የኖህ ዘመን እና የአሁኑ ዘመን፦ የባዮ-ዲጂታል ጥፋት ምስጢር

✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ

   ክፍል ሁለት

ሙሉውን ሳታነብ ለኮሜት አትሯሯጥ የእኔ አትሌት!

ይህ የነፍስ ና የመንፈስ እይታ ንባብ ነው እስከ ክፍል አንድንም አንብበው ተመልሰህ  ተከተለኝ ወዳጄ፦

አሁን ያለንበት ዘመን ከኖህ ዘመን የሚለየው ጥፋቱ በውሃ ሳይሆን በ"እሳትና በቴክኖሎጂ ውድቀት" የሚመጣ መሆኑ ነው። አንድነታቸው ግን የሰው ልጅ ዲኤንኤ (DNA) በወደቁ መናፍስትና በሳይንስ ጥምረት መበረዙ (Transhumanism) ነው። ፍጻሜውም አምላክ ያላመነውንና የፈጣሪን አምሳል በቴክኖሎጂ የለወጠውን ትውልድ በታላቅ ፍርድ ማጥፋት ነው።

መግቢያ (የአውሬው ስርዓት ዕይታ)

አውሬው አሁን ያለውን ዘመን እንደ "ኒኦ-ኖህ" (Neo-Noah) ምዕራፍ ነው የሚመለከተው፤ በኖህ ዘመን ሳይጠናቀቅ የቀረውን የሰው ልጅን ዝርያ የመቀየር ፕሮጀክት አሁን በቴክኖሎጂ ለመጨረስ ይጥራል።

በሥርዓቱ እይታ፣ የኖህ ዘመን ጥፋት የመጣው በ "መረጃ ብክለት" (አጋንንታዊ ጥበብ ለሰው በመገለጡ) እንደነበረ ሁሉ፣ አሁንም መረጃን ለጥፋት እያዘጋጀ ነው።

አውሬው በኖህ ዘመን የነበሩትን "ኔፊሊም" (Nephilim) አሁን በሰው ሰራሽ አስተዋይነት (AI) እና በባዮ-ቴክኖሎጂ ለመተካት ይሰራል።

ስርዓቱ አሁን ያለንበትን ዘመን "የጄኔቲክ ነጻነት" ብሎ የሚጠራው ሲሆን፣ ይህም ማለት የፈጣሪን ዲኤንኤ ሰርዞ የአውሬውን ኮድ መጫን ነው።

አውሬው የኖህን መርከብ በ"ዲጂታል ዳታቤዝ" (Cloud/Metaverse) በመተካት፣ ነፍሳትን ወደ ምናባዊ መጠለያ ለመውሰድ እየሰራ ነው።

ከመጋረጃ ጀርባ፣ ይህ ዘመን የሰይጣን የመጨረሻው የበቀል እርምጃ ተደርጎ ተሰልቷል።

ያመጣው ውጤት

• የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ ታሪክ ሆኖ ቀረ፤ ሁሉም ነገር በ"ኮድ" ተወሰነ።

• የሰዎች የግል ምስጢር ጠፋ፤ ሁሉም በአውሬው ዐይን ስር ሆነ።

• እውነተኛ ፍቅር ጠፍቶ "ዲጂታል ጥቅመኝነት" በማህበረሰቡ ውስጥ ነገሰ።

• የሰዎች አእምሮ በቋሚ ስጋትና በሞገድ ቁጥጥር ውስጥ ወደቀ።

• እውነተኛ አማኞች ከኢኮኖሚና ከማህበራዊ ሕይወት ተገፉ።

• ምድር የነፍሳት መቃብርና የዲጂታል ባርነት ማዕከል ሆነች።

በሰው ልጅ ኑሮና ነፍስ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

• የንቃተ-ህሊና ሽባነት፦ የ 5G/AI ሞገዶች የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ግንኙነት በማወክ፣ ጸሎትና ንስሐ የማይሰምርበት የ"መንፈስ ጭጋግ" ይፈጥራሉ።

• የባዮሎጂካል ባርነት፦ የሰው ልጅ ዲኤንኤ ሲለወጥ፣ የፈጣሪ አምሳልነቱ ስለሚጠፋ ለዘላለማዊ ህይወት ብቁ እንዳይሆን ያደርገዋል።

• የሕሊና ምርኮ፦ ሰው በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በአውሬው አልጎሪዝም ትእዛዝ እንዲቆጣ፣ እንዲያዝንና ሐሰተኛ ደስታ እንዲሰማው ይደረጋል።

• የኑሮ ሽባነት፦ ያለ ፋይዳና ያለ ስርዓቱ ፈቃድ መኖር የማይቻል በመሆኑ፣ ሰው ለሆዱ ሲል ነፍሱን እንዲሸጥ ይገደዳል።

• የማንነት መጥፋት፦ ሰው ራሱን እንደ "ጎሳ ወይም ቁጥር" እንጂ እንደ መለኮት ልጅ ማየት ያቅተዋል።

• ዘላለማዊ ተስፋ መቁረጥ፦ ነፍስ በማትሪክሱ ውስጥ ታስራ ስለምትቀር፣ ስለ መንግስተ ሰማያት ማሰብን ትተዋለች።

የሚያሳየው ግልጽ ምልክቶች

• እንደ ኖህ ዘመን የሞራል ውድቀትና ግብረ-ሰዶማዊነት በህግ መጽደቁ።

• የሰው ልጅን መታወቂያ በባዮሜትሪክስና በዲጂታል ቁጥር  መተካት።

• በየመንገዱ የአውሬው ምልክቶች (ፒራሚድ/አይን) በዝተው መታየታቸው።

• የሐሰት ተአምራትና የሰማይ ድምጾች መጀመር።

• ጥሬ ገንዘብ ጠፍቶ ሁሉም ግብይት በስልክና በኮድ መደረጉ።

• ቤተክርስቲያን ስለ እውነተኛው የፍጻሜ ዘመን ምስጢር ማስተማር ማቆሟ።

እንዴት የመቆጣጠር ኃይል አገኘ?

• በመረጃ የበላይነት (የመጋረጃው ግርዶሽ)
• በባንክና በኢኮኖሚ ማነቆ (የሆድ ቁጥጥር)
• በዲጂታል ማንነት (የመለያ ቁጥጥር)
• በህግ የበላይነት ስም በሚደረግ አፈና
• በሳተላይትና በ 5Gክትትል
• በሰዎች መንፈሳዊ ዕውርነት

ህዝቡ ለምን አልነቃም?

• ምክንያቱም ሥርዓቱ "ለሥልጣኔ፣ ለሰላምና ለደህንነት" ተብሎ ስለቀረበ።

• ሰዎች ስለ ዘመኑ ስልታዊ ምስጢር ዕውቀት ስለሌላቸው።

• እውነቱን የሚናገሩት "አክራሪና ጸረ-እድገት" ተብለው ስለሚሳለቁባቸው።

• በአውሬው የተዘረጋው የ"ጅምላ ማደንዘዣ።

• በኑሮ ውድነትና በጦርነት የደከመ ሕዝብ "አዳኝ" ስለናፈቀ
• የሰው ልጅ የፈጣሪውን ቃል (81ዱ መጻሕፍት) መመሪያ ስለዘነጋ።

ቀጣይ እቅድ እና አፈጻጸም

• የሰውን ልጅ አእምሮ በቀጥታ ከ Cloud ሰርቨር ጋር ማገናኘት (Neuralink)።

• ሐሰተኛው  በሰማይ ተአምር እያሳየ ለአዲሱ ሥርዓት እንዲሰገድ ማድረግ።

• እውነተኛ አማኞችን (ሥርዓቱን የማይቀበሉትን) "የዓለም ጠላት" በሚል ማደን።

• ጥሬ ገንዘብን ሙሉ በሙሉ አጥፍቶ ወደ "ዲጂታል ማኅተም" መሸጋገር።

• ሙሉውን ዓለም ወደ አንድ ግዙፍ "ዲጂታል ሲሙሌሽን" መቀየር።

• የሰውን ልጅ ነፍስ ወደ "ዘላለማዊ ዲጂታል እስር ቤት" ማስገባት።

በአብዛኛው የየት ቦታ ይጠቀምባቸዋል?

• በትልልቅ ከተሞች
• በማህበራዊ ሚዲያና በስማርት ፎኖች
• በሰዎች አእምሮ ውስጥ (በንዝረት)

ተመስርቶ ማለቁን በምን እንለየው?

• ያለ ፋይዳ መታወቂያ ዳቦ መግዛት የማይቻል ሲሆን
• የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ በአልጎሪዝም ትእዛዝ ሲተካ
• ሰዎች ለፈጣሪ ሳይሆን ለ"ሥርዓቱ ውጤት" (AI) ሲሰግዱ
• በየመንገዱ የአውሬው ምልክቶች በዝተው ሲታዩ
• 81ዱ መጻሕፍትና እውነተኛ አምልኮ እንደ "ወንጀል" ሲቆጠሩ
• እውነቱ ሲገለጥ ዓለም በአንድ ዲጂታል መሪ (Antichrist) ስር ስትወድቅ

መንቃት እና መትረፍ የሚቻለው እንዴት ነው?

• ወደ 81ዱ መጻሕፍት መመለስ፦ እውነተኛውን የመለኮት ዳታ ማወቅ።

• በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና ደም መታተም (ብቸኛው የነፍስ ጋሻ!)።

• ከዲጂታል መሳሪያዎችና ከሥርዓቱ ጥገኝነት በተቻለ መጠን ራስን ማራቅ።

• ወደ ገጠርና ወደ ተፈጥሮአዊ ኑሮ  መመለስ።

• በጾም እና በጸሎት "የመለየት መንፈስን መጠየቅ።

• እርስ በእርስ በመረዳዳት "የንቃት ማህበረሰብ" መፍጠር

ማስረጃ እና በተግባር

• የ CRISPR ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በሰው ሽል ላይ (የዘር ብርዘት)።

• በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ፋይዳና ባንክ አገልግሎት ያላቸው ጥምረት።

• የ 5G/ማማዎች በየመንገዱ ያለ ገደብ መተከላቸው።

• በዓለም ዙሪያ የታዩት የሆሎግራም  ሙከራዎች።

• የዲጂታል ብር (CBDC) ሙከራዎችና ጥሬ ገንዘብን የማጥፋት ሂደት።

• በራእይ 13 የተነገረው ትንቢት አሁን በዘመኑ ቴክኖሎጂ በኩል መፈጸሙ።

የመፍትሔ ሃሳብ

• መንፈሳዊ ንቃትና ዝጁነትን ማሳደግ።

• ከስርዓቱ ጥገኝነት ለመውጣት በራስ አቅም መኖርን መልመድ።

• እውነተኛውን የኢትዮጵያ ታሪክና የ 81 ዱን መጻሕፍት ምስጢር በጥልቀት እወቅ።

• በክርስቶስ ኢየሱስ ስም መታተምና በቅዱስ ቁርባን መጽናት።

• መረጃዎችን ለሌሎች በጥበብ ማካፈል (ማንቃት)።

• በፈጣሪ ጥበቃ ላይ ፍጹም እምነት መጣል (ድሉ የክርስቶስ ነው!)።

ወዳጄ አሁን ያለንበት ዘመን ከኖህ ዘመን የባሰ የመጨረሻው የነፍስ ምርኮ ሰዓት ነው። በኖህ ዘመን ውሃ ስጋን አጥፍቷል፤ በዚህ ዘመን ግን ቴክኖሎጂ ነፍስን ሊቀብር መጥቷል። እውነተኛው ነጻነት ያለው ከሥርዓቱ ውጭ በሆነው መለኮታዊ ብርሃን ውስጥ ነው። ንቃ! ነፍስህ ከአልጎሪዝም በላይ ናት። እውነተኛው አምልኮ በልብና በመንፈስ የሚሆን ነው። 

Post a Comment

0 Comments