በ ወንድወሰን ውቤ
ዘሪቱ ከበደ ትረካዋን የጀመረችው የሠራችውን ኃ*ጢ*አት ያለፍርሃትና ሃፍረት በመናዘዝ ነው። መጽሐፉ ላይ ወደፊትና ወደ ኋላ እየተወዛወዘች ደጋግማ የምታነሣው ይህንኑ ካገባች በኋላ፣ «የልጁነት» ጸጋ አግኝቻለሁ ካለች በኋላ፣ በዕድሜም በአስተሳሰብም በስያለሁ ካለች በኋላ ከጋብቻ ውጭ ባደረገችው ተራክቦ የማ*ርገ*ዟን ነገር ነው።
መውደቋን ለምን በዚህ ደረጃ አጉልታ የግለ ታሪኳ አካል እንዳደረገችው በግልጽ አልነገረችንም። «ክርስትናዋ» የወደቀ ይሰባበር፣ የወጣ አይመለስ፣ የጠፋ በግ አይገኝ የማይባልበት ክርስቶሳዊ ከሆነ ዘንድ ድቀቷ በዚህ ደረጃ ትኩረት ያገኘበት አስፈላጊነት አልገባኝም። ምናልባት ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ስለሆነ? ምናልባት በታዋቂነቷ ምክንያት የሰው ትኩረት ይዞ ቆይቶ ስለነበረ ግልጽ ለማድረግ ይሆን? ወይም በምትሳተፍበት ቸርች በጣም የተቦካ ጉዳይ ስለነበር ከፈረሱ አፍ ይስሙት በሚል መረጃ ለመስጠት ፈልጋ? ወይስ እንዲህ የነበርኩትን እንኳ ይቅር ብሎ ተቀብሎኛል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ? በጸጋው ብቻ ድኛለሁ በሚል ጽኑ እምነት ውስጥ ላለ ሰው ደግሞ ይህ ወድቆ መነሣት «የተረጋገጠው😏» መጽደቃቸው ላይ ምን ሊጨምር?
ሁኔታዋ የንስሐ አባት አያስፈልግም በሚል አስተምህሮ ውስጥ ብልጭ ያለ ሕዝቡ የንስሐ አባት ይሁነኝ ዓይነት አቋም ይመስላል። በንስሐ አባት ፊት መናዘዝን የማትቀበል ሰው በሕዝብ ፊት በዚህ ደረጃ በመናዘዝ ምን ይገኛል ብላ አስልታ እንደሆነ ያነጋግራል። ለመጽሐፉ ገበያ ፈልጋው ነው ለማለት ከሰብእናዋ አንፃር አልደፈርኩም።
ስሕተቷን በዚህ ደረጃ የመጽሐፉ አስኳል አድርጎ ማንሣቱስ ልጇ ራሱን በአደባባይ በወፍራሙ የተጮኸለት ስሕተት ውጤት አድርጎ እንዲያይ አይገፋውም ይሆን?
የዘሪቱ ግለ ታሪክ በቀጥተኛነትና በሐቀኝነት ለመጻፍ እንደተሞከረ ያስታውቃል። ግን ደጋግማ «ቀጥተኛና ግልጽ ነኝ» የምትለው ዘሪቱ እጅግ የተፈተነችበትንና ለእር*ግዝና የዳረጋትን ኃጢ*አት እንደ መጽሐፉ ቃል በቀጥታ ዝ*ሙት ብላ ለመጥራት እንደሸሸች እና በተለያዩ የዳቦ ስሞች እንደጠራችው የመጽሐፉ የመጨረሻ ገጽ ላይ እንደርሳለን።
«በባሕርየ ቀጥተኛ ነኝ» (ይህን ምስክርነቷን በብዙ ቦታ መጽሐፉ ላይ እናገኘዋለን) ብላ ስለራሷ መስክራ ሰሰትጨርስ በቀጣዩ አንቀጽ የፀፀቷ ምክንያት የሆነውን የኃ*ጢአት ሥራ(እርሷ ኃጢ*አት ብላ አትጠራውም)፣ ዝ*ሙትን በቀጥታ ሳይሆን በሽፍንፍን ቃል «አንድነት» ብላ ስትጠራው እናገኛታለን። ይህ መጽሐፍ ቅዱስን ለማረም መሞከር ወይም ግልጽ በመሆንና ባለመሆን መካከል መዋለል ነው። ነገርየው የተገለጸበት አንድ ምሳሌ እነሆ ከመጽሐፉ፤
«እንዴት የኢየሱስ ብቻ ነኝ በምልበት ዘመን ለመጸነስ የሚያበቃን አንድነት ከጋብቻ ውጭ ለመፈጸም ደፈርሁ?» (#አንድነት😉)
ከፕሮቴ*ስታንት ኳየሮች ፈልሰው በሙዚቃው ዓለም ያሉ ሙዚቀኞች «መስክርላት፣ መስክርለት» እየተባባሉ በሙዚቃው መስክ ፕሮቴስታንታዊ መረባቸውን እንዴት እንዳጠመዱ መጽሐፉ ይነግረናል።
ያደነቅሁላት
👉አተራረኳን
👉እንደ ብዙኃኑ የፕሮቴስታንት ሰዎች የነበረችበትን(?) ሃይማኖት ለመጎንተል ብዙ አልደከመችም። ነገር ግን ርቃ አልራቀችም። ለምሳሌ በቤታቸው አካባቢ ስለነበረው የግንቦት ልደታ አከባበር የተረከችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ባልዋለችበት ለማዋል ጉተደረገ አንድ ማሳያ ነው። እንዲሁም ከግለ ታሪኳ ጋር ተዛምዶ በሌለው ሁኔታ ጎትታ ባስገባችውና «ከገድል የተገኘ» ብላ የዳዊትና ጎልያድ ታሪክ ጋር አያይዛ ያቀረበችው ትረካ አለ። ክርስትናን የማያውቁ ክርስቲያኖች በሰፈር የግንቦት ልደታን በዓል ሲያከብሩ የሚያከናውኑትን ከባዕድ አምልኮ ጋር የተያያዘ ድርጊት ቤተ ክርስቲያን የምትደግፈው ወይም የማታወግዘው አስመስላ አቅርባዋለች። በስም ባልተጠቀሱ አንድ አባት ሰማሁት ያለችውን የዳዊትንና ጎልያድን ታሪክ ገድላትና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጩ አስመስላ ተርካለች።
👉 ለትዳሯ መፍ*ረስ ጣቷን ባሏ ላይ አለመቀሰሯ። Indpendent woman የሚለው አብዮታዊ የኑሮ መርኋ ትዳርን ያለሠርግ ማከናወን ቢያስችላትም ትዳሯን ለማትረፍ እንዳላስቻላት ትገልጻለች። ባህላዊው ትዳር ውስጥ ያለውን አብሮ የመኖር ጥበብ ባለመማሯና በመናቋ ዋጋ እንደከፈለችም ታሠምርበታለች።
👉 ልጆቿን ያሳደገችበት የሥነ ምግባርና የተግባቦት መንገድ ትምህርት ይሰጣል።
በመጨረሻ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተለይታ ወደ ፕሮቴስታንት መሔዷን ለመግለጽ ይመስላል የመጽፉን ርእስ «ከልጅነት እስከ ልጁነት» ያለችው። እዚህ ላይ ነው ምፀቱ።
ኦርቶዶክስ ሳለች በድንግልና ነው ያገባቸው። ይህን ከዝሙት የመራቅና የመጠበቅ ጸጋ ወይም ኅሊናዊ ዝግጁነት ያገኘችው ካስተዳደጓ ነው። እዛ አስተዳደግ ውስጥ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊነት ጉልህ ነው።
ከጌታ እቅፍ ወጥታ «ልጁነትን» አገኘሁ ካለች በኋላ ደግሞ ለበርካታ ጊዜ በጋብቻዋ ላይ ስትወ*ሰልት እንደነበረ አጠይማ ትነግረናለች። ታዲያ ለኅሊና ከመታመን ለቃል ኪዳን ወደ አለመታመን ያደረገችው የዘሪቱ ጉዞ ከልጅነት ወደ «ጅ*ልነት» ወይስ ወደ ከልጅነት ወደ «ልጁነት»?
0 Comments