ፓላንቲር | የአውሬው ሰራተኞች የመጨረሻ ግብ


ፓላንቲር ማለት የአውሬው ሰራተኞች የመጨረሻ ግባቸው ነው። መላውን ዓለም እና በውስጡ የሚኖሩትን ሰዎች በሙሉ ሁልጊዜ፣ ሁሉም ቦታ ላይ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መከታተል፣ የሁሉንም ሰው መረጃ ከነ ማንነቱ ከነ ታሪኩ መዝግቦ መያዝ እና በአንድ አይዲ ካርድ ተጠቅሞ የዛን ሰው ሁሉ መረጃ የመከታተልና የማወቅ ፍላጎትን ለማሳካት የታቀደ ነው።

ይህ በቢሊዮን ዶላሮች ፈንድ የሚደረግ ድርጅት፣ ከአሜሪካ እና እስራኤል መንግስት፣ ከፔንታጎን፣ ከሲ አይ ኤ እንዲሁም ኤፍ ቢ አይ ጋር በመሆን ሁሉንም መረጃ በአንድ የዳታ ቋት ማሰባሰብ እና ማንም ሰው እነሱ ከሚፈልጉት መንገድ ከወጣባቸው በካሜራዎች ተከታትሎ፣ ምስሉን አውጥቶ፣ ከምስሉ ስሙን አድራሻውን የህክምና ታሪኩን የባንክ የትምህርት ቤት የንብረት የወንጀል መረጃውን፣ ሶሻል ሚዲያ ላይ ፖስት ያደረገውን ነገር ጭምር በማውጣት እዛ ሰው ላይ እንዲወሰድ የፈለጉትን አይነት ማንኛውም ቅጣት ማስተላለፍ ነው። ስለዚህ ማንኛውም ሰው በሁሉም የዓለም ክፍል ከነሱ እይታ ሳይወጣ፣ መረጃው በነሱ ሳይመዘገብ መኖር እንዳይችል፣ እነሱ የፈቀዱትን ማሰብ፣ እነሱ የፈቀዱትን መብላት መጠጣት፣ እነሱ የፈቀዱትን ማለት፣ እነሱ የፈቀዱትን መግዛት መሸጥ ብቻ እንዲችል ለማድረግና ለማስገደድ የሚያስችል፣ ዓለም አቀፋዊ ፍጹም አምባገነን አገዛዝን ለማስረጽ የሚደረግ ነው። የነሱን አምባገነናዊነት እና ፋሺስትነት፣ የነሱን ሁሉንም ነገር የማየትና የማወቅ ፍላጎት በዓለም ታሪክ ተነሱ የተባሉት አምባገነኖች ሁሉ እንኳን ሊስተካከሉት፣ እንዲያውም አይቀርቡትም።

ልክ እግዚአብሔር በመላው ዓለም ያለው ነገር ከርሱ እንደማይሸሸገው ሁሉ፣ በዓለም ያለው ሰው ሁሉ ተደብቆም በግልጽም የሚያደርገውን እንደሚያውቀው ሁሉ፣ እነዚህም ያንን በመመኘት፣ እንደ ፈጣሪ ለመሆን የመሻት ነገር ነው የሚታይባቸው። እነሱ በፈለጉት ጊዜ እና ሁኔታ፣ በራዕይ ዮሐንስ ላይ ያለውን የአውሬውን፣ ጸረ ክርስቶስ የተባለውን ሃሳዊ መሲህ በራሳቸው የጊዜ ሰሌዳ የማምጣቱ እቅዳቸው አፈጻጸም ሲሆን፣ እነሱም የሚያምኑት ያ ቴክኖሎጂ ነው ሃሳዊው መሲህን ያን አይነት ሃይል እንዲኖረው የምያደርገው።

የአሜሪካው ዶላር ላይ ያለው በፒራሚድ ላይ ያለው ምልክት፣ "the all seeing eye" ወይም ሁሉን የሚያየው ዐይን ይህ ነው። ይህ ነው ለዘመናት የተመኙት እና ለመፈጸም የሰሩለት እቅድ እና ግብ። መላውን ዓለም ፍጹም ርህራሄ በሌለው ጭቁን አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ፍጹም ጸረ ክርስቲያን እና ጸረ ክርስቶሳዊ በሆነ አመራር ለመምራት እና ለመግዛት የሚያቅዱበት ህልማቸው ነው። እንዲያውም አሁን ላይ፣ ሰዎች የሚያደርጉትን ከማወቅ አልፎ ሰዎች የሚያስቡትንም ለማወቅ ፍላጎት የሚያድርባቸው ሆኗል። ይህም በኢሎን ማስክ ድርጀት ኒውራሊንክ በሚባለው ተጠቅመው በጭንቅላት ውስጥ የሚገጠም ቺፕ መስራት ከጀመሩ ቆይተዋል። ይህንን ነገርም በዚሁ ሁኔት ቀጥለው የሰዎችን ጭንቅላት እስከመቆጣጠር፣ ሰዎች የሚያስቡትንም ጭምር ልክ እንደ ፈጣሪ ለመያዝ አስበዋል።

ለዚህም ሲባል በመላው ዓለም ሁሉም መንግስታት የዲጂታል አይ ዲ ስረአትን እንዲዘረጉ፣ ዲጂታል አይዲም ከሶሻል ሚዲያ፣ ከባንክ አካውንቶች፣ ከትምህርት ቤት እና ከሁሉም የመንግስት አገልግሎቶች ጋር እንዲያያዝ በማስደረግ እቅዱ እየተፈጸመ ነው። ታድያ ከመላው ዓለም የሚመጣውን የቢሊዮን ሰዎች ዳታ ለመቆጣጠር ደግሞ እጅግ ግዙፍ ዳታን አውቶማቲክ በሆነ መልኩ የሚቆጣጠር አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ በማዘጋጀት ያም መረጃውን በሙሉ እያዘጋጀ የማንኛውም ሰው ዳታ በተፈለገ ቁጥር በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ የዛን ሰው ሙሉ ዳታ አዘጋጅቶ እንዲያስቀምጥ ማድረግ ነው።

ይህ ሁሉ ህልም ታድያ ልክ የባቢሎንን ግንብ የመገንባት አይነት ህልም በመሆኑ ፈጣሪም እንዲሳካ የማይፈቅደው ነው። ጊዜው ሲደርስ እርሱ ራሱ ያጠፋባቸዋል። ያፈርስባቸዋል። ምክንያቱም እንደ ባቢሎን ግንብ ሁሉ ይህም በፈጣሪ በራሱ ህልውና ላይ የሚደረግ መጻረር ስለሆነ፣ እግዚአብሔር እንዳለ፣ እግዚአብሔር እንደሚሰራ ለነሱም ሆነ ለመላው ዓለም ማሳየት ስላለበት ያ ህልማቸው ሳይሳካ ይቀራል። ይህም ብቻ ሳይሆን፣ ይህ ሁሉ እቅድ መሲህ የሚሉትን እነሱ ባሉት እና እነሱ በፈቀዱት ጊዜ የማምጣት ህልም ስለሆነ፣ ክርስቲያኖችንም አሳስቶና አታሎ፣ "ይህ የዓለም መጨረሻ ነው፣ የዓለም ፍጻሜ ነው" በማለት በማሳመን ተስፋ የማስቆረጥም ህልም መሆኑ ነው። ነገር ግን ችግሩ ክርስቲያኖች ስለ "የዓለም ፍጻሜ" (apocalypse) ሲያስቡ፣ እነዚህ ሰዎች ግን ከዚያ በኋላ ስለሚኖር ዓለም እና እነርሱ ስለሚገዙበት ዓለም (post-apocalypse) ነው። ከዚያ በኋላ መጨረሻው ለማይታወቅ ጊዜ መላውን ዓለም እንደ ፈጣሪ ሆነው መግዛት እና መምራት ህልም ያላቸው ስለሆነ ነው። ያ ደግሞ ቀድመን እንዳልነው እግዚአብሔር እንዲሆን የማይፈቅደው ነገር ነው።

Post a Comment

0 Comments