በሙስሊሞች ላይ የተጫኑ 4ቱ ሸክሞች!

ሚካኤል ዘኢትዮጵ

ይህ ምልከታዬ የእስልምና እምነት መሠረት የሆኑትንና በታሪክ ሂደት ውስጥ "በወሬ ብዛት" እንደ ሐቅ ተቆጥረው የቀረቡትን አራት ዋና ዋና ሸክሞች ማለትም ማንነቱ የማይታወቀው አላህ፣ ሐሰተኛው መሐመድ፣ ቁርአን እና ሐዲስ ወሸሪዓ ላይ ያተኩራል። በእምነቱ አስተምህሮ እና በተጨባጭ የታሪክና የአርኪኦሎጂ ማስረጃዎች መካከል ያለውን ሰፊ ገደል በመዳሰስ፣ እስልምና ከቀደሙት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታዎች እንዴት እንደሚጋጭና በምትኩም በባሕላዊ ትርክቶችና በኃይል የተገነባ ሥርዓት መሆኑን በጥልቀት እናያለን።

1) ምንነቱ የማይታወቀው አላህ፡

የእስልምና አምላክ ተብሎ የሚታወቀው "አላህ" ከመሐመድ በፊት በነበሩት የአይሁድና የክርስቲያን መጻሕፍት ውስጥም ሆነ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ እንደ ብቸኛና የዓለም ፈጣሪ አምላክ ተጠቅሶ አይገኝም። ምንም እንኳን እስልምና አላህን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እንደሆነ አድርጎ ቢያቀርብም፣ በጥንታውያን ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኘው የአምላክ ስም "ያህዌ" (YHWH) እንጂ አላህ አይደለም። ይህ "አላህ" የተሰኘው መጠሪያ በቅድመ እስልምና ዘመን በዓረብ ምድር ይኖሩ በነበሩ አረማውያን ዘንድ ከነበሩት ጣዖታት መካከል የአንዱ ስም እንደነበረ የታሪክ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህም ምክንያት አላህ እንደ አምላክ የተሰጡት ባሕርያትና ስሞች (99ኙ ስሞች) ከታሪካዊ ማስረጃ ይልቅ በመሐመድ ንግግር ላይ ብቻ የተመሠረቱ ናቸው። በዚህም መሠረት እስልምና የሚጠቅሳቸው መላእክት (ለምሳሌ ጅብሪል) እና የቀደሙ ነብያት ታሪክ ከቀደሙት መጻሕፍት ተቀድተው ነገር ግን ይዘታቸው ተለውጦ የቀረቡ "ምናባዊ" ትርክቶች ናቸው። መሐመድ አላህን የቀደሙት ነብያት አምላክ ነው ቢልም፣ አይሁድና ክርስቲያኖች ግን ይህንን አምላክ እንደማያውቁትና ከመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ባሕርይ ጋር እንደሚጋጭ ይታወቃል።

የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ (ያህዌ) እና የእስልምናው አላህ በመሠረታዊ ባሕርያቸው በእጅጉ ይጋጫሉ። ያህዌ ራሱን ለሰው ልጆች እንደ "አባት" የሚገልጥ፣ ከፍጥረቱ ጋር የጠበቀ የፍቅር ግንኙነት ያለውና ቃሉን የማይለውጥ የታመነ አምላክ ሲሆን፤ አላህ ግን በቁርአን (ሱራ 112:3) "አልወለደም፣ አልተወለደምም" በሚል መርህ አባትነትን ሙሉ በሙሉ ይክዳል። ይባስ ብሎም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን ፈጽሞ የማይዋሽና የማይለወጥ አድርጎ ሲያቀርብ፣ ቁርአን ግን አላህን "ከአታላዮች ሁሉ በላጭ አታላይ" (ኻይሩል ማኪሪን - ሱራ 3:54) በማለት ሰዎችን ለማታለል "መክር" ወይም ተንኮልን እንደሚጠቀም ይገልጻል። እነዚህ ልዩነቶች አላህ ከመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ጋር አንድ አለመሆኑንና ምንጩም ከአይሁድና ክርስቲያን መጻሕፍት ሳይሆን፣ ከቅድመ እስልምና የዓረብ ጣዖታት መጠሪያና ባሕርይ የተቀዳ መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ።

2) የመሐመድ የሐሰት ነብይነት

መሐመድ ራሱን የነብያት መደምደሚያ አድርጎ ቢያቀርብም፣ ለነብይነቱ ከመሐመድ ንግግር ውጭ ሌላ ገለልተኛ ምስክር የለውም። የቀደሙት ነብያት ነብይነታቸውን የሚያረጋግጥ ታላቅ መለኮታዊ ተአምር በሕዝብ ፊት ያሳዩ ነበር፤ መሐመድ ግን በቁርአን ውስጥ በግልጽ እንደተቀመጠው (ሱራ 13፡7) ተአምር እንዲያሳይ ሲጠየቅ "እኔ አስፈራሪ እንጂ ተአምር አድራጊ አይደለሁም" በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። ምንም እንኳን ከጊዜ በኋላ የተጻፉት የሐዲስ ዘገባዎች መሐመድ ጨረቃን ሰነጠቀ፣ ውኃ ከመዳፉ አፈለቀ የሚሉ ተአምራትን ቢደርድሩም፣ የቁርአኑ ቃል ግን መሐመድ ተአምር እንዳላደረገና ሐሰተኛ እንደሆነ ይመሰክራል። በተጨማሪም መሐመድ 124 ሺህ ነብያት አልፈዋል ቢልም፣ ከእነዚህ ውስጥ አንዱም ስለ መሐመድ መምጣት የተነገረ ትንቢት በመጻሕፍቶቻቸው ውስጥ አይገኝም። ሙስሊሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ጥቅሶችን (ለምሳሌ ዘዳግም 18፡18) ለመሐመድ ለመስጠት ቢሞክሩም፣ ጥቅሶቹ ከታሪካዊና ከመንፈሳዊ አውድ አንጻር ከመሐመድ ጋር የማይገጥሙ ሆነው ይገኛሉ። መሐመድ ራሱ ባመጣው የሐሰት መለኮታዊ ቃል ውስጥ ራሱን ከትችትና ከቅጣት ነፃ ማድረጉ፣ እንዲያውም ለራሱ ልዩ የጋብቻና የጦር ምርኮ መብቶችን መፍቀዱ (ሱራ 33፡50) የነብይነቱን ምንጭ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል።

3) ሐሰተኛው ቁርአን፡

ቁርአን በጅብሪል አማካኝነት ከአላህ ዘንድ የወረደ ቀጥተኛ ቃል ነው ተብሎ ይታመናል። ሆኖም ግን ቁርአን ውስጥ የሚገኙት ታሪኮች (ለምሳሌ የኖኅ፣ የአብርሃም፣ የዮሴፍና የኢየሱስ ታሪክ) ከቀደሙት መጻሕፍት የተወሰዱ ቢመስሉም፣ የታሪክና የዘመን ስህተቶች ይስተዋሉባቸዋል። ለምሳሌ ያህል የሙሴን እኅት ማርያምንና የኢየሱስን እናት ማርያምን በአንድ ዘመን እንደነበሩ አድርጎ ማቅረቡ (ሱራ 19፡28) የታሪክ ግድፈት መኖሩን ያሳያል። በተጨማሪም ቁርአን "ናሲክ ወ መንሱክ" (የሚሻርና የሚተካ) የሚባል ሕግ ያለው ሲሆን፣ ይህም አላህ ቀደም ብሎ የተናገረውን ቃል በኋላ በሚወርድ ሌላ ቃል እንደሚለውጥ ይገልጻል። ይህ የአምላክን ዘላለማዊ አዋቂነትና የማይለወጥ ባሕርይ የሚቃረን ነው። ቁርአን የወረደበት መንገድም ቢሆን መሐመድ ብቻ የሚያየውና የሚሰማው እንጂ ሌላ ምስክር ያልነበረው በመሆኑ፣ መጽሐፉ ከመለኮታዊ ምንጭ ይልቅ በመሐመድ ግላዊ አስተሳሰብና በወቅቱ በነበሩ የአረብ ባሕሎች የተቀረጸ ነው የሚለውን ሐሳብ ያጠናክራል።

4) ሐዲስና ሸሪዓ

ከሦስቱ መሠረታዊ ሸክሞች በተጨማሪ፣ "ሐዲስ" (የመሐመድ ንግግሮችና ድርጊቶች) በሙስሊሞች ላይ ትልቅ ሸክም ሆኖ ይገኛል። ሐዲሶች መሐመድ ከሞተ ከመቶ ዓመታት በኋላ የተሰበሰቡ በመሆናቸው ለፈጠራና ለፖለቲካዊ ፍጆታ የተጋለጡ ናቸው። ብዙዎቹ ሐዲሶች ከጤናማ አስተሳሰብና ከሰብአዊ መብት ጋር የሚጋጩ መመሪያዎችን (ለምሳሌ ሴቶችን ማዋረድ፣ ከእምነት የወጣን መግደል፣ የሕፃናት ጋብቻ) ይዘዋል። ሌላኛው ሸክም ደግሞ "የሸሪዓ ሕግ" ነው። ይህ ሕግ የሰውን ልጅ ነፃነት የሚገድብ፣ ጥብቅና ጨካኝ ቅጣቶችን (እጅ መ*ቁረጥ፣ በድንጋይ ወ*ግሮ መግደል) የሚደነግግ በመሆኑ፣ ተከታዮቹን በጭንቀትና በፍርሃት ውስጥ የሚጠምድ ሥርዓት ነው። 

እነዚህ ሁሉ ተዳምረው እስልምናን ከእምነት ይልቅ በወሬና በኃይል የተገነባ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅር እንዲመስል አድርገውታል። አማኙም እነዚህን ነጥቦች መርምሮ እውነቱን እንዳያውቅ "አትጠይቁ፣ አትመርምሩ" በሚሉ ሃይማኖታዊ ክልከላዎች ታስሮ ይገኛል።

Michael Z Ethiop
02/05/2018 ዓ/ም

Post a Comment

0 Comments