግ አይችሉም። አያደርጉትም። ማድረግም አይፈልጉም። ምክንያቱም እውነቱን አሳምረው ስለሚያውቁ። ለኛ ግን ይዋሹናል። ብዙ ባለ ብሩህ አእምሮ ሰዎችንም ጨምሮም፣ ብዙሃኑ በነሱ አዚማም ውሸት ይታለላል።

Post a Comment

0 Comments