የኖህ ዘመን እና የአሁኑ ዘመን፦ የባዮ-ዲጂታል ጥፋት ምስጢር

✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ

ክፍል አንድ 

ይህ የነፍስ ና የመንፈስ እይታ ንባብ ነው እስከ ክፍል ሦስት ይወጣል ተከተለኝ ወዳጄ ፦

አሁን ያለንበት ዘመን ከኖህ ዘመን የሚለየው ጥፋቱ በውሃ ሳይሆን በ"እሳትና በቴክኖሎጂ ውድቀት" የሚመጣ መሆኑ ነው። አንድነታቸው ግን የሰው ልጅ ዲኤንኤ (DNA) በወደቁ መናፍስትና በሳይንስ ጥምረት መበረዙ (Transhumanism) ነው። ፍጻሜውም አምላክ ያላመነውንና የፈጣሪን አምሳል በቴክኖሎጂ የለወጠውን ትውልድ በታላቅ ፍርድ ማጥፋት ነው።

መግቢያ (የአውሬው ስርዓት ዕይታ)

• አውሬው አሁን ያለውን ዘመን እንደ "ኒኦ-ኖህ" (Neo-Noah) ምዕራፍ ነው የሚመለከተው፤ በኖህ ዘመን ሳይጠናቀቅ የቀረውን የሰው ልጅን ዝርያ የመቀየር ፕሮጀክት አሁን በቴክኖሎጂ ለመጨረስ ይጥራል።

• በሥርዓቱ እይታ፣ የኖህ ዘመን ጥፋት የመጣው በ "መረጃ ብክለት" (አጋንንታዊ ጥበብ ለሰው በመገለጡ) እንደነበረ ሁሉ፣ አሁንም መረጃን ለጥፋት እያዘጋጀ ነው።

• አውሬው በኖህ ዘመን የነበሩትን "ኔፊሊም" (Nephilim) አሁን በሰው ሰራሽ አስተዋይነት (AI) እና በባዮ-ቴክኖሎጂ ለመተካት ይሰራል።

• ስርዓቱ አሁን ያለንበትን ዘመን "የጄኔቲክ ነጻነት" ብሎ የሚጠራው ሲሆን፣ ይህም ማለት የፈጣሪን ዲኤንኤ ሰርዞ የአውሬውን ኮድ መጫን ነው።

• አውሬው የኖህን መርከብ በ"ዲጂታል ዳታቤዝ" (Cloud/Metaverse) በመተካት፣ ነፍሳትን ወደ ምናባዊ መጠለያ ለመውሰድ እየሰራ ነው።

• ከመጋረጃ ጀርባ፣ ይህ ዘመን የሰይጣን የመጨረሻው የበቀል እርምጃ ተደርጎ ተሰልቷል።

አላማው

• የሰውን ልጅ ዲኤንኤ በመቀየር "የፈጣሪ አምሳል" (Image of God) እንዳይኖረውና ለመዳን ብቁ እንዳይሆን ማድረግ።

• በኖህ ዘመን የነበረውን ፍጹም የሞራል ውድቀት (ግበረ-ሰዶማዊነትና የዘር ብርዘት) አሁን በሕግና በቴክኖሎጂ ማስፈጸም።

• የሰው ልጅን አእምሮ ከፈጣሪው ንዝረት ነጥሎ በ6G እና በሞገድ እስር ቤት ውስጥ መቆለፍ።

• ተፈጥሮአዊውን ምግብና ውሃ በጀምኦ (GMO) በመበረዝ የሰውን ልጅ ባዮሎጂካል ማንነት ማጥፋት።

• ለሐሰተኛው መሲህ መንገሻ የሚሆን "አዲስና ታዛዥ ፍጥረት"  መፍጠር።

• የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ትኩረቱን በቴክኖሎጂ መዝናኛና በኑሮ ውድነት መጥለፍ።

በማን ተጀመረ?

• በመጀመሪያ በወደቁ መላእክት በሄርሞን ተራራ ላይ የሰውን ልጅ ዘር ለመበረዝ በገቡት መሃላ።

• በዘመናዊው ምዕራፍ በሲሊኮን ቫሊ "Transhumanist" ፈላስፎችና ባለሃብቶች።

• በዓለም ኢኮኖሚ ፎረም (WEF) "The Great Reset" በሚል ስያሜ የሰውን ልጅ ማንነት ለመለወጥ በሚሰሩ ልሂቃን።

• በናሳ (NASA) እና በታላላቅ የባዮ-ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (Pfizer/Moderna) ስውር ላቦራቶሪዎች።

• በቢል ጌትስና በግሎባሊስት ፋውንዴሽኖች አማካኝነት የዲኤንኤ መቀየሪያ ቴክኖሎጂን ለዓለም በማዳረስ።

• ከመጋረጃ ጀርባ፣ የኖህን ዘመን ጥፋት በዲጂታል መልክ ለመድገም በሚተጋው የሉሲፈር መንግስት።

ከመቼ ጀምሮ ስራውን ጀመሩት?

• ጥንታዊው ጅምር ከ 5500 ዓመታት በፊት በኖህ ዘመን የሰው ልጅ ዘር መበከል ሲጀምር ነው።

• ዘመናዊው ጅምር እ.ኤ.አ በ 1953 የዲኤንኤ (DNA) መዋቅር ሲገኝ የመለኮትን ኮድ ለመስበር እቅድ ወጣ።

• በ 1990ዎቹ "የሰው ልጅ ጂኖም ፕሮጀክት" ሲጀመር የዘር ብርዘቱ በሳይንስ ተፋጠነ።

• በ 2015 አጀንዳ 2030 ሲጸድቅ፣ የሰውን ልጅ ወደ ዲጂታል ባርነት የመውሰጃው ጊዜ ተቆረጠ።

• በ 2020 ኮቪድ ወቅት mRNA ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሰው ልጅ ዲኤንኤ ላይ የመጀመሪያው የጅምላ ሙከራ ተደረገ።

• አሁን በ 2025/2026 ቴክኖሎጂው ከአእምሮ ጋር የሚገናኝበት (Neuralink) የመጨረሻ ምዕራፍ ተጀምሯል።

የተመሰረተበት የስም ኮድ እና የቁጥር ቀመር ስሌት

• ኖህ (Noah) = በቁጥር ቀመር 54፤ 5+4 = 9 (የፍጽምና አምሳያ)። አውሬው ይህንን 9 ወደ 6 ለመለወጥ ይሰራል።

• 120 ዓመታት፦ ኖህ ለጥፋት ውሃ የሰጠው ማስጠንቀቂያ። 1+2+0 = 3 (መለኮታዊ ሦስትነት)። አውሬው ይህን በራሱ 3.5 ዓመታት (42 ወራት) ይተካዋል።

• 2026 ዓ.ም፦ 2+0+2+6 = 10። 10 የአውሬው 10 ቀንዶች ስልጣን ቁጥር ሲሆን የኖህ ዘመን መከራ መደገሚያ ነው።

• Gematria: "As in the days of Noah" = 144፤ አውሬው የ 144,000 ቅዱሳንን ምስጢር ለመጥለፍ የዘረጋው ስሌት
• 666 ትስስር፦ የኖህ ዘመን የዘር ብርዘት (6) + የአሁኑ ዲጂታል ባርነት (6) + የወደፊቱ የሐሰት መሲህ (6) = 666።

• Binary 11፦ ኖህ መለያየት (Division) ነበር፤ አሁንም ሕዝቡ ወደ 1 (ታዛዥ) እና 0 (አፈንጋጭ) የሚለይበት ኮድ ነው።

እንዴት? (አፈጻጸሙ)

• በኖህ ዘመን በአካል (Physical) የተደረገውን የዘር ብርዘት፣ አሁን በናኖ-ቴክኖሎጂ (Invisible) በደም ውስጥ ማከናወን።

• የሰውን ልጅ ከተፈጥሮአዊ ምግብ ነጥሎ በላቦራቶሪ በተመረዘ (GMO) ምግብ እንዲመገብ በማድረግ ሴሎቹን መለወጥ።

• በሳተላይት (Starlink) እና በ 5G/6G አማካኝነት የሰውን ልጅ አእምሮ በሞገድ በመምታት ንቃተ-ህሊናውን መቆለፍ።

• የሐሰት ተአምራትን (Blue Beam) በመጠቀም ህዝቡ "አማልክት መጡ" ብሎ እንደ ኖህ ዘመን እንዲሳሳት ማድረግ።

• የኢኮኖሚ ማነቆን (ፋይዳ/Cashless) በመጠቀም ሰዎች ለምግብ ሲሉ ነፍሳቸውን እንዲሸጡ ማስገደድ።

• እውነተኛውን መለኮታዊ እውቀት (81 መጻሕፍት) በዘመናዊ ትምህርትና በሚዲያ ውሸት መተካት።

የአተገባበር ስልት

• "The Great Delusion" (ታላቁ ማታለል)፦ ውሸትን እንደ እውነት በማቅረብ ህዝቡ በቅዠት ውስጥ እንዲኖር ማድረግ።

• "Biological Capture"፦ የሰውን አካል በክትባትና በኬሚካሎች በመያዝ ለዲጂታል ትእዛዝ ምቹ ማድረግ።

• "Induced Amnesia"፦ የሰው ልጅ ታሪኩንና ፈጣሪውን እንዲረሳ በማድረግ በቋሚ መዝናኛ ውስጥ መቆለፍ።

• "Controlled Chaos"፦ ጦርነትና ግርግር በመፍጠር ህዝቡ "መዳኛ" ሲል አውሬውን እንዲቀበል ማመቻቸት።

• "Spiritual Replacement"፦ ጸሎትንና ንስሐን በ"ሜዲቴሽንና በቴክኖ-አምልኮ" መተካት።

• "Genetic Lock"፦ አንዴ ዲኤንኤው የተለወጠ ሰው ተመልሶ ንስሐ መግባት የማይችልበትን የህሊና መደንዘዝ መፍጠር።

የተጠቀመው ስልት

• CRISPR-Cas9፦ የሰውን ዲኤንኤ የመቁረጥና የመቀየር ቴክኖሎጂ (ዘመናዊው የዘር ብርዘት)።

• Neuralink፦ አእምሮን ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት (የነፍስ ምርኮ)።

• Artificial Intelligence (AI)፦ የሰው ልጅን የወደፊት ዕጣ-ፈንታ በዳታ መወሰን።

• Geo-engineering፦ የአየር ሁኔታን በመቀየር ድርቅና ጎርፍ በመፍጠር ሰውን ማስገበር።

• Subliminal Priming፦ በፊልምና በሙዚቃ የሰውን ልጅ ለአውሬው ማኅተም ማዘጋጀት።

• Digital Identity (Fayda)፦ ሰውን ወደ ቁጥር በመቀየር መለኮታዊ ስሙን መደምሰስ።

የእድገት ደረጃ

• ደረጃ 1፡ የአስተሳሰብ ለውጥና የሳይንስ አምልኮ (1900-1980)።

• ደረጃ 2፡ የዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታ (1980-2010)።

• ደረጃ 3፡ የባዮ-ቴክኖሎጂ ስርገትና የዲኤንኤ ጥናት (2010-2020)።

• ደረጃ 4፡ የጅምላ ሙከራና የዲጂታል መታወቂያ ማስገደድ (2020-2025) - አሁን ያለንበት።

• ደረጃ 5፡ የሐሰተኛው መሲህ መገለጥና የብሉ ቢም ትርኢት (2026-2028)።

• ደረጃ 6፡ ሙሉ በሙሉ የፈጣሪን አምሳል አጥፍቶ የአውሬውን መንግስት መመሥረት።

እንዴት ውጤታማ ሆኑ?

• የሰው ልጅ ለ"ጥበብና ለምቾት" ያለውን ጉጉት አውሬው ስላታለለበት።

• ቴክኖሎጂው እጅግ ረቂቅ በመሆኑ ህዝቡ ጉዳቱን ማየት ስላልቻለ።

• የሃይማኖት መሪዎች ስለ ዘመኑ ስልታዊ ምስጢር ዝም ማለታቸው።

• አውሬው እውነትን በ"ሥልጣኔና በዕድገት" ስም ስለሸፈናት።

• የኑሮ ውድነትና ጭንቀት ሰውን ለማሰብ ጊዜ ስላልሰጠው።

• የሰው ልጅ ከ 81ዱ መጻሕፍት ትክክለኛ መመሪያ ስለራቀ።

ምን ጥቅም አገኘ?

• አውሬው የሰውን ልጅ ነፍስ በአንድ "ዲጂታል እስር ቤት" ውስጥ ቆለፈ።

• የሰውን ልጅ ነጻ ፈቃድ ወደ "አልጎሪዝም ታዛዥነት" ለወጠው።

• የኢትዮጵያንና የጥንታውያንን የመከላከያ ምስጢር በዳታ ቀበረው።

• የሰውን ልጅ ነፍስ ከፈጣሪዋ ነጥሎ "ለማሽኑ አምላክ" አስገዛ።

• ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ ተቃውሞ ገና ሳይወለድ እንዲጠፋ አደረገ።

ሰይጣን በምድር ላይ ያለ ተቃዋሚ የመንገሥ ዕድል አገኘ
ክፍል ሁለት ይቀጥላል ቸር ያሰማን።

Post a Comment

0 Comments